Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ለኪራይ ሰብሳቢነትና ለሙስና ትግሉ ስኬት ..

0 345

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ለኪራይ ሰብሳቢነትና ለሙስና ትግሉ ስኬት …

አባ መላኩ

ኢትዮጵያ ዛሬ በህገ መንግሥት የምትመራ አገር ሆናለች። ሠላምና ዴሞክራሲ የተረጋገጠባት አገር ናት። በፍርሃት የሚርዱባት አገር ሳትሆን ዜጎች መብቶቻቸው ተከብሮላቸው በነጻነት የሚንቀሳቀሱባት ምድር ነች። ፓርቲዎች በነጻነት ተደራጅተው የመሰላቸውን ሃሳብ የሚያራምዱበት፤ ሁሉም የመሰለውን የሚመርጥበት ሁኔታ አለ። ዛሬ ኃይማኖት፣ ባህል፣ ማንነት፣ ጾታ፣ እኩልነት የተረጋገጡባት አገር ሆናለች – ኢትዮጵያ።

አዎ! አዲስቷ ኢትዮጵያ ተመስርታለችአገሪቱ የመልካም አስተዳደር ጠንቅ የሆኑትን የኪራይ ሰብሳቢዎች ምንጮችን ለይቶ ለመጠራረግ የፀና አቋም ይዛለች። ኪራይ ሰብሳቢዎችን ብቻ ሳይሆን ትምክህትንና ጠባብነትንም ለመታገል አቋም ተይዟል። አገሪቱንም ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ ቀጣይ ትግል እየተደረገ ይገኛል።

ይህ ጉዞ ያልጣማቸው ኪራይ ሰብሳቢዎችና የውጭ ኃይሎች ሂደቱን ለማደናቀፍ ያልፈነቀሉት ድንጋይ የለም። የነዚህ ዓላማም ህዝቡ አንድነትን አጠናክሮ በልማቱ ላይ የጀመረውን የህዳሴ ጉዞ እንዳይቀጥልበት ማደናቀፍ ነው። ይሁን እንጂ ለፀረ ልማትና ፀረ ሠላምና ፀረ ዴሞክራሲ ኃይሎች የትም ቢሆን ይፋለማቸዋል። ልማታዊ ባለሃብቶችም አገር ለመለወጥ ከሚያደርጉት ርብርቦሽ ጎን ለጎን ችግሮችን በመጋፈጥ ረገድ ትግላቸውን አጠናክረው ሊቀጥሉበት ይገባል።

 

በመጀመሪያው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈጻጸም አበረታች እንደነበር ይታወሳል። የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጅማሮም በተለያዩ ዘርፎች አበረታች የአፈጻጸም ስኬቶች ታይተዋል። ይደረስበታል ተብሎ የተያዘውን ዕቅድ ዳር ማድረስ የሚያስችል መሠረት ጥሏል ማለት ይቻላል።

 

ኢትዮጵያ ከድህነት ማጥ ወጥታ ዘላቂና ቀጣይነት ያለውን የምጣኔ ሀብት ዕድገት በማስመዝገብ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ መሰለፍ ትችል ዘንድ የግብርና መር የኢኮኖሚ ሥርዓቷን ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር መሠረት ይጥላል በሚል የተነደፈውና ላለፉት ዓመታት ሲተገበር የቆየው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ በስኬት ጎዳና ላይ ቢሆንም ጉዞው አልጋ በአልጋ ነው ማለት አይቻልም። በርካታ ተግዳራቶች ቢያጋጥሙም በየደረጃው  መፍትሄ እየተሰጣቸው ይገኛሉ።

 

ከእነዚህ ዐበይት  ችግሮች መካከል ኪራይ ሰብሳቢነትና መገለጫው የሆነው ሙስና በዋናነት ይጠቀሳሉ። ለዚህም ነው መንግሥት  መሰናክሎችን እየለየ የመፍትሄ ሃሳቦችንና የአፈታት  ሥልቶችንና አቅጣጫዎችን  እያስቀመጥ ይገኛል። ከሰሞኑ እየተወሰደ ያለው ርምጃ ጥሩ ማሣያ ነው። ይህም ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ይጠበቃል።  

 

ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙሰኝነት በተንሰራፋበት ሥርዓት መልካም አስተዳደር ሊሰፍን አይችልም። መልካም አስተዳደር ከሌለ ደግሞ  ሠላም፣ ልማትና ዴሞክራሲ ይረጋገጣሉ ተብሎ አይታሰብም። ሦስቱም የማይነጣጠሉ ወሣኝ ጉዳዮ ናቸው። መልካም አስተዳደር በሌለበት ሠላምና ዴሞክራሲ እውን ሊሆኑ አይችሉም።

 

የእያንዳንዱ ዜጋ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ  መብት፤ የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች እኩልነት ባልተረጋገጠበትና የቡድን መብት ባልተከበረበት ሁኔታ በምጣኔ ሀብት የበለፀገች አገር ለመገንባት የሚደረገው ጥረት በርካታ መሰናክሎች እንደሚያጋጥሙት የአደባባይ ምስጢር ነው።

 

በተለይ እንደ ኢትዮጵያ በርካታ ብሔሮች፣ ብሐረሰቦችና ሕዝቦች ባሉባቸው አገራት ሠላም፣ ዴሞክራሲና ልማት የህልውና ጉዳይ እንደሚሆን በኢሕአዴግ የሚመራው መንግሥት ይፋ ካደረገና ይህንኑ ያገናዘበ እንቅስቃሴ  ማድረግ ከጀመረ ሁለት አሥርት ዓመታት አልፈዋል።  

 


ለአገሪቱ የዕድገት ጎዳና ዋናው መሰናክል ተብሎ የተለየው ኪራይ ሰብሳቢነትን መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀውና ራሱን ከእንደዚያ ዓይነት አፀያፊ ድርጊት አርቆ በድርጊቱ የሚሳተፉትን ግለሰቦች ላይ በሚወሰድ ርምጃ የድርሻውን እንዲወጣ ለማድረግ በተለያየ ጊዜ ቀላል የማይባሉ የአስተምህሮ ተግባራት ተከናውነዋል።

 

ኅብረተሰቡ በሙሉ ኃይሉ እንዲታገል አመቺ ሁኔታ መፍጠር በማስፈለጉ ጉዳዩን በዋናነት የሚመሩ ተቋማት በየደረጃው ተቋቁመው አቅም በፈቀደ መጠን በበቂ የሰው ኃይል የማደራጀት ሥራ ተከናውኗል። ተቋማቱ የኅብረተሰቡን ትግልና የሙስናና የኪራይ ሰብሳቢነትን ወንጀሎች በመከታተል ይመረምራሉ፣ ያጠናሉ ከዚያም እንዳስፈላጊነቱ ወንጀለኞች  በሕግ  እንዲጠየቁ ያደርጋሉ።


በየደረጃው የተቋቋሙት የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ተቋማት የግዥ አፈጻፀምን፣ ብልሹ አሠራሮችን፣ ትላልቅ የልማት ተቋማት የገንዘብና የሰው ኃይል አጠቃቀምንና የመሬት አስተዳደርን በተገቢው መልክ በመከታተል መንግሥት በየደረጃው የሚመድበው በጀት ለተመደበለት ዓላማ ብቻ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል የክትትል፣ የምርመራና በህግ ተጠያቂ የማድረግ  ሥልጣን  ኖሯቸው እንዲቋቋሙ ተደርጓል። በዚህ መልክ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያሉትንም ሆነ በተለያየ  የግል ሥራ ተሰማርተው ያለአግባብ ለመበልፀግ ሲሉ ህገ ወጥ አካሄድን በመረጡ ተጠርጣሪ ባለሃብቶች ላይ ክስ ለመመሥረት በሂደት ላይ ይገኛሉ።

 

የኪራይ ሰብሳቢዎችና ሙሰኞች ተግባር ክትትልና ምርመራ ከማድረግ  ጎን ለጎን አስከፊነቱን በኅብረተሰቡ ዘንድ የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር በመላው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶ  ለተሰነቀው የጋራ ራዕይ  መሰናክል መሆኑን ሁሉም አውቆ የበኩሉን ድርሻ በመፈፀም  መልካም መፃኢንና  የጋራ ብልጽግናን ለማፋጠን በእውቀት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ ነው።


ቀንደኛ ጠላታችን ድህነት መሆኑ ላይ በብዙዎች ዘንድ  መግባባት ላይ ተደርሷል። ድህነትን ለመቅረፍ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመግታት ለድህነት መንሰራፋት ኪራይ ሰብሳቢነት የሚኖረው ድርሻ ቀላል አለመሆኑን በተገቢው መልክ መግባባት መፍጠር ሙስናን ለመሸከም የማይችል ኅብረተሰብ ለማፍራት ያግዛል በሚል እምነት መንግሥት እየወሰደ ያለው ቆራጥ ርምጃ ሙሰኝነትን ለመዋጋት ያለውን ቁርጠኝነት በግላጭ አሳይቷል። የተጀመረውን ተስፋ ዳር ለማድረስና የለማች አዲስቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙሰኝነት ላይ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ  ከመንግሥት ጎን ተሰልፎ መዋጋት የሚያስችል መግባባት ላይ መድረስና ይህንኑ በቆራጥነት መተግበር ያሻል። 


ኢትዮጵያ ከድህነት ተላቃ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ለመሰለፍ የነደፈቻቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች በመተግበር ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት አበረታች የምጣኔ ሀብት ዕድገት ማስመዝገብ ብትችልም ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙሰኝነት የሥርዓቱ አደጋ ሆነው  ተጋርጠውባታል።  መንግሥት ኅብረተሰቡን  አስተባብሮ አገሪቱ የሰነቀችውን ራዕይ ዳር ለማድረስ  ኪራይ ሰብሳቢዎችንና ሙሰኞችን  በማጋለጥና ለህግ በማቅረብ ረገድ ጠንክሮ እየሰራ ነው።

 

ኪራይ ሰብሳቢዎች በማንኛውም መንገድ ልማታዊ አካሄድንና ልማታዊ ባለሀብትን ለማቀጨጭ ይጥራሉ። የበርካቶችን ዕድል እያጨናገፉ በሃብት ላይ ሃብትን ማካበት ዋና ዓላማቸው በመሆኑ ምንጊዜም አይዘናጉም። በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ሥልቶች እየነደፉ ሥርዓቱን መፈታተናቸው የማይቀር ሃቅ ነው። ስለሆነም ይህንን እንቅስቃሴና የሥልቶች መቀያየር እየተከታተሉ ማምከንን ይጠይቃል።


በሁለቱ ጎራ ያለው ፍትጊያ መቋጫ ማግኘት ሲችል ነው አገሪቱ አሁን እያስመዘገበች ያለችውን ፈጣንና ቀጣይ ልማት እውን በማድረግ ወደ መካከለኛ ኢኮኖሚ መግባት የምትችለው። በልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚና  በኪራይ ሰብሳቢ የፖለቲካ ኢኮኖሚ  መካከል ያለው የከረረ ትግል በልማታዊ ባለሃሀብቱ ድል አድራጊነት ከተጠናቀ የአገሪቱ የልማት ጎዳና ስኬት ይረጋገጣል። 

 

ልማታዊ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ኪራይ ሰብሳቢውን መድፈቅ ካልቻለ ግን አገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅና በዕድገት ጎዳና ለማሰለፍ በሚደረገው ሁለንተናዊ ጥረት ጥላሸት መልበሱ አይቀሬ ነው። የማታ የማታ ደግሞ የበላይነቱ ሥር እየሰደደ የሚሄድ ከሆነ የመልካም አስተዳደር እጦት ወደ ከፋ ደረጃ ይደርሳል፤ ኅብረተሰቡ ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ማግኘት ስለማይችል የታየው የብርሃን ጭላንጭል ፈተና ላይ ይወድቃል።


በተለያየ የመንግሥት የኃላፊነት ቦታ ላይ ሆነው የያዙትን የህዝብ ኃላፊነት ተገቢ ባልሆነ መንገድ  ለግል ጥቅም የሚያውሉ በርካቶች መኖራቸውን የሚያመላክት ሁኔታ ተስተውሏል። ከዚህ በመነሳትም  መንግሥት ሙሰኝነትን በቁርጠኝነት ለመዋጋት የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ ቆይቷል።

 

በቅርቡ በከፍተ ባለሥልጣናትና ከእነሱ ጋር ተያያዥነት በነበራቸው ባለሃብቶችና ደላላዎች ላይ የወሰደ ያለው ርምጃም የዚሁ ትግል አንድ ፈርጅ በመሆኑ የብዙዎችን ፍላጎት የመለሰ ሆኗልከዚያ በፊትም ቢሆን በተለያየ ጊዜ በተለያዩ ደረጃዎች በሚገኙ የምግባር ብልሹነትን ያሳዩና በሙሰኝነት የተጠረጠሩ ግለሰቦች ወደ ህግ በማቅረብ ህጋዊ ርምጃ እንዲወሰድባቸው ተደርጓል።


የተባላሹ አሠራሮችን የመለየትና በተበላሹ አሠራሮች ገብተው የግል ተጠቃሚነታቸውን ለማሳካት የሚንቀሳቀሱ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለሃብቶችና ደላላዎችን በመከታተል፣ በመመርመርና በማጥናት ለህግ ቀርበው ተገቢውን ርምጃ እንዲወሰድባቸው በማድረግ በቢሊዮን የሚቆጠር የአገርና የህዝብ ሀብት ከብክነት የዳነበት አጋጣሚ በርካታ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።

 

መንግሥት ኪራይ ሰብሳቢነትንና ሙስናንና ለመዋጋት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት ዳር ለማድረስ ትግሉ  ህዝቡ በባለቤትነት ሊመራው ይገባል። እስካሁን ያለው ተሳትፎ የበለጠ ተጠናክሮ መጪው ትውልድ በሥነ ምግባርና ሥነ ዜጋ ትምህርት ታንጾ  ሙስናን የማይሸከም ለማድረግ ሁሉም መሠረቶች ሊፈጠሩና ሊጠናከሩ የግድ ይላል።


ኪራይ ሰብሳቢነትን በግላጭ የሚዋጋ፣ ራሱንም ከኪራይ ብሳቢነት የፀዳና ሙሰኝነትን የሚፀየፍ ኅብረተሰብ መፍጠር የልማቱ መቀጠልና አለመቀጠል አንድ ወሣኝ አካል ነው። ይህንን መሠረት ለመፍጠር መንግሥት አመቺ ሁኔታ አዘጋጅቷል። ይህንን አመቺ ሁኔታ በመጠቀም ሁሉም በአንድነት  የተጠናከረ ትግል ማድረግ ይጠበቅበታል።

 

ለኪራይ ሰብሳቢነትና ለሙስና ትግሉ ስኬት ኅብረተሰቡ መገለጫዎቹን ለይቶ ማወቅና በዚያ ልክ መተግበር ይጠበቅበታል፡፡ ከእንደዚህ ዓይነቱ የአገርና የህዝብ ጠንቅ ለመቆጠብና ሌሎችንም  ለመከላከል መሠረታዊ ባሕሪያቱንና የተለያዩ ገጽታዎቹን ጠንቅቆ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ መንግሥት በትምህርት ቤቶች የሥነ ምግባርና የሥነ ዜጋ ትምህርቶች እንዲሰጡ ማድረግ ተገቢነቱ አያጠያይቅም።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy