NEWS

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ሰነድ አልባ ለሆኑ ዜጎች የሰጠው የእፎይታ ጊዜ በተጨማሪ አንድ ወር አራዘመ

By Admin

July 26, 2017

 

የሳውዲ አረቢያ መንግስት ሰነድ አልባ ለሆኑ ዜጎች የሰጠው የእፎይታ ጊዜ በተጨማሪ አንድ ወር አራዘመ

የኢፌዴሪ መንግስት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት ዜጎቻችንን ከሳውዲ አረቢያ ለማውጣት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ የእፎይታ ጊዜውን በአንድ ወር ማራዘሙን የሳውዲ አረቢያ መንግስት አስታውቋል። ዜጎቻችን ይህን እድል ተጠቅመው እራሳቸውን ከህግ ተጠያቂነት እና እንግልት ለማዳን ሪያድ፣ጂዳ፣ እና ሌሎች አገልግሎቱን በሚሰጥባቸው ጣቢያዎች በመገኘት የጉዞ ሰነድ በመውሰድ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እናሳስባለን። አሁን የተራዘመው የእፎታ ጊዜ እስከ ነሃሴ 18 ቀን 2009 ዓ.ም እንደሚቆይ ነው የተገለጸው።