HEALTH

ኤች አይ ቪ ቫይረስ ቀድሞ ከታወቀ በበሽታው የመሞት መጠን ይቀንሳል፦ ተመራማሪዎች

By Admin

July 26, 2017

ሰዎች የኤች አይ ቪ ቫይረስ በሰውነታቸው ውስጥ ቀድሞ መኖሩን ካወቁ በበሽታው የመሞት እድላቸው ዝቅተኛ እንደሚሆን የህክምና ተመራማሪዎች ገለፁ፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በኤች አይ ቪ ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች እራሳቸውን የሚያክሙት በሽታው የሰውነት የመከላከል አቅማቸውን ጎድቶ ለተለያዮ በሽታዎች ተጋላጭ ከሆኑ በሃላ እንደሆነ የዘርፉ ተመራማሪዎች ተናግረዋል፡፡

ይህንንም ዝንባሌ ለመቀልበስ የበሽታውን የህክምና አሰጣጥ በመቀየር በዓመት ከ10 ሺህ የሚልቅ የሰው ህይወት መታደግ እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ሰዎች በኤች አይ ቪ በሽታ መያዛቸውን ቀድመው ካወቁና የተለያዩ አይነት የጸረ ኤችአይቪ መድሃኒቶች ቅልቅል የሆነውን ህክምናን ከጀመሩ በኤች አይቪ ቫይረስ ብቻ ሳይሆን በሳንባ ነቀርሳና በተለያዩ በሽታዎች የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር በእጅጉ መቀነስ እንደሚቻል ነው የተናገሩት፡፡

በዚህም ሳቢያ በበሽታው የተጠቁ ሰዎች የሞት መጠን በ27 በመቶ እንዳሽቆለቆለ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ቢቢሲ