Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት ተመረቀ።

0 659

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

#የበለጸገች_ኢትዮጵያ የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በዛሬው እለት ተመረቀ።

በመቐለ ከተማ የተገነባው የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያምን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች እና የክልሉ አመራሮች በተገኙበት በዛሬው እለት ተመረቀ።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ በራእይ 2025 ያስቀመጠችው የኢኮኖሚ ተሀድሶ እቅድ በማሳካት እና በተለይም በማንፉክቸሪንግ ዘርፍ መሬት ላይ የሚታዩ ተጨባጭ እውነታዎች በመመስረት ረገድ መንግስት ለጀመረው ስኬታማ ጉዞ ቋሚ ማሳያዎች በመሆናቸው የሚሰጠው ትርጉም የተለየ መሆኑን በመግለፅ ኢትዮጵያን በአፍሪካ የማንፋክቸሪንግ ዘርፍ መሪ ማእከል ለማድረግ የተቀየሰው የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂ በትክክለኛ መስመር ላይ እየተጓዘ ስለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ ገልፀዋል።

የመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክ በአቅራብያው ባሉ ከተሞች የንግድ፣

የሆቴልየመኖርያ ቤቶች ስራ እና ሌሎች የአገልግሎቶች ዘርፍላይ የሚፈጥረው መነቃቃት የላቀ መሆኑን በማውሳት ይህ የኢኮኖሚ መነቃቃት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ያደርግ ዘንድ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥረት እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አምባሳደር ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ በበኩላቸው ጠንካራ የኢኮኖሚ ውድድር ባለበት ዘመን ኢንዱስትሪው የሚጠይቀውን ከፍተኛ ምርታማነት ሆነ የሀገራችን ኢኮኖሚ በተለይም አምራች ዘርፉ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚኖረው ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ በመደበኛነት ከሚሰጡ የድጋፍ እና የማበረታቻ ማእቀፎች በተጨማሪ የሰራተኞች እውቀት እና ክህሎት ከየኢንዱስትሪዎቹ ልዩ ፍላጎት ጋር በማጣጣም በፍጥነት ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀው። በመቐለ ኢንዱስትሪ ፓርክም የክህሎት ማበልፀግያ ማእከል እንዲቋቋም እና ዘርፍ ተኮር የስልጠና መርሀ ግብሮች እንዲደራጁ ለማገዝ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy