Artcles

በተሟላ ግንዛቤ የሁከት አጋጣሚን አምክኑ

By Admin

July 31, 2017

በተሟላ ግንዛቤ የሁከት አጋጣሚን አምክኑ

ኢብሳ ነመራ

በዚህ ዓመት የተካሄደው የነጋዴዎች የቀን ገቢ ግምት ውጤት ይፋ ከተደረገ ከሃያ ቀናት በላይ ተቆጥሯል። የቀን ገቢ ግምት ይፋ መደረጉን ተከትሎ ግምቱ በተካሄደባቸው ክልሎች ከተሞች ቅሬታዎች ተሰምተዋል። በተለይ በአዲስ አበባና በኦሮሚያ ክልሎች ደግሞ የተገመተብን የቀን ገቢ የተጋነነ ነው በሚል መነሻ የአድማነት ባህሪ ያለው የቅሬታ አቀራረብ የታየበት ሁኔታ ነበር።

የነጋዴዎች የቀን ገቢ ግምት መገለጹን ተከትሎ የሃገር ውስጥ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽንን ጨምሮ ሁሉም የህዝብና የግል የመገናኛ ብዙሃን ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው ሰፊ የዘገባ ሽፋን እንዲያገኝ አድርገዋል። በተለይ የህዝብ የመገናኛ ብዙሃን ነጋዴዎች ያነሱትን ቅሬታ በአዲስ አበባ ወረዳና ክፍለከተሞች ድረስ ወርደው ለህዝብ ለማቅረብ ያሳዩት እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው። መገናኛ ብዙሃኑ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችን የስብሰባ ንግግርና መግለጫ እየጠቀሱ ከመዘገብ ወጥተው ወደህዝብ መውረዳቸው፣ በሌሎቹም ጉዳዮች ላይ ሊታይ የሚገባው የሚበረታታ ነው። መገናኛ ብዙሃኑ ከተጽእኖ ነጻ ሆነው መስራት እንደሚችሉም አሳይቷል።

ከቀን ገቢ ትመናው ጋር ተያይዞ የቀረበው ቅሬታ ዋና መንስኤ በቀን ገቢ ትመናውና በግብር ውሳኔ መሃከል ያለውን ልዩነትና ዝምድና በሚገባ መገንዘብ አለመቻል ነው። ይሁን እንጂ የህዝብ መገናኛ ብዙሃኑ ይህን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ከመጣር ይልቅ፣ በነጋዴውም ይሁን ጉዳዩን በሚከታተለው የተቀረው ህዝበ ዘንድ መደነጋገርን ፈጥረዋል።

በተለይ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (EBC) በዋና የዜና ስርጭቱና በቢዝነስ ዘገባው በጉዳዩ ላይ ያቀረባቸው ዘገባዎች፣ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ እውነታዎችን የሚያሳዩ አልነበሩም። ቅሬታ አለን የሚሉ ነጋዴዎችን ሲያነጋግሩ፣ ተጋነነብን ስለሚሉት የቀን ገቢ ግምት እንጂ፣ በቀን ገቢ ግምቱ ምን ያህል ግብር እንዲከፍሉ እንደተጠየቁ ሲያነሱ አልተደመጡም።

አብዛኛው ነጋዴ የቀን ገቢ ግምቱን መነሻ በማደረግ በድንጋጤ ወደቅሬታና ተቃውሞ ያመራው፣ ግምቱን እንደግብር ክፍያ በመቁጠር ነው። ኢ ቢ ሲ ያነጋገራቸው ሁሉም ነጋዴዎች የተወሰነብኝ የቀን ገቢ ከአቅሜ በላይ ነው የሚሉ ናቸው። ከተገመተብህ የቀን ገቢ በመነሳት ምን ያህል ዓመታዊ ግብር ተጠየክ? የሚለው ጉዳይ ተትቷል። በመሰረቱ ከእለታዊ የቀን ገቢ ግምት በመነሳት የተወሰነው ዓመታዊ አጠቃላይ ገቢ ተከፋይ ግብር አይደለም። ቅሬታ ያቀረቡት የደረጃ ‘ሐ’ ቁርጥ ግብር ከፋዮች የአጠቃላይ ዓመታዊ ገቢያቸው ወይም ሽያጫቸው 90 በመቶ ገደማ በወጪነት ይያዝላቸዋል።

ግብር እንዲከፍሉ የሚጠየቁት ከወጪ ቀሪ በሆነችው 10 በመቶ ገደማ ገቢ ላይ ብቻ ነው። ከዚህ 10 በመቶ ውስጥ የተወሰነ እጅ ብቻ ነው ግብር የሚከፍሉት። ይህ ደግሞ የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ሊጠየቁ የሚችሉት ዓመታዊ ግብር ከ5 ሺህ ብር ሊበልጥ እንደማይችል ያሳያል። ነጋዴው መገንዘብ ያቃተው ይህን ነው። የኢ ቢ ሲ ጋዜጠኞችም ይህን የግንዛቤ ክፍተት መሙላት አቅቷቸው ስለእአለታዊ ገቢ ግምት መጋነን ሲያሰሙን ነው የሰነበቱት። እንደ እኔ አተያይ ኢ ቢ ሲም በጉዳዩ ላይ ተደናግሮ ሲያደናግር ነበር። በቀጣይነት ይህን ማስተካካል አለበት።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሌላ ያጋጠመኝ የግንዛቤ ችግር ግብር በሚከፈልበት ዓመታዊ ገቢና በሚከፈል ግብር መጠን ላይ ያለ የግንዛቤ እጥረት ነው። ምን ያህል ግብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ለጠየቁ አንዳንድ ነጋዴዎች፣ የሚከፍሉትን ግብር መጠን ከማሳወቅ ይልቅ፣ ግብር የሚከፍሉበትን አጠቃላይ ከወጪ ቀሪ ገቢ የሚነገርበት ሁኔታ አለ። የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋይ ሆነው 15 ሺህ፣ 20 ሺህ ብር ግብር ተጠየኩ የሚሉት የዚህ አይነት መረጃ የተሰጣቸው ነጋዴዎች ናቸው።

በደረጃ ‘ሐ’ ይህን ያህል ግብር የሚከፍል ነጋዴ የለም። የመገናኛ ብዙሃኑ ይህን የግንዛቤ ክፍተት ማሳየት የሚችል ስራ አልሰሩም። እርግጥ የገቢዎች ባለስልጣን የስራ ሃላፊዎችም ይህን ጉዳይ ለአብዛኛው ህዝብ ተደራሽ በሆኑ መገናኛ ብዙሃን ግልጽ በሆነ አቀራረብና ቋንቋ ሲያቀረቡ አልተደመጡም። እናም ከዕለት ገቢ ግምት ጋር በተያያዘ ያጋጠመው ቅጡ የጠፋ እስከ አድማ የዘለቀ ቅሬታ ዋነኛ ምክንያት የዚህ አይነት መደነጋጋር የፈጠረው ነው።

ለምሳሌ የቀን ገቢዬ ከ50 ብር አይበልጥም ብሎ የሚከራከር ነጋዴ ሰምተናል፤ በኢ ቢ ሲ ዘገባ። ይህ ነጋዴ የቤት ኪራይ እየከፈለ ነው የሚሰራው። የሚሸጠውን እቃ ከጅምላ ሻጭ ገዝቶ ነው የሚያመጣው። ሌሎች በቀጥታ ከንግድ ስራው ጋር የተያያዙ ወጪዎችም ይኖርበታል። ልብ በሉ የቀን ገቢው 50 ብር የሆነ ነጋዴ እነዚህን ወጪዎች ቀንሶ የሚያገኘው የቀን ገቢ ከአስር ብር አይበልጥም። አሁንም ልብ በሉ ይህ ነጋዴ ቀኑ ሙሉ ሰርቶ የሚያገኘው ገቢ አስር ብር መሆኑን እየተናገረ ነው። ይህ አሁን ካለው ተጨባጭ የኢትዮጵያ የገቢና የኑሮ ሁኔታ ጋር ፍጹም የማይመሳሰል ነው። ተቀጣሪ ሰራተኞችን ሳይጨምር አንድ ዝቅተኛ የቀን ስራ ላይ የተሰማራ ኢትዮጵያዊ በቀን ቢያንስ 70 ብር እንደሚያገኝ ልብ በሉ።

ይህ ነጋዴ የቀን ገቢዬ 50 ብር ነው ሲል የተጣራ ትርፌ 50 ብር ነው እያለን ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ በቀን የተጠየቀው የግብር መጠን 50 ብር እንዲሆንለት እየጠየቀ ነው። ከነባራዊው ሁኔታ አኳያ ሲታይ ከዚህ ውጭ ሊሆን አይችልም። ነባራዊው ሁኔታ የሚነገረን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ንግድን የሙሉ ሰአት ዋና መተዳደሪያ ስራው ያደረገ ሰው  የቀን ገቢው ከ2 መቶ ብር እንደማያንስ ነው። ዝቅተኛ የሚባለው የጫማ ማጽዳት ስራ ላይ የተሰማሩ ሰዎች በቀን መቶ ብርና ከዚያ በላይ እንደሚያገኙ ልብ በሉ።

በአጠቃላይ የሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃኑ ይህን የግንዛቤ ክፍተት በመሙላት ረገድ ምንም አላደረጉም ማለት ይቻላል። የባለስልጣኑ ሰራተኞችም ግልጽ ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ክፍተት ታይቶባቸዋል። ያም ሆነ ይህ እያደረ በንትርክ መሃከል በርካታ ነጋዴዎች እውነታውን ተገንዝበዋል። ቅሬታ ካቀረቡ ነጋዴዎች መሃከል በርካቶች ቅሬታቸውን አንስተው የተጠየቁትን ዓመታዊ ግብር የከፈሉት በዚህ ምክንያት ነው።

በሚኒስትር ማዕረግ የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ከበደ ጫኔ በዚህ ጉዳይ ላይ በሰጡት ማብራሪያ፣ ባለስልጣኑ ለነጋዴዎች የገቢ ግምትና የሚከፍሉትን የቁርጥ ግብር በአንድ ላይ ባለማሳወቁና በቂ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ ባለማከናወኑ  ቅሬታ መፈጠሩን ገልፀዋል። ይህ ሁኔታ ነጋዴው ዓመታዊ ሽያጩ ሲነገረው የሚከፍለው የግብር መጠን አድርጎ መረዳቱንና ይህም አለመግባባት እንዲፈጠር በር መክፈቱን አቶ ከበደ ጫኔ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት በተካሄደው የቅሬታ መፍታት እንቅስቃሴ አብዛኛው የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች የሚጠየቁት የቁርጥ ግብር ብቻ መሆኑን በመረዳታቸው ይህ ከሆነማ እንከፍለዋለን እያሉ መመለሳቸውንም አስታውቀዋል።

በተለይ በአዲስ አበባ ተነስቶ የነበረውን የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ቅሬታና ቅሬታው የተስተናገደበትን ሁኔታ በተመለከተ ከባለስልጣኑ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሰሞኑን በሰጠው ማብበራሪያ፣ በከተማዋ ቅሬታ ካቀረቡ የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች መሃከል 99 ነጥብ 2 በመቶ የሚሆኑት ቅሬታዎች ተፈትቷል።

ከ59 ሺህ 275 የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች መካከል 24 በመቶዎቹ ወይም 14,226 ያህሉ ቅሬታ አቅርበው 99 ነጥብ 2 በመቶ ያህሉ መፈታቱን ነው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ያስታወቀው። በዚህም መሰረት እስካሁን 40 በመቶ የሚሆኑ የደረጃ ‘ሐ’ ግብር ከፋዮች ግብራቸውን ከፍለዋል። እርግጥ ቅሬታዎቹ ተፈትተዋል የሚለው፣ ሁሉም ነጋዴ በተሰጠው ምላሽ መርካቱን አያመለክትም። ከዚህ ይልቅ ዳግም የገቢ ምርመራ እስከማደረግ የዘለቀ ማጣራት ተደርጎ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች 99 በመቶ መድረሱን ነው የሚያመለክተው።

በመቀጠል የደረጃ ‘ለ’ እና ‘ሀ’ ማለትም የመካከለኛና የከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ቅሬታ መስማት ይጀመራል። በእነዚህ ነጋዴዎች ዙሪያም ተመሳሳይ የግንዛቤ ክፍተት መኖሩን የሚያመለክቱ ሁኔታዎች አሉ። የደረጃ ‘ለ’ እና ‘ሀ’ ግብር ከፋዮች የቅሬታ ይግባኝ መስማት ባይጀመርም፣ ሱቅ በመዝጋት በአድማ ቅሬታቸውን ከገለጹት መሃከል የእነዚህ ደረጃዎች ግብር ከፋይ ነጋዴዎች ይገኙበታል። በመሆኑም በእነዚህ ደረጃዎች ግብር ከፋዮች ዙሪያ የተሟላ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ከወዲሁ መከናወን አለበት። መገናኛ በዙሃን ጋዜጠኞቻቸው አስቀድመው ጉዳዩን እንዲረዱ በማድረግ መደናገሩን ከማባባስ ይልቅ ግንዛቤ በመፍጠር ሂደቱን የሚያግዙ ስራ እንዲያከናውኑ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚል እምነት አለኝ።

የደረጃ ‘ለ’ እና ‘ሀ’ ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ስለሚጠቀሙና የሂሳብ መዝገብ ስለሚይዙ ግመታው በዚህ መሰረት የቀረበውን ሂሳብ መሰረት ያደረገ ነው። በእነዚህ ደረጃዎች ዙሪያ አዲስ ግምት የተሰራው፣ የግብር ስወራና የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ማጭበርበር የተገኘባቸው መሆናቸውን ከባለስልጣኑ የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ይሄም ቢሆን ግን የወዥንብር ምንጭ ሆኖ ጉዳዩን ለሁከት መቀስቀሻ ለመጠቀም ለሚፈልጉ  የሃገሪቱ ጠላቶችና ተላላኪዎቻቻው የትርምስ አጋጣሚ እንዳይፈጥር ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

የእለታዊ ገቢ ግምቱን መነሻ በማድረግ ገና የሚከፈለው የግብር መጠን ሳይታወቅ ከአቅም በላይ ግብር እንድንከፍል ተጠየቅን በሚል በኦሮሚያና በአዲስ አበባ መደብሮችን በመዝጋት ህገወጥ አድማ የተካሄደው በግንዛቤ ክፍተትና ክፍተቱን ተጠቅመው በገቡ የትርምስ ልዑካን ነው።

በኦሮሚያ አምቦ፣ ወሊሶና አካባቢው፤ እንዲሁም አዲስ አበባ የተካሄደው መደብር የመዝጋት ህገወጥ አድማ ቅሬታ የሌላቸው ነጋዴዎችም ጭምር የተሳተፉበት ነበር። ይህ የሆነው በማስፈራራት አድማውን ሲቀሰቅሱ በነበሩ የኤርትራ መንግስት የሁከት ልዑካን ስራ መሆኑን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ልብ ይሏል። እናም የግንዛቤ ክፍተትን በመሙላት የሁከት አጋጣሚን አምክኑ።