Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

  ወንዝ ለወንዝ መቀደስ ያረፈ ሰይጣንን መቅቀስ !!!!

0 647

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

     ወንዝ ለወንዝ መቀደስ ያረፈ ሰይጣንን መቅቀስ !!!!

    ይድረስ ሁለቱን ለማጋጨት ለምትጥሩ  ወንድሞቻችን  

                   ልብ በሉ !!!

           ክፍሉ ከጎንደር
በፌዴራል የመንግስት መዋቅር ስራዓት ውስጥ ዋና ከተማ ለመምረጥ ትኩረት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ ምክንያቱም፣ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው ስለሚያስተዳድሩ አንድ ክልል በተለየ ሁኔታ ለዋና ከተማነት ቦታ ሲለቅ በወሰኑ ጥያቄ ሊያነሳ ይችላል፡፡ ለምሳሌ የሜሪላንድ እና የቨርጂኒያን ግዛቶች የሚያክልለው የአሜሪካ ዋና ከተማ ዋሽንግተን ዲሲ በተለይም በቨርጂኒያኖች ጥያቄ ቀርቦበት ነው፡፡ የአሜሪካ መንግስት  የቨርጂኒያን ጥያቄ መልሶ፣ ዋሽንግተንን የፌዴራሉ መንግስት ግዛት አድርጓታል፡፡

ጀርመን ካሏት 16 ክልሎች መካከል ዋና ከተማዋ፣በርሊን በብራንድ ደበርግ ግዛት ውስጥ ትገኛለች፡፡ ነገር ግን ጀርመን የከተማውን ነዋሪ ሁኔታ እና የብራንድበርግ
አሰተዳድርን በማወያየት በርሊን የፌዴራሉ ግዛት አካል እንድትሆን አድርጓል፡፡
የካናዳዋ ርዕሰ ከተማ ኦቱዋ በኦቱዋ ግዛት ስር ትገኛለች፡፡ ኦቱዋዎች በግዛታቸው ሌሎችን የማይጎዳ የልዩ ተጠቃሚነት መብት ተችሯቸዋል፡፡ ኦቱዋወዎች ዋና ከተማቸውን ቶሮንቶ አድርገው ኦቱዋን ለፌዴራሉ መንግስት ሰጥተዋል፡፡ የአዲስ አበባ ጉዳይም ከካናዳዋ ኦቱዋ ብዙ የሚርቅ አይደለም፡፡

ህዳር 29 ቀን 1987 በፀደቀው በኢፌዴሪ ህገ-መንግስት አንቀፅ 49/5 አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል ስለምትገኝ ለኦሮሚያ ክልል በማህበራዊ ዘርፍ የልዩ ተጠቃሚነት መብት እንደሚሰጠው ተደንግጓል ፡፡ ነገር ግን የህገ-መንግስቱ አንቀፅ በዝርዝር የህግ ጉዳዮች እና መመሪያዎች ተደግፎ ተግባራዊ
ሳይሆን ለ 22 ዓመታት ያህል ዘልቋል፡፡ይህም ለኦሮሚያ ክልል ህዝብ  የቆየ ጥያቄ ሆኖ ቆይቷል፡፡ በ2009 ዓም መንግስት የኦሮሚያን በአዲስ አበባ ልዩ ተጠቃሚነት ዙሪያ አዋጅ አፀድቃለሁ ባለው መሰረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አዋጁን አፅድቋል፡፡ ቀጣይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ተወያይተው ውሳኔውን  ያፀድቃሉ፡፡አዋጁ ከአዲስ አበባ እኩል ፊንፊኔ መጠሪያ
እንዲሆን፣ኦሮመኛ ቋንቋ ከአማርኛ መሳ ለመሳ የስራ ቋንቋ እንዲሆን፣የኦሮሞ አሻራዎች በአዲስ አበባ እንዲቀመጡ፣ኦሮሚያ ክልሉ በአዲስ አበባ እንዲሆን የሚያፀኑ የህግ ማዕቀፎችን ይዟል፡፡ ከዚህ ረቂቅ አዋጅ ጋር ተያይዞ ሁለት ጠርዝ የረገጡ አብይ ሀሳቦች እየተነሱ ነው፡፡አንደኛው በኦሮሚያ በኩል አዋጁ ኦሮሚያን ተጠቃሚ አያደርግም የሚል አንድምታ ያለው ሲሆን፣ሌላው ደግሞ ሌሎች ብሄሮችን የሚያገል አዋጅ ነው፡፡ አዋጁ የኦሮሚያን የባህል ና የታሪክ ተጠቃሚነት ሁሉ አካቶ ወጥቶ ከዚህ በላይ ኦሮሚያን ተጠቃሚ አያደርግም የሚሉ ውስን ወገኖች ትዝብት ውስጥ የሚወድቁ ይመስላሉ፡፡አዲስ አበባ ከንጉስ ሚኒሊክ ጀምሮ እንኳ የ 130 ዓመት የዋና ከተማነት ታሪክ አላት፡፡ በዚህ ሂደት አዲስ አበባ የበርካታ ብሄረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ቤት ሆናለች፡፡ ነገር ግን የአዲስ አበባ ወሰን በኦሮሚያ ስላለ ለኦሮሚያ ክልል የልዩ ተጠቃሚነት መብት
ተሰጥቷል፡፡ ይህ ለብዙ ለኦሮሞ ወንድሞቻችን እንደሚያስደስታቸው አልጠራጠርም፡፡ በሌላ ጠርዝ ደግሞ አፋን ኦሮሞ ከአማርኛ መሳ ለመሳ የስራ ቋንቋ መሆኑ ሌሎች ብሄሮችን አይጎዳም፡፡ ቋንቋ መቻል እንዴት ይጎዳል? ይልቁንም ለተሻለ አብሮነት ጎህ ይቀዳል፡፡ ደቡብ አፍሪካ 11 የስራ ቋንቋዎች አሏት፡፡ እንደ ሁኔታው በ11 ዱም ትገለገላለች፡፡ በዚህ ሀገሪቱ አትርፋለች እንጂ አልከሰረችም ፡፡ ለኦሮሚያ ወንድሞቻችን የተሰጠው የልዩ ተጠቃሚነት መብት የበለጠ ጋርዮሻዊ ትስስራችንን እንደሚያጠብቀው አምናለሁ፡፡ የልዩ ተጠቃሚነት አዋጁ በተሻለ ሁኔታ በህዝባዊ ተግባቦት እንዲደምቅ ውይይት ያስፈልጋል፡፡ በውይይቶች ጎርባጣ አንቀፆች ካሉ ማስታረቅ ይገባል፡፡ የአዲስ አበባ የልዩ ተጠቃሚነት መብት ለተሻለ አብሮነት እንጂ አንዱን ጎድቶ ሌላውን ለመጥቀም አይሆንም፣ኦሮሞም ከሌሎች ጋር ተከባብሮ እና ተቻችሎ የመኖር እንጂ ሌሎችን የመግፋት ወግ፣ልምድና ባህል የለውም ፡፡ በውይይቶች የሻከሩ ሀሳቦች ቢኖሩ እንኳን ይታረቃሉ፡፡ በዚሁ አጋጣሚ ግን፣ የኦሮሚያ ወንድሞቻችን ሀሳባችሁ ተቀባይነት ስላገኘ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለትም እደፍራለሁ፡፡ የልዩ ተጠቃሚነታችሁ መብት የበለጠ አንድነታችንን ያጠናክረዋል፡፡ የኛ ሀሳብ ይህ ሆኖ ሳለ ያለተሞረደ አንደበት ባለቤቶች ከሆኑት አንዱ የሆነው ፍፁም ብርሀኔ የተባለ ሰው ያው የተለመደ ሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ለማጣላ ካለው ፍላጎት በመነሳት ወይ ዝበሉኻግበረሎም ወይ አዶም ግደፈሎም ; ትርጉሙም “ወይ ያሉህን አድርግላቸው ወይም አገራቸውን ልቀቅላቸው “ ብሎ ተረተ፡፡  ይህንኑ መርዙን ሲረጭ መላው የፊንፊኔ (አዲስ አበባ) መሬት የጎጃም ግዛት ይመስለው የነበረ ሰው ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ ነው ፡፡ ፊንፊኔ እየኖርክ ኦሮሚኛን ማጥላላት ፣የኦሮሞን ህዝብ ማዋረድና መናቅ አይቻልም፡፡ ወይ ያሉህን አድርግላቸው ወይም ..ነው ነገሩ ;  ሲል የዓላማ ወንድሙ ዳዊት ከበደ ደግም   “የኦሮሞ ደም ደሜ ነው ብለው ሲያላዝኑየነበሩ የቀድሞ ወዳጆቻችን ዛሬ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ፣ቋንቋዬ ነው ለማለት ለምን ዳገት እንደሆነባቸው ግራ ግብት ብሎኛል”  ብሎ ነበር

እንደው ለመሆኑ ኦሮሞ ጠላቱ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አይኑ እያየ መሬቱን ተቀራምተው ከገነቡት ህንፃ ስር ዘበኛ ያደረጉትን የእነዚህ ሁለት ሰዎች አክስቶች እና አጎቶች ወይስ ኮንዶሚንየሙን የሞሉትን እና “ቤት የእግዚአብሔር ኮንዶሚንየም የገብረ እግዚአብሔር የተባለላቸውን ይሆን? የኦሮሞ ህዝብ የቀድሞዎቹን ላይመለሱ ሸኝቷቸዋል፡፡ አዲሶቹን #ተነቃቅተናል# ብሏቸዋል፡፡ እኛም “የኦሮሞ ደም ደሜ ነው፣ ህመሙም ህምሜ ነው ፣ቋንቋውም ቋንቋዬ ነው” ከፈለግህ ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳን ጠይቃቸው ብለናል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy