Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ፓርቲዎቹ የፖለቲካ ምህዳር ለማስፋት የሚረዱ አዋጆችን በቅድሚያ ለመደራደር ተስማሙ

0 424

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ፓርቲዎቹ የፖለቲካ ምህዳርን ለማስፋት በሚረዱ አዋጆች ላይ በቅድሚያ ለመደራደር ተስማሙ

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች 12 የድርድር አጀንዳዎችን በቅደም ተከተል በማስቀመጥ በሰነድ መልክ አፅድቀውታል።

ተቀዳሚ ረዳት አደራዳሪው አቶ ዋሲሁን ተስፋዬ በአደራዳሪዎቹ በቀረቡት የድርድር አጀንዳዎች ቅደም ተከተል ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡ አጀንዳዎችን ቦታ በመለዋወጥ ብቻ መፅደቁን ተናግረዋል።

በዚህ መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ አዋጅ 573/2000፣ የምርጫ ህግ አዋጅ 532/1999፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የስነ ምግባር አዋጅ 662/2002፣ የፀረ ሽብር ህግ፣ የብዙሃን መገናኛ አዋጅ፣ የበጎ አድራጎትና የማህበራት አዋጅ፣ የዴሞክራሲና የሰብአዊ መብት ተቋማት አደረጃጀትና አፈፃፀም በተመለከተ ከአንድ እስከ ሰባት በቅደምተከተል ድርድር ይደረግባቸዋል ብለዋል።

አቶ ዋሲሁን እንዳሉት የፍትህ አካላት አደረጃጀት አዋጅና አፈፃፀም፣ ዜጎች በየትኛውም የአገሪቱ ክፍሎች የመዘዋወር የመኖር ንብረት የማፍራት መብትና የህግ ማዕቀፍ፣ የሊዝ አዋጅና የልማት ተፈናቃዮችን፣ የታክስ ስርዓት እና ብሔራዊ መግባባትን የተመለከቱ አጀንዳዎችን ከ8 እስከ 12 በማስቀመጥ በቅደም ተከተል ድርድር ይደረግባቸዋል።

በውይይቱ “ምርጫ እየቀረበ ስለሆነ የምርጫ ህጎች ይቅደሙ” አይደለም “ብሔራዊ መግባባት መቅደም አለበት” የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ሀሳቦች ተነስተዋል።

ፓርቲዎቹ በተዘጋጀው የፅሑፍ አቀራረብና የጊዜ ሰሌዳ መርሀ ግብር ላይም ማሻሻያ በማድረግ አፅድቀውታል።

ተቀዳሚ ረዳት አደራዳሪው እንዳሉት ሁሉም ፓርቲዎች በሚደራደሩባቸው በ12ቱም አጀንዳዎች ፅሑፍ አስቀድመው ለገዢው ፓርቲ የሚያቀርቡ ይሆናል።

ገዢው ፓርቲም እንዲሻሻሉ በሚፈልጋቸው አጀንዳዎች ብቻ ለተደራዳሪ ፓርቲዎች እንዲሻሻሉ የሚፈልጋቸውን ነጥቦች በፅሑፍ ያቀርባል ብለዋል።

ፓርቲዎች በማይደራደሩበት አጀንዳ ላይ ፅሑፍ የማቅረብና የመገኘት ግዴታ የለባቸውም በማለትም ፓርቲዎቹ የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

አደራዳሪዎቹ ከተደራዳሪ ፓርቲዎች የሚቀርቡ የድርድር አጀንዳዎች የተመለከቱ ፅሑፎች በአንድ ቀን ውስጥ በአደራዳሪዎች በኩል እንዲሰራጭ ያደርጋሉ። ፓርቲዎች ድርድሩን በ90 ቀናት ውስጥ ለማጠናቀቅና በሳምንት ሶስት ቀን ለመደራደርም ተስማምተዋል።

ባፀደቁት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አንድ የድርድር አጀንዳ ከአምስት ቀናት በላይ የማይወስድ ሲሆን  አጀንዳዎች በቅደም ተከተል ድርድር የሚደረግባቸው ይሆናል።

በመጨረሻ ፓርቲዎቹ በዝግ ባካሄዱት አጭር ስብሰባ ለሚካሄደው ድርድር የሚያግዝ የሎጂስቲክ ኮሚቴ አቋቁመዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy