Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአንጎላ ጥንታዊ ከተማ ሜባንዛ ኮንጎ የአለም ቅርስ መዳረሻ ሆና ተመዘገበች

0 2,024

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአንጎላ ጥንታዊ ከተማ ሜባንዛ ኮንጎ የአለም ቅርስ መዳረሻ ሆና ተመዘገበች
የአንጎላዋ ከተማ ሜባንዛ ኮንጎ የኮንጎ ኪንግደም የፖለቲካና መንፈሳዊ መዳረሻ በመሆን አገልግላለች፤ ይህም በደቡብ አፍሪካ ከ14-19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩ ትላልቅ መንግስታት አንዷ ነበረች፡፡

በዚህ ታሪካዊ ስፍራ የነገስታት መኖሪያ ፣ባህላዊ ችሎት ፣”ቅዱስ ዛፍ” እና የነገስታት መቃብር ይገኛል ፤ፖርቹጋሎች በ15ኛው ክፍለ ዘመን በስፍራው ሲደርሱ ከተሜነትን ለማስፋፋት በአውሮፓውያን የአገነባብ ስልት የአካባቢውን ቁሶች ተጠቅመው ግንባታ ማከናወናቸውን ዩኔስኮ ገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የደቡብ አፍሪካው ኮማኒ የተሰኘው የተፈጥሮ አቀማመጥ የአለም ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ ተወስኗል፤ በአካባቢው በስፋት የሚታየው አሸዋ የሰው ልጅ ከድንጋይ ዘመን እስከአሁን በአካባቢው እንደኖረበት አመላካች እንደሆነ ዩኔስኮ ገልጿል ፤ቦታው ለረዥም ጊዜ የኖሩበትን የኮማኒ ህዝቦች ባህልን እንደሚያንፀባርቅና አስቸጋሪውን የበረሃ ኑሮም የተላመዱበትን ስትራተጂ እንደሚያሳይ ሲጂቲን ዩኔስኮን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy