NEWS

ህብረቱ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሶስት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት የ60 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገ

By Admin

July 07, 2017

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ ለሰብአዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 60 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ይፋ አደረገ።

ህብረቱ ዛሬ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ፥ ተጨማሪ ድጋፉ የአውሮፓ ህብረት በዚህ አመት በምስራቅ አፍሪካ ለሰብአዊ ድጋፍ ያደረገውን የገንዘብ እርዳታ 260 ሺህ ሚሊየን ዩሮ እንዲደርስ አድርጓል።

አዲሱ የህብረቱ ድጋፍ በድርቅ ለተጠቁ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ እርዳታ እያቀረቡ ለሚገኙ አጋር ተቋማት ይሰጣል ተብሏል።

በውሃ አቅርቦት፣ የእንሰሳት ህይወትን ለመጠበቅ እና ወረርሽኞችን ለመቆጣጠር ለሚከናወኑ ስራዎችም ድጋፉ ጥቅም ላይ እንደሚውል ህብረቱ አስታውቋል።

ከአዲሱ የህብረቱ ድጋፍ ኢትዮጵያ 15 ሚሊየን ዩሮ የምታገኝ ሲሆን፥ ሶማሊያ 40 ሚሊየን ዩሮ፣ ኬንያ ደግሞ 5 ሚሊየን ዩሮ ይደርሳቸዋል።