Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ሁለት ፓርቲዎች ሀገር ዓቀፉን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ተቀላቀሉ

0 408

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሀገር አቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአባልነት ጥያቄ ያቀረቡ ሁለት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ተቀበለ።

የአባልነት ጥያቄ ካቀረቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ህብረት (ኢዴህ) እና የመላው ኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኦህዴፓ) ወቅታዊ ሰነዶቻቸውን አሟልተው በመቅረባቸው ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል፡፡

ሌሎች በአባልነት መቀላቀል የሚፈልጉ አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሰነዶቻቸውን  አማልተው ከቀረቡ በአጭር ጊዜ እንደሚስተናገዱ ምክር ቤቱ አስታውቋል፡፡

በሌላ ዜና ምክር ቤቱ የ2009 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ገምግሞ  የ2010 በጀት ዓመት ዕቅዱን አፅድቋል።

የጋራ ምክር ቤቱ በግምገማው ባለፈው  በጀት ዓመት የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልልን፣ ታላቁን የህዳሴ ግድብ ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ከተማን የውሃ መጠጥ ፕሮጀክቶች እና የጋምቤላ ክልልን የመንደር መሰባሰብ ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ያደረገውን ጉብኝት በጥንካሬ ተመልክቶታል፡፡

በመስክ ምልከታው  የተለዩ ጠንካራ ጎኖች እንዲቀጥሉ እንዲሁም ደካማ ጎኖች እንዲስተካከሉ ሃሳብ ማቅረቡንም እንዲሁ።

የመደበኛ ስብሰባዎች መቆራረጥና የክትትልና ቁጥጥር ማነስ በበጀት ዓመቱ ከታዩ ድክመቶች መካከል በዋናነት  ተጠቅሰዋል።

በ2010 በጀት ዓመት በአካባቢያዊ ምርጫ ጠንካራ እንቅስቃሴ ለማድረግ፣ በሚዲያ ክርክሮችና ውይይቶችን ለማካሄድ ፣ የስልጠናና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ለማከናወንና የጋራ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ለማደራጀት  አቅዷል።

ምክር ቤቱ በተለያዩ አካባቢዎች የመስክ ምልከታ ለማድረግ ያቀደ ሲሆን በሚወጡ አዳዲስ ሀገራዊ ፖሊሲዎች  ግብአት በመስጠት እንደሚሳተፍም ገልጿል።

በዕቅድ አፈፃፀም ላይ የሚያጋጥሙ ክፍተቶችን በወቅቱ ማስተካከል እንዲቻል  የአጀንዳ ኮሚቴ የክትትልና ቁጥጥር ሥራውን ደርቦ እንዲሰራ ኃላፊነት ተሰጥቶታል።

የጋራ ምክር ቤቱ ዛሬ በአባልነት የተቀላቀሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ አስር አባላት አሉት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy