Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በሰበታ ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0 486

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኦሮሚያ የስነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በክልሉ በሙስና የተጠረጠሩ 26 ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ።

የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ አዲሱ አረጋ እንደገለጹት፥ ግለሰቦቹ በሰበታ ከተማ ለተለያዩ ፕሮጀክቶች የተመደበ ሀብትን በመመዝበር፣ የሀሰት የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ እና ደረሰኝ በማዘጋጀት በመስጠት የተጠረጠሩ ናቸው።

በተጨማሪም የይዞታ ማረጋገጫ እና ሀሰተኛ ደረሰኝ በመስጠት እና በመሸጥ፣ የካሳ ክፍያ ለማይገባቸው ክፍያ በመፈፀም እና መቀበልም ተጠርጥረዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በአነስተኛ እና ጥቃቅን በሀሰት በመደራጀት ገንዘብ በመውሰድም ተጠርጥረው ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

ከተጠርጣሪዎች መካከል በሰበታ ከተማ አስተዳደር በከንቲባነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ገዛኸኝ ጎቤ ይገኙበታል።

መሀንዲሶች፣ የቢሮ ሰራተኞች እና ደላሎችም በቁጥጥር ስር ከዋሉት 26 የሙስና ተጠርጣሪዎች መካከል ይገኛሉ ብለዋል አቶ አዲሱ። fbc

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy