Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የስደት በር ይዘጋ!

0 432

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የስደት በር ይዘጋ!

                                                                ታዬ ከበደ

ህገ ወጥ ስደት የግለሰቦችንና የሀገርን ክብር እንደሚጋፋ ጥቅል ግንዛቤ በማስጨበጥ፤ በአገራችን የውጭ አገር የስራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 በአዲስ መልክ በመውጣቱ ዜጎች እንዳይንገላቱና በህጋዊ መንገድ እንዲሄዱ የሚያደርግ ነው። አዋጁ ህጋዊነትን የሚደግፍና የሚያበረታታ እንዲሁም የህገ ወጥ ስደትን በር የሚዘጋ መሆኑም ይታወቃል። ከአዋጁ ውጭ በህገ ወጥ መንገድ መንቀሳቀስ አደጋው የከፋ መሆኑ አያጠያይቅም።

የትኛውም አካል ቢሆን ህገ-ወጥ ስደት ህይወትን የሚያሳጣ የተሳሳተ መንገድ መሆኑን ለመገንዘብ በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ዕውቀት ሊኖረው የግድ ነው። የዚህ ፅሑፍ አነሳሽ ምክንያትም ይኸው ነው—ህገ ወጥ ስደትን ከዓለም አቀፍ ህግጋትና ከሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣመር ግንዛቤ በመፍጠር በመንስኤዎቹ ላይ የተባበሩ ክንዶች ይረባረቡባቸው ዘንድ ድጋፍ ማድረግ።

ከዓለም አቀፍ ብያኔ ስንነሳ፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እንደ አውሮፕያኑ አቆጣጠር በ2000 ዓ.ም ያወጣውና “የፓርሌሞ ስምምነት” እየተባለ የሚጠቀሰው ሰነድ ላይ በግልፅ እንደተበየነው፤ ሰዎችን ለብዝበዛ ዓላማ በኃይል፣ በዛቻ፣ በተንኮል፣ በማታለል፣ በመጥለፍ ወይም በተበዳይ ላይ ኃላፊነት ላለው ሰው ገንዘብ ወይም ሌላ ጥቅም በመስጠት መመልመል፣ ማጓጓዝ፣ ማስተላለፍ፣ መደበቅ ወይም መቀበል ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መሆኑን ያስረዳል።

የሀገራችን የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ህግም ሰዎችን በህገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወርን በወንጀል ተግባር ይፈርጀዋል። ይኸውም ሰዎችን በኃይል ወይም በማታለል መመልመል፣ በሀገር ውስጥ ወይም ወደ ሌላ ሀገር ህገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወር እና አዘዋዋሪዎች ተበዳዮችን የገንዘብ ጥቅም ማግኛ ማድረጋቸው ወይም ለብዝበዛ የተጠቀሙባቸው እንደሆነ በወንጀል ድርጊት እንደሚያስጠይቅ እንደሆነ ትርጓሜ ሰጥቷል።

እርግጥ የዜጎች ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ህገ-መንግስታዊ ዋስትና ያገኘና በተግባር እየተከናወነ ያለ ጉዳይ ነው። እናም እዚህ ላይ ዜጎች ለምን ከቦታ ቦታ ይዘዋወራሉ እያልኩ አለመሆኑ ሊታወቅልኝ ይገባል። ይሁንና ሰዎች በሀገር ውስጥ ወይም ወደ ውጭ ሀገር ከቦታ ወደ ቦታ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ወይም ስደት የተሻለ ስራ ፍለጋና ህይወት ወይም ልክ ወንድም እንደሆነው የኤርትራ ህዝብ ከጭቆና ለመሸሽ አሊያም የመኖሪያ ቦታን ለመቀየር ሊሆን ይችላል።

ዳሩ ግን የእንቅስቃሴው ዓላማ በሰዎች ለመነገድ ሲባል የሚከናወን ከሆነ ተግባሩ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የሚፈረጅ መሆኑ ግንዛቤ ውስጥ መግባት ይኖርበታል። እናም በዚህ ፅሑፍ ላይ ለመጥቀስ እየመከርኩት ያለሁት በመግቢያዬ ላይ ያነሳሁትን ዓይነት የዜጎቻችንን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው በህገ-ወጥ ደላላዎች አማካኝነት ቤተሰብንና ዘመድ አዝማድን ብሎም ዜጎችን እያስለቀሰ ስላለው ስለዚሁ የዝውውር ዓይነት መሆኑ ልብ ሊባልኝ ይገባል።

መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከሁለት ዓመታት በፊት ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ባደረገው ጥናት፤ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል 76 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት የህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባዎች መሆናቸውን አረጋግጧል። ከእነዚህ ውስጥ ወደ ተለያዩ የሰሜን አፍሪካ እንዲሁም የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ለስራና ለሌሎች ምክንያቶች ከተጓዙት የሀገራችን ዜጎች ውስጥ፤ 7 ነጥብ 5 በመቶ የሚሆኑት ከ13 እስከ 17 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል፤ ከእነዚህ ውስጥ 87 ነጥብ 1 በመቶ የሚሆኑት የህገ-ወጥ ዝውውር ሰለባዎች መሆናቸውም ጭምር ። በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የሀገራችን ኤምባሲ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ በዚያች ሀገር ውስጥ እስከ 50 ሺህ የሚደርሱ ዜጎቻችን ይገኛሉ። ከእነዚህ ውስጥ እስከ 95 በመቶ የሚደርሱት ወደዚያች ሀገር የሚያቀኑት በህገ-ወጥ ደላሎች አማካኝነት ነው።

እዚህ ላይ ‘ለመሆኑ እነዚህ ህገ-ወጥ ደላሎች እነማን ናቸው?’ የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል። እርግጥ የእነዚህ ህገ-ወጥ ደላሎች ግንኙነት እንደ ሰንሰለት በተያያዘ ሰንሰለት የተቆራኘ ነው። ይሁንና በዚህ አነስተኛ ፅሑፍ ላይ ከህገ-ወጥ ደላሎቹ ማንነት፣ አሰራራቸውና በዝውውሩ ሂደት ከሚኖራቸው ሚና አኳያ አዘዋዋሪዎቹን የአካባቢ፣ ድንበር አሻጋሪ፣ ጉዞ አቀላጣፊ፣ ከስደት ተመላሾችና ቤተሰቦቻቸው እንዲሁም በመዳረሻ ሀገራት የሚገኙ ደላሎች በማለት ልንከፍላቸው እንችላለን።

የአካባቢ ደላሎች በመገኙባቸው ቦታዎች የተሳሳተ መረጃ በማሰራጨትና በሌሎች ዘዴዎች ለህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር አመቺ ሁኔታ የመፍጠር እንዲሁም ተጋላጭ ግለሰቦችን የመለየት ስራን ከሌሎች ጋር በመሆን ያከናውናሉ። ድንበር አሻጋሪዎቹም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ በኮንትሮባንድ ነጋዴነት የሚፈረጁ ናቸው። እነዚህኛዎቹ አዘዋዋሪዎች ሰዎችን በቡድን ከአካባቢ ደላሎች ተቀብለው ለሌሎች ተመሳሳይ አዘዋዋሪዎች የማስተላለፍ ስራዎችን ይተገብራሉ።

ጉዞ አቀላጣፊዎቹም ቢሆኑ መቀመጫቸውን ትላልቅ ከተማዎች ላይ በማድረግ ወደ መዳረሻ ቦታዎቹ የሚደረገውን ጉዞና የቅጥር ሁኔታዎችን የሚያመቻቹ ሲሆን፣ ከስደት ተመላሾችና ቤተሰቦቻቸው ደግሞ ዘመድና ጎረቤቶች እናግዛለን በማለት እነርሱ ወደ ነበሩበት ሀገር ሄደው እንዲቀጠሩ በግለሰብ ደረጃ ሁኔታዎችን በማመቻቸት በመደበኛነት የሚንቀሳቀሱ ናቸው።

የእነዚህ ከስደት ተመላሽ ዜጎች እንቅስቃሴ በቤተሰባቸውም ይደገፋል። ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸው ውጪ ሀገር ሄደው የሚያመጡት ገንዘብ በምን ሁኔታ የተገኘ መሆኑን ስለማይገነዘቡ ከስደት የተመለሱት ልጆቻቸው ያስገኙላቸውን “ጠቀሜታዎች” በመዘርዘር የህገ-ወጥ ስደቱ ሂደት ተካፋይ ይሆናሉ። በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በደላልነት ተሰልፈው የዜጎቻቸውን ህይወት ለአደጋ አሳልፈው ይሰጣሉ። በመጨረሻም በእነዚህ መንገዶች ከሀገራቸው በህገ-ወጥ ሁኔታ በመውጣት ራሳቸውን ያገለጡት ዜጎች በመዳረሻ ሀገሮች ውስጥ የሚገኙ ደላሎች እጅ ላይ ይወድቃሉ። እነዚህ ህገ-ወጥ ደላሎችም ቀደም ሲል በጠቀስኳቸው የተለያዩ ደላሎች አማካኝነት የቀረቡላቸውን ግለሰቦች፤ በማታለል፣ በማስገደድ አሊያም በማስፈራራት በቀጥታ ለብዝበዛ እንዲጋለጡ ያደርጓቸዋል። በዚህ መንገድ ወደ ሌሎች ሀገራት ውስጥ የሚገቡ ዜጎች በመንገድ ላይ ህይወታቸው ካላለለፈና ወደ መዳረሻ ሀገሮች በሰላም ከገቡ ዕጣ ፈንታቸው ብዝበዛ ወይም ለህልፈተ-ህይወት ከሚዳርግ አደገኛ ሁኔታ ጋር መላተም ነው።

እንግዲህ በዚህ ሰንሰለታማ ህገ-ወጥ ዝውውር ውስጥ አንድ ግለሰብ ምን ያህል ገንዘብ ሊያወጣ እንደሚችል ማንኛውም አንባቢ የሚገነዘበው ይመስለኛል። የገንዘቡ ምንጭ ቤተሰብ ወይም ሀብትና ንብረት በመሸጥ አሊያም በብድር ከሚገኝ ገቢ ሊሆን ይችላል። የህገ-ወጥ ተዟዟሪዎቹ ሁኔታ ልክ በመግቢያዬ ላይ እንደጠቀስኳቸው 19 ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ በአሳዛኝ ሁኔታ ፍፃሜ የሚደመደም በመሆኑ፣ የወጣው በርካታ ገንዘብ ሀገር ውስጥ ቢሰራበት የሚያመጣውን ጥቅም ሳያስገኝ ውሃ በልቶት ይቀራል። ከሁሉም በላይ ደግሞ በህገ-ወጥ መንገድ ገንዘቡን የከፈሉት ወጣቶች በገዛ ገንዘባቸው ህይወታቸውን አጥተው ህልፈታቸውም ለቤተሰባቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና ሃዘኑን ለሚሰሙት ዜጎች የእግር እሳት ይሆናል።     

ያም ሆነ ይህ ግን በእነዚህ የትስስር ሰንሰለቶች ውስጥ ተጠያቂዎቹ ቤተሰብ፣ ደላሎችና ሌሎች ወገኖች ብቻ ሊሆኑ አይችሉም። አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው የመንግስት ስራ የሚከውኑ ግለሰቦችም በሂደቱ ውስጥ ሊኖሩበት ይችላሉ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በተለያዩ ወቅቶች እንዳጫወቱኝ ከሆነ፤ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር የድለላ ስራ ውስጥ ለወገኖቻቸው ደንታ የሌላቸው አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ይሳተፋሉ።

በዚህም ምክንያት ዝውውሩን ለመግታት በሚደረጉ ስራዎች ላይ አሜኬላ እሾህ ሆነው ይቆማሉ። ታዲያ ይህ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች የነካካን አስከፊ ሁኔታ ለመከላከል ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት። የስደት በር እንዲዘጋ ሚናን መወጣት አገርን መጥቀም መሆኑን ሁሉም ዜጋ ማወቅ አለበት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy