Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በመቀሌ ለ1 ሺህ 582 መምህራንና የጦር አካል ጉዳተኞች የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ ተሰጠ

0 1,182

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ለ1 ሺህ 582 መምህራን እና የጦር አካል ጉዳተኞች ለመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታ በዛሬው እለት በእጣ አስተላልፏል።

ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚሆነው ቦታው ለ1 ሺህ 332 መምህራን እና ለ250 የጦር አካል ጉዳተኞች ነው በዛሬው እለት ተላልፎ የተሰጠው።

ለጦር አካል ጉደተኞቹ በከታማዋ ለሊዝ ጨረታ ተብሎ ተለይቶ የነበረ ቦታ የተሰጣቸው መሆኑም ተገልጿል።

እንዲሁም ለመምህራኑ አዲስ የመምህራን መንደር እንዲፈጠር በማሰብ በሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ነው የመኖሪያ ቤት መገንቢያ ቦታው ተላልፎ የተሰጠው።

ለጦር አካል ጉዳተኞች እና መምህራንም 140 ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ከከተማ ከመቀሌ ተከማ አስተዳደር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር እና የክልሉ የከተማ ልማት፣ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ፥ የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ብርሀነ ገብረኢየሱስ በበኩላው፥ በከተማዋ ውስጥ ለመኖሪያ ቤት የሚሆን ቦታን ለማዘጋጀት መንግስት 177 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ካሳ ከፍሏል ብለዋል።

መንግስት ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሰጠውን መሬት በመካከለኛ የሊዝ ዋጋ ቢሸጥ እንኳ 10 ቢሊየን ብር ያገኝበት እንደነበርም ተናግረዋል።

በሙልጌታ አፅብሀ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy