የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በ በፊንፊኔ እያካሄደ መሆኑ ተነግሯል።
ማዕከላዊ ኮሚቴው በእስካሁን የስብሰባ ቆይታው በ2009 ዓ.ም የፖለቲካና የድርጅት ስራዎች አፈፃፀም ላይ በዝርዝር መክሯል።
ኦህዴድ የተጠናቀቀው በጀት ዓመት ባካሄደው ጥልቅ ተሃድሶ ያሉትን ጥንካሬዎችና ድክመቶች ከሕዝብ ጋር በመሆን የለየበት መሆኑም ተነስቷል፡፡
የድርጅቱ አባላትና የክልሉ ሕዝቦች በተሳተፉበት የጥልቅ ተሃድሶ የተቀመጡ ውሳኔዎች በተገቢው መንገድ እየተፈፀሙ መሆናቸው ተገምግሟል።
ሆኖም በቀሪ ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የክልሉን ሕዝብ በማሳተፍ፥ ተሃድሶውን በተግባር ተፈፃሚ ለማድረግ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ነው የተገለጸው፡፡
የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ በስብሰባው በ2010 የፓለቲካና የድርጅት ስራዎች እቅድ ላይ ከመከረ በኋላ አቅጣጫዎችን እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል፡፡