Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ ከ2 ዓመት በኋላ የምታመጥቀው ሳተላይት ግንባታ እየተካሄደ ነው

0 633

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ ከሁለት ዓመት በኋላ የምታመጥቀው ሳተላይት ግንባታ እየተካሄደ መሆኑ ተገለፀ።

ይህ የተገለፀው ዛሬ የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲጀምር ነው።

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት 1ኛ ጉባኤ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰብሳቢነት ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሂዷል።

space_scince.jpg

ጉባኤው በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን የበለጠ ለማጎልበጎት የሚያስፈልጉ የቅንጅት ሥራዎችና የህግ ማዕቀፎችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም በውይይቱ ላይ እንዳሉት፥ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የሚመለከቱ ምክረ ሀሳቦች፣ ምርምሮችና ሳተላይት የማምጠቅ ስራዎች ዓላማቸው ሀገራዊ አንዳዎችን መደገፍ ነው።

ሀገራዊ አጀንዳው የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በማሳደግና መዋቅራዊ ሽግግር በማድረግ የሕዝባችን የኑሮ ሁኔታ ሁሉ አቀፍ በሆነ መልኩ ማሻሻል እንዳሆነ አብራርተዋል።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ህዋ ላይ የራሷ ሳተላይት እንደሚኖራት ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅትም ከቻይና መንግስት በተገኘ ድጋፍ የሳተላይቱ ግንባታ እየተካሄደ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ሳተላይቱም 65 ኪሎ ግራም የሚመዝን ነው ብለዋል።

ሳተላይቱ ከመሬት እስከ 700 ኪሎ ሜትር ከፍ ብሎ የሚቀመጥ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የሳተላይቱ ግንባታ ስራ ላይ የኢትዮጵያ መሃንዲሶችም እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል።

እየተገነባ ያለው ሳተላይት ሶስት ከፍሎች እንዳሉት የተነገረ ሲሆን፥ ከእነዚህም አንደኛው ወደ ጠፈር ተልኮ በዚያው የሚቀመጥ ነው።

ሁለተኛው ክፍል በእንጦጦ ላይ የሚገነባ እና ሳተላይቱን ለመቆጣጣር የሚያገለግል ሲሆን፥ ሶስተኛው ደግሞ ሳተላይቱ አገልግሎት ላይ እንዲውል የሚረዱ መተግበሪያዎች ክፍል ነው ተብሏል።

ሳተላይቱ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2019 ወደ ህዋ ይመጥቃል ያሉት ሚኒስትሩ፥ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥም ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የምድር ላይ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ይኖራታል ብለዋል።

ሳተላይቱ ወደ ጠፈር ከመጠቀ በኋላም የተለያዩ መተግበሪያዎችን በመጠቀም አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ እንደሚቻል ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ አስታውቀዋል።

65 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ሳተላይቱ በምድር ላይ ላሉ የተለያዩ አገልግሎቶች የሚውል ሲሆን፥ በተለይም የአየር ሁኔታን ለመከታተል እና ለመሰል ግልጋሎቶች እንደሚሰጥም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ምክር ቤት በዋናነት የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂን በሚመለከቱ ጉዳዮች ምክረ ሐሳቦችን የሚያቀርብ ሲሆን፥ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ሥራዎችን በባለቤትነት ይመራል፡፡

የስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የሚመለከቱ መርሃ ግብሮችን የጀመሩ ዩኒቨርሲቲዎችና ከሳይንስና ተክኖሎጂ ጋሪ ተያያዥነት ያላቸውን ሥራዎችን የሚሰሩ ተቋማት በምክር ቤቱ አባል ሆነው ታቅፈዋል።

ወደፊትም ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት አባል የሚሆኑበት ዕድል እንዳለ ተገልጿል።

በስላባት ማናዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy