Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ስደት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ያሳጣል!

0 281

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ስደት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ያሳጣል!

                                                               ታዬ ከበደ

የህገ ወጥ ስደትን አስከፊነት ነው። በስደት ውስጥ ሆኖ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን ማስጠበቅ አይቻልም። ሁለንተናዊ ውርደትንም ያስከትላል። ህገ ወጥነት ሁሌም ህገ ወጥነት በነሆኑ ለሌላ ህገ ወጥ ተግባር መጋለጥን ያመጣል። የሰው ልጅ ሰው በኘሆኑ ሊከበሩለት የሚገቡት ሰብዓዊ መብቶች ዋጋ ያጣሉ።

ታዲያ መንግስት ወደ ውጭ ለመሄድ የሚፈልጉ ዜጎች የተመቻቸውን ህጋዊ መንገድ መጠቀም እነዚህን ሁሉ አደጋዎች የሚያስቀር ነው። ህጋዊው መንገድ ዜጎች ምንም ዓይነት አካላዊም ይሁን አዕምሮአዊ እንግልት ሳይደርስባቸው ኑሮቸአቸውን ለመምራት ያስችላቸዋል። ህግ ወጥነት እንደ አማራጭ መያዝ መዘዙ የከፋ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል። ዜጎች ወደ ፈለጉት ቦታ የመንቀሳቀስ ህገ መንግስታዊ መብት ያላቸው ቢሆንም፤ በሀገር ውስጥ ያለውን ሰርቶ የማደግ ሁኔታን በአማራጭነት መያዝም ይገባል።

እንደሚታወቀው ሁሉ በህገ ወጥ ስደት አደጋ የሚጠቁ ኢትዮጵያውን የስደታቸው መንስዔ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮቻቸው መሆኑን ሲገልፁ ይደመጣል። በእርግጥ ድህነትና ስራ አጥነትን ለመቅረፍ የጥቃቱ ሰለባ የሚሆኑ ዜጎቻችን ቁጥር በቀላሉ እንደማይገመት የሚታወቅ ቢሆንም፤ የችግሩ መንስኤ ግን ሁሉንም ይወክላል ብሎ መፈረጅ ተገቢ አይመስለኝም። ምክንያቱም በህጋዊ መንገድ መውጣት እየተቻለና ሰርተው መበልፀግ የሚያስችል ገንዘብ እያላቸው ለህገ ወጥ አዘዋዋሪ ከፍለው ለችግሩ የሚጋለጡ ዜጎች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን በዓይናችን የምናየውና በጆሯአችን የምንሰማው ሃቅ ስለሆነ ነው።

ለነገሩ ማንም ሰው በላቡ ጥሮና ግሮ ህይወቱን ለማሻሻል የማይሻ ሰው አለ ብሎ ለመናገር አይቻልም። ለዚህ አባባሌ መላው ህዝባችንና መንግስት ከድህነትና ኋላቀርነት ለመውጣት ከፍተኛ ትግል በማካሄድ ላይ የሚገኙበት ዋነኛው ምክንያታቸው ለዜጎች ብልፅግና እና ኑሮ መሻሻል መሆኑን በአስረጅነት መጥቀስ የሚቻል ይመስለኛል።

ታዲያ ዜጎች ድህነትን ለመቅረፍ የሚያደርጉት ተነሳሽነት ትክክል አይደለም ሊባል የማይችል ቢሆንም፤ በህገ ወጥ ደላሎችና አፈ ቅቤዎች ተታልለው የእነርሱ ሲሳይ መሆናቸው ግን እጅጉን የሚያሳዝን ነው። ከዚህ ባሻገርም ሁሉም ነገር ህግን የተከተለ አካሄድ ተጠቅሞ ማደግና ራስን ጠቅሞ ቤተሰብንና ሀገርን መጥቀም እየተቻለ ህገ ወጥ አካሄድን መርጦ ለእንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ መጋለጡ ተገቢ አይደለም። በቅድሚያ አገራዊ ሁኔታን መመልከት ይገባል።

እርግጥም እዚህ ሀገር ውስጥ ሰርቶ ማደግና መለወጥ ይቻላል። የኢትዮጵያ መንግስት በሀገራችን የተንሰራፋውን ድህነትንና ኋላቀርነትን ለማስወገድ የተለያዩ ስልቶችን ቀይሶ መንቀሳቀስ ሲጀምር፤ ስራ አጥነት መቅረፍ አንደኛው ተግባሩ በማድረግ ነበር። እናም ወደ ስደት ፊትን ከማቅናት በፊት ይህን አገራዊ ሁነታ መቃኘት የሚገባ ይመስለኛል።

ይህም ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በዚያች ሀገር የሚኖሩ ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸው ሳይጠበቅላቸውና ክብራቸው ተገፍፎ በአደጋ ውስጥ ሊገኙ እንደሚችሉ የሚያመላክት ይመስለኛል። እናም ምንም እንኳን የዜጎች በፈለጉት ቦታ ተንቀሳቅሰው የመስራትና ንብረት የማፈራት ህገ መንግስታዊ መብት ቢኖራቸውም፤ ይህን መብታቸውን ህጋዊ በሆነ መንገድ መጠቀም ያለባቸው ይመስለኛል።

ኢትዮያዊ ዜጋ ከሀገር ወጥቶ ለመስራት እስከፈለገ ድረስ ህጋዊ ሆኖ በመንግስት ዕውቅና መብቱና ክብሩ ተጠብቆለት የሚሰራበት ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል። እዚህ ሀገር በመከናወን ላይ ካለው ተምሳሌታዊ ልማታዊ ተግባር ባሻገር፤ ዜጎች ወደ ውጭ ሄደው እንዲሰሩ በመንግስት የወጣው የውጭ ሀገር የስራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 ይህን ህጋዊነት እያረጋገጠ ነው።

እንደሚታወቀው ህገ ወጥ ስደት የሀገርንና የወገንን ክብር የሚነካ ባርነት ነው። እናም ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸውና ክብራቸው ሳይነካ መንገስት በፈጠረው ምቹ ሁኔታ መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ማንኛውም ዜጋ በሀገሩ ለመስራት ካልፈለገና ‘በውጭ ሀገር ሰርቼ ሃብት አፈራለሁ’ ብሎ ካሰበ የሚከለክለው አካል አይኖርም። ምክንያቱም በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ የዜጎች የመንቀሳቀስ መብት ህገ መንግስታዊ እውቅና እና ጥበቃ ያለው ነው። ማንኛውም ዜጋ በፈለገው ጊዜና ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራትና ሃብት የማፍራት የማይገሰስ ህገ መንግስታዊ መብት አለው። ይህን ማንም ሊቀለብሰው አይችልም። ይህን መብት መቃወም ህገ መንግስቱን መፃረር ነው።

ታዲያ ይህን ህገ መንግስታዊ መብት በአግባቡና ህጋዊ በሆነ ሁኔታ መጠቀም ይገባል። አንድ ዜጋ ባሻው ቦታ የመንቀሳቀስ መብት ስላለው ብቻ ራሱን ለአደጋ ቤተሰቡን ደግሞ ለችግርና ለስጋት አጋልጦ ህገ ወጥ መንገድን መጠቀም ያለበት አይመስለኝም።

የኢፌዴሪ መንግስት ይህን የዜጎችን እንግልትና ችግር በመመልከት ዜጎች ለስራ ወደ ውጭ ሲጓዙ ከሞት፣ ከእንግልትና ከስቃይ ይላቀቁ ዘንድ ህጋዊ የአሰራር ማዕቀፍን አበጅቷል። በተለይም ከላይ የጠቀስኩት አዋጅ ቁጥር 923/2008 የውጭ ሀገር የስራ ስምሪትን ህገዊ በሆነ መንገድ ለመፈፀም የተዘጋጀ ነው።

በዚህ አዋጅ ተመርቶ በህዊ መንገድ ወደ ውጭ የስራ ስምሪት ማድረግ ራስን ከአደጋ ቤተሰብን ደግሞ ከሃሳብና ከሰቀቀን የሚታደግ ይሆናል። ይህን አዋጅ ተጠቅሞ በህጋዊ መንገድ ወደ ውጭ መጓዝ የህገ ወጥ ደላላዎችን መንገድ ይዘጋል።

በአጠቃላይ ህጋዊነትን ተቀብሎ በህግ አግባብ ማንኛውንም ነገር ማከናወን ራስን ከአደጋና ከውርደት በመጠበቅ የሀገርን ክብርም ማስጠበቅ መሆኑን ግንዛቤ መያዝ የሚገባ ይመስለኛል።

ያም ሆኖ አገራችን በአሁኑ ወቅት ሀገራችን በትክክለኛ የልማት ጎዳና ላይ ትገኛለች። ዕድገቱም ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፈጠሩ ዜጎች የልማቱ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል፡፡ በተለይም ወጣቶች በአነስተኛና ጥቃቅን ልማታዊ ሥራዎች ላይ በመሳተፋቸው የቤተሰብ እጅን ከመጠበቅ ለመዳን ችለዋል። እንዲያውም ራሳቸውን ከመቻል አልፈው ቤተሰቦቻቸውንም እየረዱ ነው።

በዚህም በከተሞች የሚታየውን የስራ አጥነት ችግር ለመቅረፍ ጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራትን በማደራጀት እንዲሁም የብድር አገልግሎት በመስጠት ለዜጎች የስራ ዕድል መፍጠር ችሏል። ዜጎችም በየሙያቸው በመሰማራት ለሀገራዊ ልማት ከፍተኛ ጉልበትና አቅም መሆን መቻላቸውን አረጋግጠዋል።

ዛሬ በጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ከመንግስት እንዲሁም ከቁጠባና ብድር ተቋማት ባገኙት ገንዘብ ተጠቅመው ወደ መካከለኛ ኢንዱስትሪ ባለቤትነት የተሸጋገሩ ዜጎች በርካታ ናቸው፡፡ እነዚህ ዜጎች ከራሳቸው አልፈው ለሌሎችም የሥራ ዕድል በመፍጠር የመንግስትን ጥረት በመደገፍና የሀገሪቱን ልማት በማፋጠን ላይ እንደሚገኙ እማኝ የሚያስፈልገው ጉዳይ አይመስለኝም። ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብትን ላለማጣት ይህን አገራዊ ሁኔታ በተገቢው መንገድ መረዳት ይገባል።

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy