Artcles

ስራ ፈጠራን የሚያበረታታ ፖሊሲ

By Admin

July 21, 2017

ስራ ፈጠራን የሚያበረታታ ፖሊሲ

ዳዊት ምትኩ

በቅርቡ የአገራችን የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ምሩቃን አሰመርቀዋል። ኢትዮጵያ በሁሉም መስኮች የተማረ የሰው ኃይልን ማፍራት የምትችል አገር ናት። አገራችን የምትከተለው የትምህርት ፖሊሲ ጥራት ላይ በማተኮር 70 በመቶ በተፈጥሮ ሳይንስ መስኮች እንዲሁም 30 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ መስኮች ላይ ያተኮረ ነው። ፖሊሲው በራሱ ስራ ፈጠራን የሚያበረታታ ነው። በመሆኑም ምሩቃኑ ስራ ጠባቂ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸው ነው።

እንደሚታወቀው በትምህርቱ ዘርፍ በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን የተገኘውን ውጤት የማጠናከር ስራዎች እየተከናወኑ ነው። በሁለተኛው የልማት ዕቅድ የትምህርቱ ዘርፍ የህፃናትንና የሴቶችን የትምህርት ተሳትፎ የሚገድቡ ችግሮች ለመቅረፍ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው። ከሀገራችን የትምህርት ግቦች ጋር የሚጣጣሙ የድህረ 2015 ዓለም አቀፋዊና አህጉራዊ የልማት ግቦች የዕቅዱ አካል ተደርገው ተፈፃሚ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ነው።

ትምህርትን በተመለከተ ቁልፉ ጉዳይ ጥራት ቢሆንም፤ ቀጥሎ ትኩረት የሚያሻቸው ከሽፋን ጋር የተያያዙ ጉዳዮች በመኖራቸው ይህንኑ ጉዳይ ለማሻሻል እየተሰራ ነው። የመጀመሪያው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ሽፋን የማስፋፋት ጉዳይ ነው። በያዝነው የዕቅድ ዘመን ይህን ሽፋን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘም ለቅድመ መደበኛና የጐልማሶች ትምህርት ትኩረት በመስጠት ስራው እየተሳለጠ ነው። እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የመምህራንና የትምህርት ቤቶችን ጥራትና ቁጥር ለማሳደግ የሚወሰዱ ርምጃዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል።

እርግጥ እቅዱ ከተጀመረ ገና አንድ ዓመት ከመንፈቅን እልፍ ያለ ቢሆንም መንግስት በየደረጃው የትምህርት ጥራትን የማሻሻል ፕሮግራም ዘርግቶ እየሰራ ነው። ለኢኮኖሚ እድገቱና ለማህበራዊ ልማቱ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁ ዜጋ ማፍራት ቁልፍ ተግባር እንደመሆኑ መጠን፤ መንግሥት የከፍተኛ ትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ስራ በማጠናከር ተገቢውን ተግባር እየተወጣ ነው። ለዚህም የግል ባለሃብቶች በትምህርት ዘርፍ በሰፊው እንዲሳተፉ ማበረታታት፣ ድጋፍ መስጠትና ስታንዳርዱን የጠበቀ ለመሆኑ ተገቢው ክትትልን የማድረግ ስራዎችን እያከናወነ ነው። በመንግስት የትምህርት ተቋማትም እንዲሁ።

ያም ሆኖ ግን በመንግስት ጥረት ብቻ የትምህርት ጥራት ሊጠበቅ አይችልም። በመሆኑም ህብረተሰቡ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በመደረገው ጥረት ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆን ይኖርበታል።

በእስካሁኑ ሂደት ህብረተሰቡ የመማር ማስተማሩ አካል እንዲሆን በማድረግ ከጥራት አኳያ የሚነሱትን ችግሮች ለመፍታት በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ድርሻ እንዲያበረክት እየተደረገ ነው። ይህ ሁኔታም በቀሪዎቹ የዕቅዱ ዓመታት ተጠናክሮ ከቀጠለ በትምህርት ጥራት ላይ ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት የሚቻል ይመስለኛል። አበረታች ውጤትም እየተገኘ ነው።

እንደሚታወቀው የከፍተኛ ትምህርትን ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ቀደም ሲል ከነበሩት በተጨማሪ አስራ አንድ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎችን በመገንባት በቅድመ-ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም 600 ሺህ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም እንዲኖራቸው ይደረጋል። የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ብዛትም ወደ 63ሺ ከፍ እንዲል ግብ ተጥሎ ስራው በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እየተከናወነ ነው።

ይህም የሴት ተማሪዎች ተሳትፎን በቅድመ ምረቃ ፕሮግራም በ2007 ዓ.ም ከነበረበት 32 በመቶ በ2012 ዓ.ም ወደ 45 በመቶ ከፍ እንዲል፣ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በ2007 ዓ.ም ከነበረበት 22 በመቶ በ2012 ዓ.ም ወደ 35 በመቶ እንዲያድግ እንዲሁም በሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በ2007 ዓ.ም ከነበረበት 11 በመቶ በ2012 ዓ.ም ወደ 20 በመቶ እንዲያሳድግ ታስቦ መሰረታዊ ስራዎች ገቢራዊ እየተደረጉ ነው።

በሁለተኛው የልማት ዕቅድ የጤና እና የትምህርት ግብ በዚህ መልኩ እየተከናወኑ ናቸው። ሆኖም በአንድ ዓመት ከስድስት ወር አፈፃፀም ብቻ ከወዲሁ ሁኔታውን ለመገምገም ያስቸግራል። ያም ሆኖ ግን በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑት ስራዎች መጪውን ጊዜ የሚያመላክቱ ናቸው። ያም ሆኖ ግን በእነዚህ የማህበራዊ ዘርፎች በ“ዕትዕ” የተቀመጡት ግቦች በቀጣዩቹ የዕቅዱ ጊዜያት ውጤታማ እንደሚሆኑ የሚያጠያይቅ አይመስለኝም።

የትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ልማት ዕቅድ ዝግጅት መሰረት ያደረገው ሃገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሃገራት ተርታ ለማሰለፍ የተያዘውን ራዕይ ስኬታማ ለማድረግ ለኢንዱስትሪው በተለይም በማደግ ላይ ያለውን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት ነው።

ከዚህ በመነሳት የአጠቃላይ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርትን በተመጋጋቢነት በማስፋፋት በዕቅድ ዘመኑ ጥራቱና ፍትሃዊነቱ የጠበቀ ትምህርትና ስልጠና ለማረጋገጥ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል።

ከሃገሪቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስኬታማ ከማድረግ አኳያ ጠቀሜታ ያላቸውን አዳዲስ የስልጠና መርሃ ግብሮችን ቀርዖ ተግባራዊ ከማድረግ ጎን ለጎን የነበሩትን የትምህርት ዘርፎች ጥራት ለማረጋገጥ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል። ከዚህም ባሻገር በአንዳንድ የስልጠና መስኮች የሚሰለጥነውን የሰው ኃይል ቁጥር ከሃገሪቱ ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እርምጃዎችን ለመውሰድ የተቻለበት ሁኔታ ነው ያለው።

ከከፍተኛ ትምህርት ጋር በተያያዘ በሁለቱ ዓመታት የተከናወነው የስርዓተ ትምህርቶችን ተግባራዊነት ማረጋገጥ ነው። ለዚህም የተግባር ልምምድ  ቁልፍ  መሳሪያ ሆኖ ይገኛል። ምክንያቱም ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ ደረጃ በክፍል ውስጥ የወሰዱትን ትምህርት በተግባር ማየታቸው በአንድ በኩል ስርዓተ ትምህርቱ ትክክለኛና ተግባር ላይ ሊውል የሚችል መሆኑን ለመፈተሽ የሚያስችል ሲሆን፤ በሌላም ጎኑ ተማሪዎች በንድፈ ሃሳብ የቀሰሙትን እውቀት በተግባር እንዲያዳብሩ የሚረዳቸው ይሆናል።

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዘመናት በአስከፊ ድህነትና ኋላ ቀርነት ውስጥ ኖሯል። ይህ ደግሞ የውጭ ኋይሎችን እርዳታና ድጋፍ እየጠበቀ ከመኖር የተሻለ አማራጭ እንዳይኖረው ያስገደደው እንደነበር ለማንም ግልፅ ነው።

ታዲያ እዚህ ላይ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ  ባለፉት ጊዜያት ህዝቡ ከውጭው አለም እንዲቸረው ይጠብቅ የነበረው የእህል አልያም የገንዘብ ድጋፍና ዕርዳታን ብቻ አለመሆኑን ነው። በአገራችን በተለያዩ ደረጃዎች በሚካሄዱ የልማት ስራዎች ውስጥ የእውቀት ድጋፎችን የሚሻም ነው። እናም ይህን ሁኔታ ለመቅረፍ የከፍተኛ ትምህርት በስፋት መዳረስ ይኖርበታል። ሰሞኑን የተመረቁት ወደ 50 ሺህ የሚጠጉ ተመራቂዎች ሀገራችን በምትከተለው የስራ ፈጠራ መርህ የሰለጠኑ በመሆናቸው የአገሪቱ ፍላጎት መገለጫ ናቸው ማለት ይቻላል።