NEWS

የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡

By Admin

August 03, 2017

የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ አካላት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡

ጥልቅ ተሀድሶዉን ተከትሎ ለአለፉት አስር ወራት የኦህዴድ ኢሀዲግን የስራ አፈፃፀም በህዝብ እይታ ለመገምገም በምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ከተማ የተገኙት የዉጭ ጉዳይ ሚንስቴር እና የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጥልቅ ተሀድሶዉን ተከትሎ የተገኙ ዉጤቶች እና ህብረተሰቡ ባነሳቸዉ የአሰራር እንከኖች ዙሪያ ከተሳታፊዎች ጋር መክረዋል፡፡

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች እና ሀሳበች የኦሮምያ ክልላዊ መንግስ እና የምእራብ ሸዋ ዞን መስትዳድር የስራ ሀላፊዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ክቡር ዶር ወርቅነህ ገበየሁም ማጠቃለያ የማጠቃለያ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡