Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በኦሮሚያ የስነምግባር ጉድለት በተገኘባቸው የህግ ስራ አስፈጻሚ ሰራተኞች ላይ እርምጃ ተወሰደ

0 449

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በኦሮሚያ ክልል የስነምግባር ጉድለት በተገኘባቸው ዳኞች፣ የህግ ኦፊሰሮችና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት ገለጹ፡፡

የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የሥራ ዘመን ሁለተኛ ዓመት ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

በዛሬው ውሎው የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶችን ሪፖርት አድምጧል።

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ አዲሱ ቀበኔሳ፥ በፍትህ ስርዓቱ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን አቅርበዋል።

በሪፖርታቸውም በክልሉ ያሉ ፍርድ ቤቶች ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን አንስተዋል፥ ለዚህም በክልሉ ከቀረቡ 565 ሺህ በላይ የክስ መዝገቦች ለ517 ሺህ መዝገቦች ውሳኔ መሰጠቱን ጠቅሰዋል።

የፍትህ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማረጋገጥና ጥራቱን ለማሻሻል በተደረገው ጥረትም አሁን ላይ አፈጻጸሙ ከ91 በመቶ በላይ መድረሱን አስረድተዋል።

ፕሬዚዳንቱ በሪፖርታቸው በዳኝነት ስርዓቱ ላይ የታየዩ ደካማ አፈጻጸሞችንም አቅርበዋል።

ከአድሎ የፀዳ ፍርድ አለመስጠት፣ የአመለካከት ችግር እና ኪራይ ሰብሳቢነት የዳኝነት ስርዓቱ ተግዳሮቶች መሆናቸውንም ገልጸዋል።

እነዚህ ችግሮች የዳኝነት ስርዓቱ በህብረተሰቡ ዘንድ አመኔታ እንዳያገኝ ማድረጉን ጠቅሰው፥ የችግሩ ምንጮች ናቸው በተባሉ ዳኞች፣ የህግ ኦፊሰሮች እና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም ነው የገለጹት።

በዚህም ባለፈው አመት የማጥራት ስራ ሲሰራ ለዚህ አመት ከተሸጋገሩ ውስጥ 5 ዳኞች እና 9 የህግ ኦፊሰሮችና ድጋፍ ሰጭ ባለሙያዎች ከስራ መሰናበታቸውን ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም 18ቱ ከደረጃቸው ዝቅ እንዲሉ ሲወሰን 66ቱ ደግሞ በገንዘብ እንዲቀጡ ተደርጓል።

በተጨማሪም በጥልቅ ተሃድሶ ግምገማው በፍርድ ሂደቱ ለሚፈጠሩ ቅሬታዎች መንስኤ ናቸው በተባሉ፥ ከባለሙያ እስከ ፕሬዚዳንት የሚደርሱ 71 አመራሮች ከሃላፊነት እንዲነሱ መደረጉም በሪፖርቱ ተጠቅሷል።

በቀጣይም የዘርፉን አገልግሎት ጥራት ለማስጠበቅ በሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነትና አድሏዊ አሰራር ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል።
በሰርካለም ጌታቸው

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy