Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአማራና የትግራይ ህዝብ የማይነጣጠል አንድነት ተጠናክሮ ይቀጥላል—የሃገር ሽማግሌዎች

0 1,138

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለዘመናት በሰላም አብረው የኖሩት የአማራና የትግራይ ህዝቦች የማይነጣጠል አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሃገር ሽማግሌዎች ገለጹ።

ከትግራይ እና ከአማራ ክልል የተውጣጡ የሃገር ሽማሌዎች የሚሳተፉበት ህዝባዊ ኮንፈረንስ በመቀሌ ከተማ ከሐምሌ 14 እስከ ሔምሌ 16/2009 ዓ.ም ይካሔዳል።

ኮንፈረንሱን አስመልክቶ የሁለቱም ህዝቦች ተወካይ የሃገር ሽማግሌዎች ዛሬ ጠዋት በመቀሌ ከተማ በሰጡት መግለጫ እንዳመለከቱት ለዘመናት የቆየው የሁለቱ ህዝቦች አብሮነት ስር የሰደደ ነው።

በመግለጫው ከትግራይ ህዝብ የተወከሉ የሃገር ሽማግሌ መልአከ ፀሀይ ተሻለ ገብረሚካኤል  እንደገለጹት ሁለቱም ህዝቦች  ከተለያዩ  አብራኮች የወጡ  ሳይሆኑ መንታ ህዝቦች ናቸው።

“የጣልያን ወረራን ለመደምሰስ በአድዋና በተለያዩ የአገሪቱ አከባቢዎች በጋራ  መስዋእትነት የከፈሉ ህዝቦችም ናቸው” ብለዋል።

በደርቡሽ ወረራ መተማ ዮሀንስ በጋራ ተሰልፈው የከፈሉት መስዋእትነት ለአብሮነታቸውና አንድ ስለመሆናቸው የሚገልጽ  የቅርብ ጊዜ የታሪክ ማስረጃ እንደሆነም ገልጸዋል።

ከአማራ ክልል  የተወከሉት የሃገር ሽማግሌ አቶ ሞላ መኮንን በበኩላቸው ባለፈው ዓመት በአንዳንድ የክልሉ አከባቢዎች የተፈጠረው ግጭት የሁለቱንም ህዝቦች የቆየ ግንኙነት የማያበላሽ መሆኑን ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ሐሙስ በሚጀመረው ሕዝባዊ ኮንፈረንስ የሁለቱም ክልሎች ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ የክልልና የፌደራል ከፍተኛ አመራሮች ተሳታፊ እንደሚሆኑ ከኮንፈረንሱ አዘጋጆች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከወራት በፊት በአማራ ክልል  በታች አርማጮህ ወረዳ በሳንጃ ከተማና በትግራይ ክልል ደግሞ በሰቲት ሑመራ ከተማ መሰል ህዝባዊ ውይይቶች መካሄዳቸው ይታወሳል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy