የሳውዲ አረቢያ መንግስት ሰነድ አልባ ለሆኑ ዜጎች የሰጠው የእፎይታ ጊዜ በተጨማሪ አንድ ወር አራዘመ
የኢፌዴሪ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ዜጎቻችንን ከሳውዲ አረቢያ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የእፎይታ ጊዜውን በአንድ ወር ማራዘሙን የሳውዲ አረቢያ መንግስት አስታውቋል።
ዜጎቻችን ይህን እድል ተጠቅመው እራሳቸውን ከህግ ተጠያቂነት እና እንግልት ለማዳን ሪያድ፣ጂዳ፣ እና ሌሎች አገልግሎቱን በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች በመገኘት የጉዞ ሰነድ በመውሰድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እናሳስባለን።
አሁን የተራዘመው የእፎታ ጊዜ እስከ ነሃሴ 18 ቀን 2009 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተገለጸው።