በዘመቻ መትከል ብቻ ሳይሆን እንክብካቤም ይሻሉ!
በዘመቻ መትከል ብቻ ሳይሆን እንክብካቤም ይሻሉ!
ወንድይራድ ኃብተየስ
ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ከአረንጓዴ ልማት ጋር ለማስተሳሰር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ነች። እ.አ.አ ከ2011 ከደቡብ አፍሪካ ደርባን ከተካሄደው የዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ በፊት አገራችን የአየር ንብረት ለውጥ አሳስቧት የተለያዩ ተግባራትን ታከናውን ነበር። የኢፌዴሪ መንግስት ወደ አገሪቱን መምራት እንደጀመረ ለአየር ንብረት ለውጥ ከፍተኛ ትኩረት አድርጓል። ኢትዮጵያ ባለፉት 26 ዓመታት ባካሄደችው የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገብ ችላለች። በአካባቢ ጥበቃ ስራ ሳቢያ በርካታ የስራ እድሎች ተፈጥረዋል። በተካሄዱ የተፋሰስ ልማት ሳቢያ ወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል ስለተፈጠረላቸው ገቢያቸው ተሻሽሏል። የበርካታ ዜጎች ህይወት ተቀይሯል።
በቀጣይ ሁለት ወራት በቻይና በሚካሄደው ዓለም አቀፍ ውድድርና ሽልማት ላይ አገራችን በረሃማነትን ለመከላክል ባደረገችው ጥረት ለሽልማት ታጭታለች። አገራችን ባከናወነችው የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ሳቢያ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂን ተግባራዊ በማድረግ ምርጥ ተብለው በተባበሩት መንግስታት የበረሃማነት መከላከል ምክር ቤት ለመጨረሻ ዙር ውድድር ከታጩ ስድስት የዓለም ሀገራት መካከል አገራችን በትግራይ ክልል በተከናወኑ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ለሽልማት መታጨት ችላለች። ኢትዮጵያ በረሃማነትን ለመከላክል በህዝብ ነፃ ጉልበት ባከናወነችው የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ ያስመዘገበችው ተጨባጭ ለውጦች እንዲሁም የህዝቡ በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በፍላጎትና በነጻ ላይ የተመሰረተ አስተዋጽዖ ማድረጉ ነው።
አገራችን በዘንድሮው የክረምት ወቅት ብቻ በቢሊዮን የሚቆጠሩ አገር በቀል የሆኑ ችግኞችን በመትከል ላይ ነች። ይህ እንደእኔ መልካም ነገር ነው። ባለፉት አመታት በርካታ ችግኞችን በመትከል እንዲሁም ሰፊ የተፋፈሰስ ስራዎችን ማከናወን በመቻሉ የአገሪቱ የደን ሽፋን እጅግ አስገራሚ በሆነ ፍጥነት ዕድገት አሳይቷል። ከአካባቢ ጥበቃና ደን ሚኒስቴር በ2008 ዓ ም ማብቂያ አካባቢ የወጣ መረጃ እንደሚያመላክተው የአገራችን የደን ሽፋንም በጥቅል ሲታይ 15.5 በመቶ ደርሷል። የደን ልማቱ በክልል ስርጭት ሲታይ በኦሮሚያ 20.29 በመቶ፣ የአማራ 10.44 በመቶ፣ የትግራይ 9.13 በመቶ፣ የደቡብ/ብ/ብ/ሕ 25.83 በመቶ፣ የጋምቤላ 30.83 በመቶ፣ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ 24.56 በመቶ፣ የሶማሌ 11.42 በመቶ፣ የአፋር 1.23 በመቶ፣ የአዲስ አበባ 5.80 በመቶ ነው፡፡
በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማብቂያ ማለትም በ2012 ዓ ም የአገራችን የደን ሽፋን 20 በመቶ እንዲሁም በ2017 ዓ ም ደግሞ ወደ 30 በመቶ ለማድረስ የሚያስችል አገራዊ የደን ዘርፍ ልማት ኘሮግራም በመተግበር ላይ ይገኛል። በዚህም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞች በመልማት ላይ ናቸው። ባለፈው ዓመት የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ጂም ዮንግ ኪም፤ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ተዋናይ እንደሆነች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አነስተኛ የካርቦን ልቀት ያላት ከመሆኑ ባሻገር እያካሄደች ያለችው ከአካባቢ ተስማሚ የሃይል አቅርቦት ጎን ለጎን ከፍተኛ የሆነ የደን ልማት በማካሄድ ላይ ነች።
ይሁንና አገራችን ለችግኝ ተከላ የሰጠችውን ትኩረት ያክል በችግኝ እንክብካቤ ላይ ትኩረት ተደርጓል የሚል ዕምነት የለኝም። አዎ ችግኞችን ተከላ በዘመቻ እንዳካሄድነው ሁሉ ችግኞችንም እንክብካቤ በዘመቻ ይከናወን ማለቴ አይደለም። ይህ ሊተገበርም አይቻልም። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች “በርካታ ችግኝ በመትከል ብቻ ለውጥ አይመጣም። ይልቁንም የተከልናቸውን ችግኞች ሁኔታ በቅርብ መከታተል ይገባል” ይላሉ። በዓመት የተወሰነች ገንዘብ በማዋጣት ችግኞችን የሚንከባከቡ ሰራተኞችን በመቅጠር በየዓመቱ ለምንተክላቸው ችግኞች መንከባከብ ይገባል። ከአንዳንድ መረጃዎች እንደተረዳሁት መንግስት በየዓመቱ ለሚተከሉ ችግኞች ሰራተኞች ቀጥሮ በማስጠበቅ ላይ ነው። ይሁንና እነዚህ አካሎች ችግኞችን ከእንሰሳት ንክኪ ይከላከሉ እንደሆን እንጂ ችግኞች የሚያስፈልጋቸውን ግብዓት በማቅረብ እንክብካቤ አያደርጉም።
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን ለማስፈፀም ከፍተኛ ገንዘብ ከማስፈለጉ በተጨማሪ ህብረተሰቡ ስለአካባቢ ጥበቃ ስራ ተገቢው ግንዛቤን እንዲኖረው ማድረግ ተገቢ ነው። አሁን ላይ የኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ለአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተዋል። አገራችን ለአየር መበከል ያላት አስተዋጽዖ እጅግ አነስተኛ ቢሆንም በአየር መለወጥ ሳቢያ የሚደርስባት ጉዳት ግን ከፍተኛ ነው። ለአብነት እንኳን ከ2008 ዓ ም ጀምሮ በከፍተኛ ድርቅ በመጠቃት ላይ ነች።
መንግስት የአየር መበከልን ለመከላከል ከሚያደርገው ጎን ለጎን ለአካባቢ ብክለት ዋንኛ ምክንያት ናቸው ተብለው የተለዩ ምክንያቶችንም ለመቀነስ በመስራት ላይ ነው። ለአብነት ለአካባቢ ብክነት ምክንያት ተደርገው ከሚወሰዱ ነገሮች መካከል አንዱ የፕላስቲክ ምርት ነው። ፕላስቲክ የመሬትን ለምነት በከፍተኛ ሁኔታ ከሚቀንሱ ነገሮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነገር ነው። በ2008 ዓ ም የተካሄደ ጥናት እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ብቻ ካሉ 21 ፕላስቲክ ማምረቻ ተቋማት መካከል 14ቱ ውፍረቱ 0.3 ሚ.ሜ እና ከዚያ በታች የሆነ ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ ምክንያት የሆኑ የፕላስቲክ ከረጢቶችን ከህግ አግባብ ውጪ የሚያመርቱ እንደነበር አንድ ጥናት አመልክቶ ነበር። መንግስት በቀጣይ ለአካባቢ ብክለት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያላቸውን ደረቅም ሆነ ፍሳሽ በካይ ነገሮች መከላከል አለባቸው።
አገራችን በቅርቡ በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት የኢንዱስትሪ አብዮት በማቀጣጠል ላይ ነች። በእርግጥ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ለአካባቢ ጥበቃ ምቹ ተደርገው የሚገነቡ ናቸው። ይሁንና ከዚህ ቀደም የተገነቡ ፋብሪካዎችን መንግስት በቅርበት መከታተል ይኖርበታል። መንግስት የአበባ እርሻ ልማት ድርጅቶች፣ የቆዳ፣ ጨርቃ ጨርቅ፣ ቀለም፣ ወዘተ ፋብሪካዎችን የምርት ሂደታቸውን በቅርበት መከታተል ይኖርበታል።
ከትራንስፖርት ጋር ተያይዞ የምናያቸው ችግሮች በደንብ መታየት አለባቸው። አንዳንድ ተሽከርካሪዎች የሚያወጧቸው የጭስ መጠን እጅግ አስገራሚ ነው። እንደሚመስለኝ በኢትዮጵያ ለተሽከርካሪዎች የአገልግሎት ጊዜ የተቀመጠ አይመስለኝም። በአገራችን የምንመለከታቸው አንዳንድ ተሽከርካሪዎች በየትኛውም አገር ያሉ አይመስለኝም። በአካባቢያችን ላይ እያስከተሉ ያሉት ብክለት የሚታይ ሆኖ ሳለ በዚህ በተጨናነቀ ጎዳና ላይ እንመለከታቸዋለን። በዚህ ረገድ መንግስት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር የሚገቡበትን የምርት ዘመን ከመወሰን ባለፈ አገር ውስጥ ያሉትስ ምን ያህል እድሜ አላቸው ሊል ይገባል።
ለሌላው ተለያዩ ምክንያቶች ከህክምና እስከ ግብርና ከውጭ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ኬሚካሎች ሌላው የብክለት ምንጭ ናቸው። እነዚህን ኬሚካሎች በተገቢው ሁኔታ ያለመጠቀም ወይም በተሳሳተ ሁኔታ ያለመያዝ የሚያስከትሉት ጉዳት ከጥቅማቸው ያለተናነሰ በመሆኑ ባለሙያዎች ተገቢውን ቁጥጥር ሊያደርጉ ይገባል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ Global Green Growth የተሰኘው ተቋም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ሮበርት ሙኪዛም “ኢትዮጵያ በአፍሪካ ውስጥ ብክለትን ለመቀነስ ያሳየችውን ያህል ቁርጠኝነት ማንም አገር አላሳየም” ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በየክረምቱ በአስርት ቢሊዮን የሚቆጠር ችግኞችን በአገር ደረጃ ለመትከል እያደረግን ያለነውን ርብርብ ችግኞችን በመንከባከብ ውጤታማ ማድረግ ይኖርብናል። ችግኞችን መንከባከብ እንደመትከል ቀላል አይደለም። ችግኞችን መንከባከብ እንደመትከል በዘመቻ የሚፈጸም አይደለም። ነገር ግን ችግኞችን ለመንከባከብ ቀላሉ መንገድ ለመትከል የተረባረብን ዜጎች ሁሉ ቢቻል በየወሩ ካልሆነ በየዓመቱ የተወሰነ ገንዘብ ብናዋጣ ችግኞችን በቅርበት የሚንከባከቡ ሰራተኞችን በቋሚነት መቅጠር ይቻላል። “ሃምሳ ሎሚ እንደሚባለው የሚከብድ አይመስለኝም። ይህን በማድረጋችንም አሁን ማጽደቅ ከቻልነው ችግኞች ቁጥር በላይ በማጽደቅ የአገራችንን የደን ሽፋን በአጭር ጊዜ ማሳደግ ይቻላል። ለዜጎችም ተጨማሪ የስራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበት ዘርፍ ይሆናል።