Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን 49 ቀበሌዎች በኦሮሚያ ስር እንዲተዳደሩ መካለላቸውን የክልሉ መንግስት አስታወቀ

0 885

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን 49 ቀበሌዎች በኦሮሚያ ክልል ስር እንዲካለሉ መደረጉን የክልሉ መንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

በኦሮሚያ እና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መሃል ሲስታዋል የነበረውን ችግር ለመፍታት የወሰን ማካለል ስራ እየተሰራ መሆኑንም የቢሮው ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ አስታውቀዋል።

አቶ አዲሱ እንዳሉት በሁለቱ ክልሎች መካከል ያለው የወሰን ችግር በተለያዩ ጊዜያት ግጭቶችን በማስከተል ለበርካታ ሰዎች ሞትና ለንብረት ውድመት ምክንያት ነበር።

በ1997 የተደረገውን ህዝበ ውሳኔ መሰረት በማድረገግ ከወሰን ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሁለቱም ክልሎች ከስምምነት መድረሳቸውን ያስታወሱት ሃላፊው፥ በስምምነቱ መሰረት ወሰን የማካለሉ ስራን ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት በምስራቅ ሀረርጌ ዞን እስካሀን በተከናወኑ ስራዎች በሁለቱም ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ሲነሳባቸው ከነበሩ 68 ቀበሌዎች 48ቱ በኦሮሚያ ክልል ስር እንዲተዳደሩ የሚያደርግ የማካለል ስራ ተጠናቋል ብለዋል።

የ19 ቀበሌዎችን ወሰን የማካለሉ ስራ አሁንም ቀጥሏል ያሉት አቶ አዲሱ፥ ወሰን የማካለል ስራውም በቁንቢ ወረዳ 3 ቀበሌዎች፣ በአመዩ ወረዳ 4 ቀበሌዎች፣ በሚደጋ ቶላ ወረዳ 2 ቀበሌዎች፣ በጉርሱም ወረዳ 2 ቀበሌዎች፣ በጭናክሰን ወረዳ 2 ቀበሌዎች እንዲሁም በሜታ ወረዳ የሚገኝ 1 ቀበሌ ነው ብለዋል።

ከወሰን ጋር ተያይዞ የሚስተዋለው ግጭት በ1997 ዓ.ም የተካሄደው ህዝበ ውሳኔ ላይ በመመርኮዝ ሰላማዊ እና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በመፍታት ድንበር አካባቢ ያሉ አስተዳደሮች የግጭት እና የሰዎች ህይወት የሚያልፍባቸው ሳይሆን ሰላምና ልማት የሚረጋገጥበት እንዲሁም የህዝቦች ወንድማማችነት የሚመሰረትበት ስፍራ እንዲሆን የኦሮሚያ ክልል መንግስት በሰላም እና በብስለት እንዲሁም ሃላፊነት በተሞላበት መንገድ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ከወሰን ጋር በተያያዘ ከክልሉ አዋሳኝ ከሆኑ ጎረቤት ክልሎች ጋር የሚነሱ ችግሮችን ሰላማዊ እና ህዝብን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ አዲሱ አረጋ አያይዘው ተናግረዋል።

በዚህ መልኩም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል መካከል ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያይዞ ሲስተዋል የነበረ ችግር የወሰን ማካለል ስራ መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።

ከጋምቤላ፣ ከአማራ እና ከደቡብ ክልሎች ጋር ከወሰን ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችንም የክልሉ መንግስት ሰማላዊ በሆነ እና ህዝቡን ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ ለመፍታት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን አቶ አዲሱ ገልጸዋል።FBC

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy