Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም መስፈን ቁርጠኛ ሆና ትሰራለች- ውጭ ጉዳይ

0 861

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን  ኢትዮጵያ ትኩረት ሰጥታ እየተንቀሳቀሰች እንደሆነ የውጭ ጉዳይሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ገለፁ᎓᎓

ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ለአሜሪካ ኮንግረስ አባላትና ሰራተኞች በዋይት ሃውስ ተገኝተው ስለኢትዮ አሜሪካ ግንኙነት ገለፃ አድርገዋል᎓᎓

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ፤ ብሄራዊ ደህንነት ፖሊሲባ እስትራቴጂ ዋንኛ ግቦች  ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ማረጋገጥ፤ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መፍጠር፤ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጪ ፖሊሲዋ እንዲጣጣም ማድረግ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የሆነ የኢንቨስትመንት መዳረሻ እየሆነች መምጣቷን የተናገሩት ሚኒስትሩ እየተከናወኑ ያሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች፤ ግዙፍ የሆኑ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግድቦች ግንባታዎች፤  ከጎረቤተ ሃገራት ጋር በመሰረተ ልማት መተሳሰር፤ አለም አቀፋዊና ቀጠናዊ ስብሰባዎችን ማስተናገዷ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲና ስትራቴጂ ትክክለኛነት ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል᎓᎓

በቀጠናዊ ጉዳዮችም ኢትዮጵያ  በምስራቅ አፍሪካ ሰላምና መረጋጋት እንዲፈጠር ንቁ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል᎓᎓

ተሳታፊዎችም ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ሰላም እንዲሰፍን የምታደርገውን እንቅስቃሴ አድንቀው ለወደፊቱም እንደዚህ ያለ ውይይት እንዲደረግ ሃሳብ አቅርበዋል᎓᎓

በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የውጪ ግንኙነቶች ሊቀመንበር ሴናተር ቦብ ኮከር በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ዋንኛ አቀንቃኝ ናት ብለዋል፡፡

ሁለቱም ወገኖች አሁን ያለውን የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ እንደሚሰሩ አብራርተዋል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy