Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ጃፓን የዲፕሎማሲያዊ ግንኙታቸውን ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገለፁ

0 363

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና ጃፓን ረዥም ጊዜያት ያስቆጠረ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙታቸውን ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ አስታወቁ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጃፓን አቻቸው  ታሮ ካኖ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም በአካባቢዊና አለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የጃፓን የውጭ ጉዳይ  ሚኒስትር ታሮ ካኖ ኢትዮጵያ በአህጉሪቱ ካላት ስፍራ አንጻር ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረግ ግንኙነት ለአፍሪካ ጃፓን ትብብር ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

ጃፓን ለኢትዮጵያ መሰረተ ልማት ግንባታ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ የመቀጠል ፍላጎት እንዳላት የገፁት ሚኒስትሩ ከጅማ እስከ ጭዳ ያለውን መንገድ ለማሻሻል የ1ዐዐ ሚሊየን ዶላር የፋይናንስ ድጋፍ ታደርጋለችም ብለዋል፡፡

የጃፓኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስር ታሮ ካኖ የጃፓን አፍሪካ ግንኙነትን ለማጎልበት ጃፓን በአዲስ አበባ ጽህፈት ቤት እንደምትከፍትና ኢትዮጵያ ኢጋድ በደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚያደርጉትን ጥረት ሃገራቸው እንደምትደግፍም ተናግረዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ታሮ ካኖ፡፡

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት የበለጠ እንዲጠነክር እንዲሁም በአካባቢውና አለምአቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ከጃፓን ጋር የመስራት ፍላጎት እንዳላት ማረጋገጣቸውን የተናገሩት ውይይቱን የተከታተሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም ናቸው፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy