አፍሪካ እና የወጣቶቿ ፍልሰት
ሰለሞን ሽፈራው
መዲናች አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረትን 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ከሰኔ 26 እስከ 27/2009 ዓ.ም ድረስ በነበሩት ሁለት ቀናት ውስጥ አስተናግዳለች፡፡ለህብረቱ 29ኛ ጉባኤ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የአህጉሪቷ መሪዎች በሁለት ቀናት ውሏቸው በርካታ የጋራ አጀንዳዎችን አንስተው እንደተወያዩም ነው መገናኛ ብዙኃን የዘገቡት፡፡ በተለይም ደግሞ የወቅቱ ዓለም አቀፋዊ አሳሳቢ ችግር ተደርጎ ስለሚወሰደው የአፍሪካውያን ወጣች ሕገ ወጥ ስደት ጉዳይ ጉባኤው ትኩረት ሰጥቶ እንደመከረበት ነው መረጃዎች ያመለከቱት፡፡
እንዲያውስ እኔም በሰሞነኛው የአፍሪካ ህብረት 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ቀዳሚ የመወያያ አጀንዳዎች ከነበሩት ርዕሰ ጉዳዮች መካከል አንዱ በሆነው የአህጉሪቷን ወጣቶች ከሕገ ወጥ ስደትና ከሚያስከትለው ፈርጀ ብዙ ጉዳት የመታደግ አስፈላጊነት ዙሪያ ተጨማሪ ሃሳብ መሰንዘር ተገቢ መስሎ ስለተሰማኝ ነው ይህ ጉዳይ ማንሳቴ፡፡ ስለዚህም አሁን በቀጥታ ወደ ዋናው ነጥብ አልፌ፤ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች በህብረቱ 29 ጉባኤ ላይ፤ እንደ ቀዳሚ የጋራ አጀንዳ ወስደው ስለተወያበት አፍሪካውያን ወጣቶችን በሕገወጥ ስደት ምክንያት እየደረሰባቸው ካለው አደጋ የሚታደግ መፍትሔ የማፈላለግ ጉዳይ ማንሳት ያለብኝን ተጨማሪ ሃሳብ ለማንሳት እሞክራለሁ፡፡
ይልቁንም ደግሞ ጉዳዩን ወደ ኢትዮጵያ ወቅታዊ እውነታ አምጥተን በሀገራችን ከሚስተዋለው የወጣቶች ፍልሰት ወይም ሕገወጥ ስደት አኳያ ስናየው የሚኖረውን አንድምታ በተሻለ መልኩ ለመገንዘብ ይረዳሉ የምላቸውን አንዳንድ ተጨባጭ እውነታውን የሚያመለክቱ ነጥቦች እያነሳን ከአፍሪካ ህብረቱ የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ወቅታዊ ውሳኔ ጋር የሚጣጣም የመፍትሔ ፍለጋ ጥረት ስለማድረግ ጉዳይ ሃሳብ ብንለዋወጥ ጠቃሚ ሆኖ ይሰማኛል፡፡ ስለዚህም፤ የአፍሪካ ህብረት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ፤ በአሁኑ 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ “እያንዳንዱ የአፍሪካ ሀገራት መንግስት የወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ ባሻገር፤ የውሳኔ ሰጪነት ሚናቸው እንዲጨምር የማድረግ ስራ መስራት ይኖርበታል” ሲሉ በአጽንኦት መሳሰባቸውን አስታውሼ ነው ወደ ራሴ ተጨማሪ አስተያት የምገባው፡፡
እናም አርሳቸው የህብረቱን 29ኛ መደበኛ ጉባኤ በከፈቱበት ንግግር የአህጉሪቱን ወጣት የህብረተሰብ ክፍል እየገጠመው ስላለው የሕገወጥ ፍልሰት ፈርጀ ብዙ አደጋ አንስተው የሰነዘሩት የመፍትሔ ሃሳብ፤ በእርግጥም ወቅታዊ ምላሽ የሚያሻው የአባል ሀገራቱ የጋራ አጀንዳ መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል ባይ ነኝ እኔ በበኩሌ፡፡ ይህን የምልበት ዋነኛ ምክንያትም ደግሞ፤ አሁን ላይ ህብረቱን በሊቀ መንበርነት እየመሩ የሚገኙት የጊኒው ፕሬዚዳንት አልፋ ኮንዴ “አፍሪካ ውስጥ ከሚኖረው አጠቃላይ የህዝብ ብዛት ስልሳ አምስት በመቶ ያህሉ ወጣቶች ናቸው ተብሎ ይታመናል” ሲሉ በጥናታዊ መረጃ አስደግፈው እንዳቀረቡት ከሆነ፤ ጉዳዩ የአህጉሪቷን ህዝቦች መፃኢ ዕጣ ፈንታ የመወሰን አቅም ያለውን አምራች ኃይል ከሕገ ወጥ ስደት አደጋ ታድጎ ለልማት ተግባር የማዋል ቁልፍ ጥያቄ ይሆናል፡፡
ለነገሩ አፍሪካን የብሩህ ተስፋ አህጉር ተደርጋ እንድትወሰድ ከሚያደርጓት መመዘኛ ነጥቦች መካከል አንዱና ምናልባትም ቀዳሚ ስፍራ ሊሰጠው የሚችለው ምክንያት፤ የበርካታ ወጣቶች መገኛ መሆኗ ነው የሚለውን አቋም የሚጋሩ የኢኮኖሚ ተንታኞች ጥቂት አይደሉም፡፡ ይህን መሰረተ ሃሳብ የሚያነሱት ልሂቃን አስተያታቸውን በምክንያታዊ ማብራሪያ የተደገፈ ለማድረግ የሚሞክሩትም “አፍሪካ እንደ አህጉር የበርካታ ተፈጥሮአዊ ሀብት ባለጸጋ ምድርናት ተብሎ ስለሚታመን፤ ያን በከርሰምድሯ ውስጥ አቅፋ የያዘችውን ልዩ ልዩ የተፈጥሮ ሀብቷን እያወጣች ጥቅም ላይ ማዋል የምትችለው የወጣት ዜጎቿን እውቀትና ጉልበት በአግባቡ ስትይዝ ብቻ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም” ነው የሚሉት፡፡
እናም ሰሞኑን በተካሄደ የአፍሪካ ህብረት 29ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ የተገኙት የአህጉሪቱ መሪዎች ይህን ጉዳይ ከመቸውም ጊዜ ይልቅ ትኩረት ሰጥተው ሲመክሩበት መደመጣቸው ያለ ምክንያት አይደለም ማለት ይቻላል፡፡ ይልቅስ ከላይ በትምህረተ ጥቅስ ውስጥ የተመለከተው የበርካታ የዘርፉ ምሁራን ምክር አዘል ትንተና ፈጽሞ ቸል መባል የሌለበት የዛሬዋ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ጉዳይ ስለመሆኑ፤ አጉልቶ የሚያሳይ ዓለም አቀፋዊ ጥሬ ሀቅ ባፈጠጠና ባገጠጠ መልኩ ገሃድ እየወጣ ስለመጣ ነው ህብረቱም የዚያኑ ያህል ገፍቶ ለመሔድ የሞከረው ብንል እውነታውን በተሻለ መልኩ የሚገልጸው ይመስለኛል፡፡
በእርግጥም ደግሞ የመላው አፍሪካውያን ህዝቦች መጻኢ ተስፋ፤ አህጉሪቱ የታደለችውን የገጸ ምድርና የከርሰ ምድር ተፈጥሮአዊ ጸጋ ወደ ተጨባጭ ጥቅም ለመለወጥ የሚያስችል ሀብት በማፍራት ጥረት ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለመረዳት፤ የግድ የፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም፡፡ ያን ለማድረግ የሚቻለው በተለይም የአህጉሪቷን ወጣት የህብረተሰብ ክፍል አመለካከት ከመሰረቱ የማቃናትና ሕገ ወጥ ስደት ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ እንደማይችል አምኖ ከመቀበል በሚመነጭ ቁርጠኛ አቋም ግንባር ቀደም የልማት ኃይል ሆኖ እንዲሰለፍ በማድረግ ነው የሚለው ነጥብም እንዲሁ ማንኛውም ተራ ሰው የሚስተው አይደለም፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ቁም ነገር ተደርጎ መወሰድ የሚገባው፤ የዛሬዋ አፍሪካ ውስጥ በጎላ መልኩ የሚስተዋለውን የወጣቶች ፍልሰት (ሕገ ወጥ ስደት) ለመግታትና አዲሱ ትውልድ የአህጉሪቱን ዘርፈ ብዙ ተፈጥሮአዋ ጸጋዎች ወደ ተጨባጭ ጠቀሜታ እየተለወጠ ሀብት ስለማፍራት አስፈላጊነት የምር አምኖ እንዲቀበል ለማድረግ ይቻል ዘንድ መስራት የሚኖርብንን ወሳኝ የቤት ስራ ለመስራት ምን ያህል ዝግጁዎች ነን? ለሚለው ቁልፍ ጥያቄ የምንሰጠው ተግባራዊ ምላሽ ነው፡፡
በእርግጥም ደግሞ አሁን አሁን እየተስተዋለ ካለው ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ኃይሎች አስላለፍ አኳያ እውነቱን አንስተን እንነጋገር ካልን፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌላ ማንኛውም አፍሪካዊ አገር በህብረቱ 29ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የጊኒው ፕሬዚዳንት የሰጡትን ማሳሰቢያ ተግባራዊ ለማድረግ ከመጣር ውጪ ምርጫ የሚኖረው አይመስልም፡፡ ስለዚህ እንደኔ እንደኔ የመጣጥፌ ማጠንጠኛ በሆነው ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ የህብረቱ ጉባኤ ላይ የተነሳውን መሰረተ ሃሳብ ጠቀሜታ በሚመለከት የተሟላ የጋራ ግንዛቤ መውሰድ ይገባል ብቻም ሳይሆን፤ የአህጉሪቱን ወጣቶች እየገጠማቸው ካለው አደጋና ማህበራዊ ቀውስ የሚታደግ የመፍትሔ እርምጃ ግድ እንደሚልም ጭምር እያንዳንዴ አባል ሀገር መረዳት ይጠበቅበታል የሚል ጽኑ እምነት ነው ያለኝ፡፡
ይህን የመፍትሔ ሃሳብ ወደ ተግባር ከመቀየር የተሻለ ምርጫ ሊኖር እንደማይችልም ደግሞ፤ አንዳንድ የምዕራቡ ዓለም ባለጸጋ ሀገራት ጭምር እያመኑበት የመጡ ስለመሆናቸው ማስታወስ የሚቻል ይመስለኛል፡፡ ለአብነት ያህልም ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ወደ አውሮፓ አህጉር የሚፈልሱ ሕገ ወጥ ስደተኞችን በመቀበል ረገድ ቀዳሚ ስፍራ ይዛ የምትገኘው ሀገረ ጀርመን፤ በተለይም የአፍሪካ ወጣቶችን ችግር ከምንጩ ማድረቅ ስለሚቻልበት ጉዳይ የራሷን የመፍትሔ ሃሳብ እንዳቀረበች ነው መረጃዎች የሚያመለክቱት፡፡ በዚህ መሰረትም የጀርመኗ መራሔ መንግስት (ቻንስለር) አንጌላ መርክል ራሳቸው የተገኙበት አንድ የምክክር መድረክ በቅርቡ መካሄዱን የዘገቡ የሀገር ውስጥ ሚዲያዎች መኖራቸውን አውቃለሁ፡፡
ለምሳሌ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባስደመጠን ዜና፤ መራሔ መንግስት አንጌላ መርክል “ጀርመን ወደ አውሮፓ ለመግባት ሲሞክሩ ሜዲትራኒያን ባህርባህር ውስጥ የመስጠም አደጋ የሚያጋጥማቸውን አፍሪካውያን ወጣቶች ለመታደግ የሚደረገው ጥረት ዘላቂ መፍትሔ በሚያመጣ መልኩ መካሄድ እንዳለበት ታምናለች፡፡ ስለሆነም ወጣቶቹን በሕገ ወጥ መንገድ ለመሰደድ ከመሞከር ይልቅ እዚያው ከአፍሪካ ውስጥ እየኖሩ የየራሳቸውን ስራ ለመስራት እንዲነሳሱና የገቢ ምንጭ እንዲፈጥሩ የሚያደርግ የገንዘብ ድጋፍ የመስጠት ፍላጎት አለን” ሲሉ የተሰሙበትን ንግግር አየር ላይ ማዋሉን አስታውሳለሁ፡፡
ጀርመን አሳሳቢውን ችግር ለማቃለል በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ከአፍሪካ ህብረትና እንዲሁም ደግሞ ከየሀገሪቱ መንግስታት ጋር ተቀናጅታ ለመስራት ስለማሰቧ ቻንስለሯ መግለጻቸውንም ጭምር ነው ዘገባው ያመለከተው፡ ስለሆነም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ይህን መሰሉን የባለፀጋ ምዕራባውያን መንግስታት ተነሳሽነት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ወጣቶቻቸውን ለህልፈተ ህወትና እንዲሁም ለፈርጀ ብዙ ማህበራዊ ቀውስ እየዳረገ ያለው ሕገ ወጥ ስደት እንዲገታ መስራት ይጠበቅባቸዋል የሚለው ነጥብ ላይ ልናሰምርበት ይገባል፡፡ በግልጽ አነጋገር፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ የጀመረችውን የህዳሴ ጉዞ አጠናክራ ልትቀጥልና ዳር ልታደርስ የምትችለው የአህጉሪቱን መፃኢ ዕጣ ፈንታ የመወሰን ታሪካዊ ኃላፊነት የመሸከም ብቃት ያለው ወጣት የህብረተሰብ ክፍል ሲኖር ብቻ እንደሆነ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለምና ነው ይሄን ቁልፍ ነጥብ አጽንኦት ሰጥተን እንድናየው መገደዳችን፡፡
ይልቁንም ደግሞ ሀገራችን ኢትዮጵያ፤ ለመላው አፍሪካውያን ሀገራት ከዘመናት የአውሮፓ ቀኝ ገዢዎች የባርነት ቀንበር መላቀቅ ፋና የወጋችበትን የዓድዋውን ድል ተቀዳጅታ ያሳየች የነፃት ቀንዲል እንደመሆኗ መጠን፤ ዛሬ ላይ እጅጉን በጎላ መልኩ እየተስተዋለ ያለው የአህጉሪቷ ወጣቶች ሕገ ወጥ ስደት የዘመናዊ ባርነት መገለጫ ተደርጎ ሊወሰድ እንደሚገባ በማስገንዘብ ረገድም ተጨባጭ ምሳሌ ሆኗ መገኘት ይጠበቅባታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ለዚህም ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ የምትገኝበት የህዳሴ ጉዞ፤ ሌሎቹ የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር ስር ከሰደደ ድህነትና ኋላ ቀርነት ጋር የሞት ሽረት ትግል ገጥመው ህዝቦቻቸውን ወደ ብልጽግና የሚወሰዱበትን ልማታዊ የዕድገት ጎዳና እየቀየሱ እንዲከተሏት በሚያደርግ መልኩ ሊቀጥል የማይችልበት ምክንያት እንደማይኖር ደፍሮ መናገር ይቻላል፡፡
ስለሆነም፤ በፈርጀ ብዙ የህዳሴ ጉዞ ላይ የምትገኘው የዛሬዋ ኢትዮጵያ፤ 29ኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ጉባኤ ትኩረት ሰጥቶ የመከረበትን የአህጉሪቷን ወጣቶች ከሕገ ወጥ ፍልሰት (ስደት) ታድጎ ለዘላቂ ልማት የማሰለፍ አጀንዳ ተግባራዊነት፤ ግንባር ቀደም አዎንታዊ ሚና ለመጫወት የሚያስችላትን ሀገራዊ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባት ነው የሚሰማኝ፡፡ ለህዳሴው ዘመን የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ይህን ማድረግ አንብዛም የሚያዳግት ጉዳይ ይሆናል የሚል እምነትም የለኝም፡፡
ምክንያቱም ኢትዮጵያ ሕገ ወጥ ስደትን ለማስቀረትና በተለይም ወጣቶችን የሀገራዊ ልማታችን ግንባር ቀደም ተዋንያን እንዲሆኑ ለማድረግ ስትል ብዙ ርቀት እንደተጓዘች የሚካድ ጉዳይ አይሆንምና ነው፡፡ ለአብነት ያህልም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንርፕራይዞች፤ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ወደ ስደት ከመመልከት ይልቅ እዚሁ ሀገር ውስጥ ሰርቶ እራስን መቻል እንደሚመረጥ አምኖ ይቀበል ዘንድ የማይናቅ አዎንታዊ ሚና መጫወታቸውን ማስታወስ ይበቃል፡፡
ስለዚህም በ29ኛው የህብረቱ መደበኛ ጉባኤ ላይ የተመከረ-የተዘከረባቸው አፍሪካዊ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ወደ ተግባር ተተርጉመው ለማየት ያበቃን ዘንድ እየተመኘሁ ሐተታዬን እንዲህ አጠቃልላሁ፡፡ መዓሰላማት!