Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዘጠኝ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

0 2,074

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው 34ኛ መደበኛ ስብሰባው ዘጠኝ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ምክር ቤቱ ከተወያየባቸው ረቂቅ አዋጆች መካከል የኢፌዴሪ መንግስት ከአለም ነዳጅ ላኪ ሃገራት (ኦፔክ) ዓለምአቀፍ ልማት ፈንድና ከዓረብ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማት ጋር፥ ለሻምቡ-አጋምሳ የመንገድ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የተፈረሙ የብድር ስምምነቶች ይገኙበታል።

በመንግስትና በአፍሪካ ልማት ፈንድ መካከል ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳኒቴሽንና ሃይጂን ብሄራዊ ፕሮግራም እንዲሁም፥ ለሞጆ ሀዋሳ የፍጥነት መንገድ ማስፈፀሚያ ከቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ ጋር በተደረገ የብድር ስምምነት ላይም ተወያይቷል።

ለአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫና ለአዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ በኢትዮጵያና በቻይና ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ መካከል፥ እንዲሁም ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የሊዝና የብድር አገልግሎቶች ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር በተደረጉ የብድር ስምምነቶች ላይም መክሯል።

የብድር ስምምነቶቹ ከሃገሪቷ የብድር ስትራቴጂ ጋር የሚጣጣሙ በመሆናቸው ይጸድቁ ዘንድም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መርቷቸዋል።

ምክር ቤቱ ከብድር ስምምነቶቹ ባለፈም የኢትዮጵያ ምርት ገበያን ማቋቋሚያ አዋጅና የቡና ግብይትና ጥራት ቁጥጥርን ለማሻሻል በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ በመወያየት ምክር ቤቱ እንዲያፀድቀው መላኩን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy