Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ህገ መንግስታዊ ነው!

0 625

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም ህገ መንግስታዊ ነው!

ዳዊት ምትኩ

በቅርቡ ኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በአዲስ አበባ ላይ ስላለው ልዩ ጥቅም አስመልክቶ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ቀርቧል። ይህ ልዩ ጥቅም በህገ መንግስቱ አንቀፅ 49 ላይ የሰፈረ ነው። በህገ መንግስቱ በዚሁ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ አምስት ላይ “የኦሮሚያ ክልል የአገልግሎት አቅርቦት ወይም የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀምና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በተመለከተ እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የምትገኝ በመሆኗ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳስሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ያለው ልዩ ጥቅም ይጠበቅለታል። ዝርዝሩ በህግ ይወሰናል” የሚል ድንጋጌ ሰፍሯል።

በዚህ መሰረት የተለያዩ አካላት ከተወያዩ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የተላከው ረቂቅ አዋጅ ህገ መንግስታዊ ከመሆኑም በላይ፤ ሌላውን ብሔር ለመጉዳት ተብሎ አይደለም። እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች በደማቸው የፃፉት ሰነድ ነው።

የዚህ ሰነድ ዓላማ በህዝቦች መፈቃቀድና ፍላጎት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለማጎልበት እንዲቻል በጋራ ያፈሯቸው እሴቶችና ሃብቶች እንዲሁም ትስስሮች እንዳሏቸው በማመን በታሪካቸው ሂደት ውስጥ ያጎለበቷቸውን የጋራ ጉዳዮች ይበልጥ ለማበልፀግና የተዛቡ ግንኙነቶችንም በማረም አንድ ጠንካራ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ እና የጋራ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ለማጠናከር የታለመ መሆኑ ይታወቃል።

ታዲያ ይህን በማድረግም በሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ዋስትና ያለው ዴሞክራሲ እንዲሰፍንና ፈጣንና ህዝቡ በየደረጀው ተጠቃሚ የሚሆንበትን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት ለማፋጠን በራሳቸው ፈቃድና በፍላጎታቸው የመረጡት መሆኑን ከማንም የተሰወረ አይደለም።

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን ልዩ ጥቅም በህገ መንግሥቱ እንዲሰፍር ያደረጉት የኦሮሞን ህዝብ ጨምሮ መላው የሀገራችን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ናቸው። እናም እነዚህ የህገ መንግስቱ ባለቤቶች በአዲስ አበባ ላይ የኦሮሚያ ክልል የሚኖረውን ልዩ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ረቂቅ አዋጅ ማዘጋጀታቸው ትክክለኛና ተገቢ ነው። እንዲያውም በእኔ እምነት አዋጁ እስካሁን መዘግየት አልነበረበትም ባይ ነኝ። ይህን ህገ መንግስታዊ ድንጋጌ መቃወምም ኢ-ህገ መንግስታዊነት ይመስለኛል።  

የጥበትና የትምክህት ሃይሎች ጉዳዩን ሌላ ቅርፅ በማስያዝ በህዝቦች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር ሙከራ ማድረጋቸው አሁንም እንዳለፉት ጊዜያት ከህግ መንግሰቱ ጋር ከመጋጨት ውጭ የሚያስገኝላቸው ጥቅም የለም። እነዚህ ሃይሎች በጥበትና በትምክህት የተወጠሩ በመሆናቸው ህገ መንግስቱን አያከብሩም። ሲከበር ማየትም አይፈልጉም። ለዚህም ነው—የኦሮሚያን ክልል ልዩ ተጠቃሚነት ለማጥላላት የሚሞክሩት።

ያም ሆኖ የአገራችን ህዝቦች በፈቃዳቸው እውን ያደረጉት ፌዴራላዊ ስርዓት ያለፉ የተዛቡ ግንኙነቶችን ለማረም መሆኑ ይታወቃል። ባለፉት ስርዓቶች ኢትዮጵያ የብሔሮችና ብሔረሰቦች እሥር ቤት ልትሆን የቻለችው የቡድን ማንነቶች ማፈን ዋነኛ የጭቆና መገለጫ ስለነበር ነው። ይህን ጭቆና በትግል በማስወገድ የራስ አስተዳደር መብትን በማረጋገጥ ብቻ የሚመለስ አልነበረም።

የህዝቦች ሁለንተናዊ መብቶች መከበር ነበረባቸው። ከእነዚህ መብቶች ውስጥ ህዝቦች የተስማሙበት እንደ የኦሮሚያን ልዩ ተጠቃሚነት ዓይነት መብቶች እውን መሆን አለባቸው። እናም ረቂቁ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩትን የተዛባ ግንኙነት በተጠናከረ ሁኔታ ከማረም ባሻገር፣ በህገ መንግስቱ ህዝቦች ለህዝቦች የፈቀዷቸው መብቶችን እውን ከማድረግ አኳያ መታየት ይኖርበታል።

የኢፌዴሪ ህገ መንግስት የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኘው ልዩ ጥቅም የሚደነግገው በአስተዳደራዊ ጉዳዩች ላይ ነው። በዚህም መሰረት ከአገልግሎት አቅርቦት ልዩ ጥቅም አኳያ፣ ከተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምና የአካባቢ ጥበቃ ጋር የተያያዘ ልዩ ጥቅሞች እንዲሁም አዲስ አበባ በኦሮሚያ ክልል መሐል የምትገኝ በመሆኑ የሚነሱ ሁለቱን የሚያስተሳሰሩ አስተዳደራዊ ጉዳዮችን ማዕከል ያደርጋል። በመሆኑም የኦሮሚያ ክልል ያለው ልዩ ጥቅምን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አንቀፆች እንዲቀረፁና እንዲካተቱ ተደርጓል። ይህ ሁኔታ ህገ መንግስቱን ከማስፈፀም ውጪ ሌላውን አካል ለመጉዳት ታስቦ አይደለም። ሊሆንም አይችልም።

ለአብነት ያሀል በከተማዋ ውስጥ የሚገኙ የአርሶ አደሩ ልጆችንና አዲስ አበባ ወይም ፊንፊኔ የኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በመሆኗ ምክንያት ልጆቻቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው ማስተማር ለሚፈልጉ ዜጎች የከተማ አስተዳደሩ በአፋን ኦሮሞ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ማደራጀት እንዳለበት በረቂቅ አዋጁ ላይ መስፈሩ የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ሊጎዳ እንደሚችል ለማንም ግልዕ አይደለም።

በእንዲሁም በረቂቅ አዋጁ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ ላይ ያለው የኦሮሚያ ክልል ነዋሪ አብዛኛውን አገልግሎቱን በተለይም የሆስፒታል አገልግሎቶችን ከከተማዋ የሚያገኝ በመሆኑ በኦሮሚያ እምብርት ላይ የተቆረቆረች ይህች ከተማ ይህንን አገልግሎት ለመስጠት በእቅዷ ውስጥ ማካተት ይኖርባታል መባሉ የትኛውን የህብረተሰብ ክፍል ይጎዳ ይሆን?…

ይህ የከተማዋ የሆስፒታል አገልግሎት ቀደም ሲል የነበረ ነው። የተደረገው ነገር በህግ እንዲሰፍር ማድረግ ብቻ ነው። እርግጥ ረቂቅ አዋጁ የትኛውንም ወገን አይጎዳም። ጠባቦችና ትምክህተኞች ግን ይህን ሁኔታ ገልብጠው በመመልከት ለማራገብ ይሞክራሉ። የተለየ ቅርፅ በማስያዝም ሌላው ወገን የተጎዳ አስመስለው ያቀርባሉ። ምክንያታቸው ግልፅ ነው። እርሱም ህዝብን ከህዝብ ጋር በአሉባልታ ለማጋጨት በመጣር እዚህ ሀገር ውስጥ ሰላምና መረጋጋት እንዳይኖር ማድረግ ነው።

የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ የሚያገኛቸው ጥቅሞች ሌላ ትርጉም ሊሰጣቸው አይገባም። አገልግሎቶቹ በሚቀርቡበት ጊዜ የኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ከተማና ከሌሎች ክልሎች በተለየ ሁኔታ ሊጠበቅለት የሚገባው ልዩ ጥቅምን ለማመላከት ብቻ ነው።

በአዲስ አበባ ነዋሪ ዜጎች ላይ በብሔር ልዩነት ምክንያት የተለየ ጥቅም ለማቅረብ አይደለም። የትኛውንም ብሔር ለመጉዳት አይደለም። እዚህ ሀገር ውስጥ በብሔር ልዩነት ምክንያት በግለሰብ ባለሃብቶች፣ በመንግሥት ሰራተኞች ወይም በማናቸውም ዜጎች መካከል ልዩነት ሊኖር አይችልም። ዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እያበበ ባለበት ሀገር ውስጥ እንዲህ ዓይነቱ ተግባር ሊፈፀም አይችልም።

ያም ሆኖ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመጠጥ ውሃ የሚያገኘው በአብዛኛው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ከሚገኙ የከርሰና የገፀ ምድር መገኛዎች በመሆኑ ከዚህ አኳያ ጉድጓዱ የሚቆፈርበት፣ ግድብ የሚለማበት ወይም የውሃ መስመሩ አቋርጠው የሚያልፍባቸው የክልሉ ከተሞች እንዲሁም ቀበሌዎች በአስተዳደር ወጪ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በረቂቅ አዋጁ ላይ መቀመጡ ችግር ሊኖረው አይችልም።

በአጠቃላይ በአስተዳደራዊም ይሁን በማህበራዊ መብቶችም ይሁኑ በሌሎች ጉዳዩች የኦሮሚያ ክልል ከአዲስ አበባ መስተዳድር እንዲያገኝ የቀረበው ልዩ ጥቅም ህገ መንግስቱን ገቢራዊ ከማድረግ ውጪ ሌላ ዓላማ የሌለው መሆኑን ግንዛቤ መያዝ ይገባል።  

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy