Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ለዓለም አቀፍ ሽልማት ታጨች

0 1,058

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሽልማት መታጨቷ ተገልጿል።

የአካባቢ ተፈጥሮ ሀብት ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ ምርጥ ተብለው፥ በተባበሩት መንግስታት የበረሃማነት መከላከል ምክር ቤት ለመጨረሻ ዙር ውድድር ከታጩ ስድስት የዓለም ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ መመረጧ ነው የተነገረው፡፡

የትግራይ ክልል ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር አትንኩት መዝገቡ እንደገለፁት፥ በቀጣይ ሁለት ወራት በቻይና በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድርና ሽልማት ላይ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በተከናወኑ ተግባራት በእጩነት መቅረቧን ተናግረዋል ።

ኃላፊው “ክልሉ ላለፉት 29 ዓመታት በረሃማነትን ለመከላክል በህዝብ ነፃ ጉልበት ባከናወነው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ፥ ያስመዘገበው ተጨባጭ ለውጥ በመረጋገጡ ሀገሪቱን ለእጩነት እንድተበቃ አድርጓታል” ብለዋል ።

በክልሉ በተካሄደው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ከ100 ሺህ ሄክታር የሚበልጥ መሬት ከጎርፍ መሸርሸር አደጋ ማዳኑን ለአብነት ጠቅሰዋል።

በዘርፉ በየዓመቱ ህዝቡ የሚያደርገው የነፃ ጉልበት ተሳትፎ በአማካይ 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ግምት እንዳለው ኃላፊው አመላክተዋል።

የአፈር መሸርሸርንና የአየር ንብረት መዛባትን ለመከላከል በየዓመቱ በአማካይ ከ147 ሚሊየን በላይ ችግኝ እንደሚተከልም ተናግረዋል ።

ምንጭ፡-ኢዜአ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy