CURRENT

የዘንድሮ የሓጂ ጉዞ ታሪካዊ የኣል ነጃሺ መስጂድ በመጎብኝት ይሆናል

By Admin

June 29, 2017

የዘንድሮ የሓጂ ጉዞ ታሪካዊ የኣል ነጃሺ መስጂድ በመጎብኝት ይሆናል

ከያዝነው አመት ጀምሮ ወደ  መካ የምደረግ ሃይማኖታዊ የሓጂ ጉዞ ታሪካዊ የኣል ነጃሺ መስጂድ በመጎብኝት ይሆናል። በያዝነው አመት ከነሃሴ 01/2009 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ኣስር ቀናት በሚደረገው የሓጂ ጉዞ፤ የሃይማኖቱ ምእመን ከመላው ሃገሪቱ በኣል ነጃሺ መስጂድ በመጋናኘት በአለም የመጀመርያ የእስልምና ሃይማኖት ኣማኞች ያረፍበቱን ቅዱስ ደርሒ ፆሎት በማድረግና በመጎብኘት በቀጥታ በመቐለ ከተማ ከሚገኘው የኣሉላ ኣባነጋ የአየር ማረፍያ ሜዳ በመነሳት ወደ መካ ይሄዳሉ።

ከሃገረ ሱዳን የመጡ ልኡካን በኣልነጃሺ የሚገኝ ደርሒ/የቅዱሳን መቃብር/ ፆሎት እያደረጉና እየጎበኙ

ይህ ውሳኔ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የኢትዮጵያ  የእስልምና ጎዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና የኢትዮጵያ ኣየር መንገድ በመተባበር ተግባራዊ ይሆናል። ከያዝነው አመት የሚጀምረው ይህ ስራ በተጣናከረ መንገድ ቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል የሓጂ እና የዑምራ ጉዞዎች እንደሚነሩ የጋራ ኮሚቴው ገልፀዋል።

በመቐለ ከተማ የሚገኙ የኣገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና ኣስጎብኚ ድርጅቶች እንግዶቻቸውን በሚያስደስትና ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ይዞት የጠበቀ ኣቀባበል ለማድረግ በዝግጅትላይ ናቸው።

ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የትግራይ ክልልን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ወደላቀ ደረጃ የሚያሸጋገር እና ቱሪዝም ፍሰት በማስፋት ሃገራችን ከዚህ ዘርፍ ተጠቃሚነቷ የሚያረጋግጥ ጥሩ ጅምር ነው።

ጅምሩ በሚቀጥሉት ተከተታታይ አመታት ከአፍሪካ እና ከመላው አለም ወደ መካ የሚያደርጉት የሓጂ እና የዑምራ ጉዞዎች የኣል ነጃሺ መስጂድን እንደ ዋነኛ መዳረሻቸው በመውሰድ መሸጋገርያቸው/ትራዚት/ ለማድረግ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

በልማት ላይ ያለ የኣልነጃሺ መስጂድ በከፊል

 

የትግራይ ባህል ቱሪዝም ቢሮ