Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

መንግስት የድርቁን ችግር ይመክታል!

0 239

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

መንግስት የድርቁን ችግር ይመክታል!

                                                         ደስታ ኃይሉ

መንግስት በአገራችን የተፈጠረው ድርቅ ወደ ረሃብነት እንዳይሸጋገር የሚያደርግ አቅም ገንብቷል። በአሁኑ ወቅትም በመጠባበቂያ በመጋዘኖች በቂ ክምችት ስላለው የድርቅ ተጠቂ ዜጎች የእርዳታ እጥረት አያጋጥማቸውም። ቀደም ሲል መንግስት በጥናት ላይ ተመርኩዞ በቂ ዝግጅት በማድረጉ የሚፈጠር ችግር እንደማይኖር ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ የተለመደውን አመኔታ ማሳደር አለበት። ምክንያቱም መንግስት ሁሌም ቢሆን የገባውን ቃል የማያጥፍ ስለሆነ ነው።

እንደሚታወቀው በአሁኑ ወቅት ለድርቅ አደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ለመታደግ መንግስት ማናቸውንም ተግባራት ያከናውናል፤ በማከናወን ላይም ይገኛል። መንግስት የችግሩን ስፋትና ጥልቀት አስቀድሞ በመገንዘብ የተፈጠረውን ሁኔታ ለመቋቋም በዜጎችና በኢኮኖሚው  ላይ ሊደርስ የሚችለውን  ጉዳት ለማስቀረት የሚያስችል አቅጣጫ ቀይሶ ተግባራዊ እያደረገ ነው።

እርግጥ በተፈጥሮ የአየር መዛባት ምክንያት በሀገራችን የድርቅ አደጋ ሲከሰት አዲስ ነገር አይደለም። ይህ ደግሞ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰት ጉዳይ በመሆኑ ምንም ማድረግ አይቻልም። ሆኖም ይህ በየጊዜው ሀገራችንን የሚጎበኛት የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብነት እንዳይቀየር መንግስት ብርቱ ጥረት አድርጓል።

እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት የአየር ንብረት መዛባትና ድርቅ  ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን  የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆመቆየቱ አይዘነጋም።

የኤልኒኖ አደጋ በተከሰተበት ወቅትም አደጋውን በመቀልበስ የልማት አጋር ሀገራትን ድጋፍ እምብዛም ሳያገኝ ችግሩ ወደ ረሃብነት ሳይቀየር መቋቋሙ ይህን ጥረቱን አጉልቶ የሚያሳይ መሆኑን ከማንም የተሰወረ ጉዳይ አይመስለኝም።

መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረግ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ  በሆነ አኳሃን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረጉ ለዜጎቹ ያለውን የኃላፊነትና የተጠያቂነት መንፈስ ስሜትንና ቁርጠኝነትን የሚያሳይ ነው።

ባለፉት 26 ዓመታት መንግስት የአርሶና የአርብቶ አደሩ ኑሮ እንዲሻሻል ተገቢውን ትኩረት ሰጥቷል። በዚህም አርሶ አደሩ ከራሱ ተርፎ ለገበያ በማምረት ተጠቃሚ የሚሆንበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ፣ ሀገሪቱም ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ ጎዳና እንዲፈጠር አድርጓል። ለዚህ ስኬት በመንግስት በኩል የተወሰዱት እርምጃዎች በቂ ማሳያዎች ናቸው ማለት ይቻላል።

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ለእርሻ የሚውል ሰፊ መሬት አላት። ሆኖም በተለያዩ ምክንያቶች በአርሶ አደሩ እጅ እንዳለ የሚታሰበው መሬት አነስተኛ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ካለችውም መሬት ቢሆን የሚያገኘው ምርት ዝቅተኛ ነው። አመራረቱም እጅግ ኋላ ቀር ሆኖ ቆይቷል።

ይህን ዕውነታ የተገነዘበው መንግስት ዘርፈ ብዙ የማሻሻል ጥረቶች አድርጓል። በውጤቱም አነስተኛ ይዞታ ባላቸው አነስተኛ የአርሶ አደሮችን ማሳ ላይ ለውጥ ማምጣት አይቻልም የሚለውን አስተሳሰብ ሰብሯል። አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ትኩረት ከመስጠት ይልቅ ለሰፋፊ እርሻዎች ትኩረት መስጠትና ለውጥ ማምጣትን የሚሰብኩ ወገኖችን አፍ ማስያዝ የቻለ ትክክለኛ መስመርን በመከተል ውጤት ማምጣት ችሏል።

በአርብቶ አደሩም አካባቢ ተመሳሳይ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በመቅረፅና ቀደ ተግባር እንዲገባ በማድረግ ድርቅ ሊፈጥር የሚችለውን አደጋ በአያሌው መቀነስ ተችሏል። ከእነዚህ መንግስታዊ ጥረቶች ውስጥ የአርብቶ አደር የልማት ፓኬጆችን በመቅረፅ፤ አርብቶ አደሩ ከልማዳዊ የአኗኗር ባህል ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ህይወት እንዲቀየር፣ ከአርብቶ አደሩ ጋር በመነጋገር ድርቅን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመስኖ ልማት ስራዎችን በማስፋፋት ወደ ከፊል አርሶ አደርነት እንዲሸጋገር ብሎም ምርጥ ዝርያዎችን አግኝቶ ተጠቃሚነቱን እንዲያሳድግ፣ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ውሃዎችን በአግባቡ የማሰባሰብ ስራዎችን እንዲያጠናክር፣ የመሰረተ ልማትና የሌሎች የልማት ዘርፎች ተቃሚ ይሆን ዘንድ በፍፁም ፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የሰፈራ ፕሮግራምን እንዲቀበል፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱ እንዲጠናከርና በዚህም ብሔራዊ መግባባት እንዲፈጠር የማድረግ ስራዎችን ማከናወኑና በማከናወን ላይ መሆኑ ጥቂት ተጠቃሽ ምሳሌዎች ናቸው።

እንደ እውነቱ ከሆነ ባለፉት ዓመታት የመንግስት ትኩረት ምንም ዓይነት  የአየር ንብረት  መዛባትና ድርቅ ቢያጋጥምም፤ ህዝባችን የማይራብበት ሁኔታን በመፍጠር ላይ ሲረባረብ ቆይቷል።

በመሆኑም መንግስት ከአጭር ጊዜ አኳያ በተፈጥሮ ችግር ምክንያት የሚከሰተውን ድርቅ ለመከላከል በፍጥነት በመድረስና ዕርዳታ ማድረጉ እንዲሁም ድጋፉ ልማታዊ በሆነ አኳኋን ጥቅም ላይ እንዲውል የክትትል አሰራርን መከተሉ አሁን ላለበት አቅም ያበቁት ይመስለኛል።

እንደሚታወቀው በልማታዊውና ዴሞክራሲያዊው መንግስት የምትመራው ሀገራችን ላለፉት 15 ተከታታይ ዓመታት ባስመዘገበችው ዕድገት ችግሮችን እየተቋቋመች መጥታለች። በእነዚህ ዓመታቶች ውስጥ መንግስት ልማታዊ የግል ኢንቨስትመንቶችን በማበረታታትና የኪራይ ሰብሳቢነት አማራጮችን በማጥናት ለማስወገድ በመሞከርና በግሉ ዘርፍ የማይሰሩ የልማት ክንዋኔዎችን በመስራት፣ ያሉትን ውስን ሃብቶች መሠረታዊ ችግሮችን በሚፈቱበት የልማት ስራዎች ላይ በማዋል፣ የልማት ኃይሎችን በማቀናጀትና በመምራት፣ የህዝብ ተሳትፎን በማጎልበት እና የግል ኢንቨስትመንት በማበረታታት ፈጣን ቀጣይነትና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ ዕድገትና ማህበራዊ ልማት ለማምጣት ተችሏል።

ይህ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ልማት በአሁኑ ወቅትም ገቢራዊ እየሆነ ላለው ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መንደርደሪያ ነው። ዕድገቱም የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየፈታ ህዳሴያችንን አረጋጋጭ መሆኑ አይቀሬ ነው።

በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን የድርቅ አደጋ ለመከላከል ከለጋሽ ሀገራት እገዛና ድጋፍ ከተገኘ እሰየው ነው። ካልተገኘ አሊያም እገዛው የሚፈለገውን ያህል ካልሆነ ደግሞ መንግስት ህዝባዊ ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ እንደተለመደው ችግሩን ከህዝቡ ጋር በመሆን ይወጣዋል። ይህን ለማድረግም ቀደም ሲል የጠቀስኩት የመንግስት አቅም ምላሽ ይሰጣል፤ እየሰጠም ነው።

መንግስት የተከተለው ልማታዊ መስመር ድርቅን በተገቢው ሁኔታ እየተቋቋመ ነው። በአሁኑ ወቅትም በዝናብ እጥረት ሳቢያ በደቡብና በምስራቁ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው የድርቅ አደጋን ለመከላከል፣ ያለፉትን ተሞክሮዎች በመቀመርና ሊከሰቱ የሚችሉ ተግዳሮቶችን ከወዲሁ በመለየት ህዝባዊ ኃላፊነቱን የመወጣት ተግባሩን መቀጠሉ አይቀሬ ነው። እያንዳንዱ ዜጋም ዛሬም ቢሆን መንግስት ይህን በተፈጥሮ የአየር ለውጥ ምክንያት የተከሰተውን ድርቅ እንደሚቋቋመው ሊገነዘብ ይገባል። መንግስት ባለፉት 15 ዓመታት የፈጠረውን አቅም ተመርኩዞ የሚፈጠሩ ማናቸውንም ችግሮች መመከቱ አይቀርም። ትናንት ሲያደርገው እንደመጣው ሁሉ ዛሬም ይሁን ነገ ችግሮችን ይመክታል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy