Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ አገር ቱሪስቶች እንደሚጎበኙ ይጠበቃል

0 363

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በዘንድሮው አውሮፓውያን ዓመት ብቻ ኢትዮዽያ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ የውጭ አገር ቱሪስቶች እንደሚጎበኙ ይጠበቃል ሲል አንድ የእንግሊዝ ተቋም የትንበያሪፖርት አቀረበ።

በተቋማት ላይ ክትትል በማድረግ በየጊዜው ሪፖርት የሚያወጣው ፕራይስ ወተር ሃውስ ኩፐርስ የተሰኘ የእንግሊዝ ተቋምን ጠቅሶ የቻይና ዜና አገልገሎት /ሽንዋ/ ትናንት እንደዘገበው የጎብኚው ቁጥር በ5.7 በመቶ እንደሚያድግ ሪፖርቱ ይገልጻል።

ኢትዮዽያና ባለፈው አውሮፓውያን ዓመት ከጎበኙ ቱሪስት ቁጥርበ831ሺሀ 132 የሚልቅ ጉብኚ በዚህ አመት ወደአገሪቱ ይመጣል።

አገሪቱን ለመጎብኘት እኤአ በ2016   የተመዘገቡት የቱሪስቶች ቁጥር ከ868 ሺ 780 እንደሚበልጥ የቻይናው ዜና አግልገሎት ሪፖርቱን ጠቅሶ  ሲዘግብ  በተያዘው የአውሮፓውያን  አመት ደግሞ አሃዙ 918 ሺ 010  እንደሚደርስ ጠቁሟል።

የቱሪስ ፍሰቱ  በ5.7 በመቶ ለጎብኚዎቹ ቁጥር ማደግ  ምክንያት ደግሞ በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ መዳረሻዎችን እየከፈተ የሚገኘ  የኢትዮዽያ አየር መንገድ አስተዋፅኦው የላቀ መሆኑንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

የሃገር ውስጥንም ሆነ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች ቁጥርን ለመጨመር የሚያስችሉ መዳረሻዎችን እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ማከናወኑ ለደንበኞች መስተናግዶም ብቃቱን እንደሚያሳድግለት ይጠበቃል ብሏል።

ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ከተገኘ 345 ሚሊዮን ዶላር ብድር ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የቦሌ ዓለም ኣቀፍ የአውሮፕላና መነሐሪያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት አሁን ካለበት 7 ሚሊዮን ደንበኞች የማስተናገድ አቅምን ወደ 22 ሚሊዮን እንደሚያሳድገው ገልጿል።

ሽንዋ በድረ ገፁ እንዳሰፈረው የግንባታ ስራው በ74ሺ ስኩዌር ቦታ ላይ እየተከናወነ ነው።

በተጨማረሪም ኢትዮዽያ አለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉ ሆቴሎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑና ዋና ከተማዋ አዲስ አበባም በኮንፈረንስ ቱሪዝም ረገድ ስሟ እየገነነ መምጣቱንም አክሏል።

እንደ ሪፖርቱ አለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው እንደ ሸራተን፣ ማሪዮትና ራዲሰን ብሉ ሆቴሎች በስራ ላይ ሲሆን ሌሎች አምስት አለም አቀፍ ሆቴሎች ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል።

በ2016 በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በቱሪስት ፍሰቱ ላይ ተፅዕኖውን አሳርፎበት የነበረ መሆኑን ያሰታወሰው  ሪፖርቱ በተያዘው የፈረንጆች አመት ሁኔታው ተሻሽሎ ዘርፉ ውጤታማ እንደሚሆንም ስሌት ማስቀመጡን ዘገባወ አመልከቷል።

ሪፖርቱን መሰረት ያደረገው የⶲንዋ ኔት ድረ ገፅ እኤአ በ2016 ሃገሪቷን ለመጎብኘት የተመዘገቡት ቱሪስቶች ቁጥር ከ868 ሺ 780 እንደሚልቁና በተያዘው የፈረንጆች አመት ደግሞ 918 ሺ 010 ሊደርሱ እንደሚችሉ ዘግቧል።

በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ መዳረሻዎችን እየከፈተ የሚገኘው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ለጎብኚዎቹ ቁጥር ማደግ አስተዋፅኦው የላቀ መሆኑንም ሪፖርቱ አመልክቷል።

የሃገር ውስጥንም ሆነ የውጭ ሃገር ቱሪስቶች ቁጥርን ለመጨመር የሚያስችሉ መዳረሻዎችን እያሰፋ የሚገኘው አየር መንገዱ በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ፕሮጀክት እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል።

ይህም የደንበኞች ማስተናገድ ብቃቱን እንደሚያሳድግለት ይጠበቃል።

ከቻይናው ኤግዚም ባንክ ከተገኘ 345 ሚሊዮን ዶላር ብድር ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው የቦሌ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ደንበኞችን የማስተናገድ አቅሙን አሁን ካለበት 7 ሚሊዮን ወደ 22 ሚሊዮን እንደሚያሳድገው ጠቁሟል።

የግንባታ ስራው በ74ሺ ስኩዌር ቦታ ላይ እየተከናወነ እንደሆነም አስታውቋል።

በኢትዮዽያ አለም አቀፍ ደረጃን ያሟሉ ሆቴሎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑና ዋና ከተማዋ አዲስ አበባም በኮንፈረንስ ቱሪዝም ረገድ ስሟ እየገነነ መምጣቱም ገልጿል።

እንደ ሪፖርቱ አለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው እንደ ሸራተን፣ ማሪዮትና ራዲሰን ብሉ ሆቴሎች በተግባር ላይ የሚገኙ ሲሆን ሌሎች አምስት አለም አቀፍ ሆቴሎች ግንባታቸው እየተፋጠነ ይገኛል።

በ2016 በሃገሪቱ ተከስቶ የነበረው አለመረጋጋት በቱሪስት ፍሰቱ ላይ ተፅዕኖውን ያሳረፈ  የእንደነበረ አስታውሶ በተያዘው የፈረንጆች አመት ሁኔታው ተሻሽሎ ዘርፉ ውጤታማ እንደሚሆን ስሌቱንም አስቀምጧል ብሏል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy