Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለዜጎቹ ደህንነት የሚቆረቆር መንግስት

0 434

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለዜጎቹ ደህንነት የሚቆረቆር መንግስት

                                                           ታዬ ከበደ

የኢትዮጵያ መንግስት ለህዝብ የወገነ ነው። ይህ ማንነቱም በተለይ በሳዑዲ መንግስት ህገ ወጥ ተብለው ለተፈረጁ የሀገራችን ዜጎች እየተገለፀ ነው። መንግስት የሳዑዲ ስደተኞች ወደ ሀገራቸው ያለ አንዳች ችግር እንዲመለሱ ያደረጋቸውን ተግባሮች እጅግ የሚያስመሰግነው ነው።

የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፤ የምህረት አዋጁ እንደወጣ ሰሞን ስደተኞቹ ያለ ችግር ወደ ትውልድ ሀገራቸው እንዲመለሰሱ ከሳዑዲ መንግስት ጋር የሚነጋገር ከፍተኛ የመንግስት ልዑካን ቡድን ሪያድ በመገኘት ኢትዮጵያዊያኑ ንብረታቸውን ይዘው እንዲገቡ በማድረግ ስምምነት አድርጓል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁም ተመላሽ ስደተኞች ወደሚገኙበት የተለያዩ ስፍራዎች በማቅናት አበረታትተዋቸዋል።

መንግስት ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው ሲገቡም በርካታ የመገልገያ ዕቃዎቻቸውን ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ፈቅዷል። እነዚህ ከታክስ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱ ቁሳቁሶች ዝርዝር፣ ስደተኞች ጅዳና ሪያድ በሚገኙ የኤምባሲው ቢሮዎች እንዲሁም የጉዞ ሰነዶች በተዘጋጁላቸው ሁሉም ቦታዎች ማግኘት እንደሚችሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማስታወቁ አይዘነጋም። እስካሁን ድረስም 46 ሺህ ያህል ስደተኞች ተመልሰዋል።

ያም ሆኖ አሁንም ህገ ወጥ ደላላዎች የተሳሳቱ ወሬዎችን እየነዙ ነው። ስደተኞቹም ባለማወቅ ለእነርሱ አሁንም ገንዘብ ከፍለው የሚሄዱት ወገኖች እንዳይቀሩባቸው በመስጋት መሆኑን ሰነዱን ያልወሰዱት ዜጎች ሊያውቁ የሚገባ ይመስለኛል። ህገ ወጥ ደላለዎቹ የሳዑዲ መንግስት ከሚወስዳቸው ርምጃዎች ሊያስጥሏቸው እንዳማይችሉም ማወቅ አለባቸው።

ያም ሆኖ ህገ ወጥ ደላላዎቹ ያሻቸውን ቢያወሩም፤ የሳዑዲ መንግስት ፍላጎት ግን የየትኛውም ሀገር ዜጋ በህጋዊ መንገድ በሀገሩ ውስጥ ተመዝግቦ እስካልኖረ ድረስ ከሀገሩ ማስወጣት መሆኑን ዜጎቻችን መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

ያም ሆኖ አሁንም ህገ ወጥ ደላላዎች የተሳሳቱ ወሬዎችን እየነዙ ነው። ስደተኞቹም ባለማወቅ ለእነርሱ አሁንም ገንዘብ ከፍለው የሚሄዱት ወገኖች እንዳይቀሩባቸው በመስጋት መሆኑን ሰነዱን ያልወሰዱት ዜጎች ሊያውቁ የሚገባ ይመስለኛል። ህገ ወጥ ደላለዎቹ የሳዑዲ መንግስት ከሚወስዳቸው ርምጃዎች ሊያስጥሏቸው እንዳማይችሉም ማወቅ አለባቸው።

ይሁንና ህገ ወጥ ደላላዎቹ ያሻቸውን ቢያወሩም፤ የሳዑዲ መንግስት ፍላጎት ግን የየትኛውም ሀገር ዜጋ በህጋዊ መንገድ በሀገሩ ውስጥ ተመዝግቦ እስካልኖረ ድረስ ከሀገሩ ማስወጣት መሆኑን ዜጎቻችን መገንዘብ ይኖርባቸዋል። መጋቢት 21 ቀን 2009 ዓ.ም የተጀመረው የምህረት አዋጅ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም ተጠናቋል።

ሆኖም መንግስት ባደረገው ጥረት የአንድ ወር ጭማሪ ተደርጓል። ታዲያ ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ የጉዞ ሰነዶችን መውሰድ ያለባቸው ይመስለኛል። የ30 ቀናት ጭማሪ በጣም ብዙ ነው።

በአሁኑ ወቅት በህገ ወጥነት በሳዑዲ ውስጥ የሚገኙት ዜጎች ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ ፍላጎት ካላቸው በህጋዊ መንገድ ወደዚያው ማቅናት ይችላሉ። ምክንያቱም የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ መንግስቶች ዜጎች በህጋዊ መንገድ ተገቢውን ስልጠና ወስደው ወደ ሳዑዲ እንዲሄዱ የሚያስችል ስምምነት በቅርቡ በመፈራረማቸው ነው። እናም ይህን መፃዒ ዕድል ለመጠቀም በዚያች ሀገር የሚገኙት ዜጎች በቅድሚያ ወደ ሀገር ቤት መምጣት ይኖርባቸዋል። ይህ ወርቃማ ዕድል ሊያመልጣቸው የሚገባ አይመስለኝም።

ርግጥ መንግስት ለዜጎቹ አቅሙ በፈደቀ መጠን ድጋፍ እያደረገ ነው። ቀደም ሲል በማሳያነት ያቀረብኳቸውና ከሳዑዲ መንግስት ጋር ዜጎች በያሉበት ቦታ ሁሉ የጉዞ ሰነዶችን እንዲወስዱ የማመቻቸት፣ ከሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር የዜጎቹን ህይወትና ንብረት ለመታደግ ያደረጋቸው ስምምነቶች፣ ዜጎቻችን ንብረታቸውን ሳይቀሙና አሻራ ሳይሰጡ እንዲወጡ እንዲሁም አየር መንገዱ መዳረሻዎቹን እንዲጨምርና የትኬት ዋጋም በግማሽ እንዲቀንስ ማድረጉ ብሎም ሌሎች ጥረቶች ማከናወኑን መጥቀስ ይቻላል።

በእኔ እምነት ይህ የመንግስት ጥረት አቅም በፈቀደ መጠን የተከናወነ ነው። ስደተኞቹ ወደ ሀገር ቤት ከመጡ በኋላም እንደ ማንኛውም ዜጋ በሀገሪቱ ውስጥ እየተሳለጠ በሚገኘው የልማት ስራዎች ውስጥ በአቅማቸው ሊሳተፉ ይችላሉ። በቂ ጥሪት ያላቸውም ሀገራቸው ውስጥ ባለው ምቹ የኢንቨስትመንት መስክ በግልም ይሁን በጥምረት ተሳትፎ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ይህ ሀገር በዕድገት ላይ የሚገኝ በመሆኑም ሁሉም ዜጋ በየደረጃው በልማቱ ላይ እንደሚያደርገው አስተዋፅኦ ተጠቃሚ እንደሚሆነው ሁሉ፤ እነርሱም በልማቱ ላይ በሚጫወቱት ሚና ልክ ተጠቃሚ ይሆናሉ። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ መንግስት ይህን ሁኔታ ያመቻቻል—ለማንኛውም ዜጋ እንደሚያደርገው ሁሉ።

እናም ለተመላሾቹ አቅም በፈቀደ መጠን እንደ ማንኛውም ዜዳጋ ድጋፍ ይደረጋል። በእነዚህ ሀገራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ይሳተፋሉ ማለት ይመስለኛል። የተለየ ፍላጎት ሊኖርበትም ይሁን የተለየ ትርጓሜ ሊሰጠው ይገባል ብዬ አላምንም። መንግስት ማድረግ ያለበት ድጋፍ ለሌላው ዜጋው የሚከውነውን ተግባር ነውና።  

በአሁኑ ወቅት መንግስትና ህዝቡ በሀገራችን ውስጥ እየፈጠሩት ያለው ሁኔታ ለሚሰራ ማንኛውም ዜጋ የተመቻቸ ነው። በእኔ እምነት በሳዑዲ ይኖሩ የነበሩት ዜጎቻችን ማናቸውንም የስራ ዓይነቶች በሚገባ ይገነዘባሉ። ይህን ሁኔታም በሚገባ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ርግጥ በመጀመሪያው የጊዜ ገደብ የኢፌዴሪ መንግስት ባመቻቸው ሁኔታ ተጠቅመው በርካታ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ከዚያች ሀገር እየወጡ ነው። ያለ አንዳች ችግርም ከቤተሰቦቻቸውና ከህዝባቸው ጋር እየተቀላቀሉ ነው።

መንግስት የጊዜ ገደቡ ካለቀ በዜጎቹ ላይ ሊከተል የሚችለውን አደገኛ ሁኔታ ከወዲሁ በመገንዘብ ስደተኞቹ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል።

መንግስት የሀገሪቱ ህዝቦች ንብረት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ባወጣው የምህረት አዋጅ ምክንያት ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ያለ አንዳች ችግር በፍጥነት መጓጓዝ እንዲችሉ ከማድረጉም በላይ፤ በጉዞው የትኬት ዋጋ ላይ የ50 በመቶ ቅናሽ ማድረጉ ሰሞኑን ተገልጿል። በዚህም ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ ለአንድ ጉዞ ይጠይቅ የነበረውን አንድ ሺህ 800 የሳዑዲ ሪያል ወደ 900 ሪያል ዝቅ አድርጓል።

ቅናሹ ህጋዊ የመኖሪያና የስራ ፈቃድ ለሌላቸው እንዲሁም ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ዜጎች ብቻ የተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በአየር መንገዱ የተደረገው ቅናሽ ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት አንድ አካልና ማበረታቻ መሆኑን በማብራራት ጭምር።

እነዚህ ከላይ የጠቃቀስኳቸው ጥቂት ጉዳዩች መንግስት ምን ያህል ዜጎቹ የሚጨነቅ መሆኑን የሚያሳዩ እውነታዎች ናቸው። አሁንም በተገኘው ተጨማሪ የአንድ ወር ጊዜ ተመላሾቹ ወደ ሀገራቸው መምጣት ይኖርባቸዋል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy