በአማራ ክልል የሚገኙ የቱሪዝም መስህቦችን በ2009 በጀት ዓመት ከጎበኙ የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኝዎች ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቋል።
ገቢው ከእቅዱ አንፃር የ72 ነጥብ 8 በመቶ አፈፃፀም እንዳለው ተገልጿል።
በበጀት ዓመቱ በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም መዳረሻዎችን 9 ነጥብ 6 ሚሊየን ሰዎች መጎብኘታቸው ተነግሯል።
የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች ቁጥር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሲሆን ከ1 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል።
ከተለያዩ የውጭ ሀገራት የመጡ ከ105 ሺህ በላይ ጎብኝዎች በክልሉ በነበራቸው ቆይታ 506 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘት መቻሉን ቢሮው ገልጿል።
በዙፋን ካሳሁን