Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ያልተማከለ የስልጣን ክፍፍል ሲባል…

0 611

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ያልተማከለ የስልጣን ክፍፍል ሲባል…

                                                                 ደስታ ኃይሉ

በኢፌዴሪ ህገ መንግስት የክልሎች ያልተማከለ የስልጣን ክፍፍል እውን ሆኗል። ይህም ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው እንደሚያስተዳድሩ፣ ካለቸው ስልጣን ለፌዴራል መንግስቱ ቆርሰው በመስጠት ፌዴራላዊ መንግስቱን መስርተዋል። በህገ መንግስቱ “የክልል ስልጣንና ተግባር” በሚለው አንቀፅ 52 (1) መሰረት በህገ መንግስቱ ለፌዴራሉ መንግሥት በተለይ ወይም ለፌዴራሉ መንግሥትና ለክልሎች በጋራ በግልፅ ያልተሰጠ ስልጣን የክልል ስልጣን እንደሚሆን ተደንግጓል።

ይህም ክልሎች በጋራ ከመሰረቱትና የእርሱ ስልጣን እንዲሆን ለሰጡት ለፌዴራል መንግስት ውጭ ያሉት የስልጣን ክፍሎች ሁሉ የክልሎች መሆኑን የሚያሳይ ነው። በዚህም ክልሎች ባልተማከለ መንገድ ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።

የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን እስከ መገንጠል መብታቸው መጠበቁን፣ እያንዳንዱ ማንነት በቋንቋው የመናገር፣ የመፃፍ፣ ቋንቋውን የማሳደግና ባህሉን የመግለጽ፣ ታሪኩን የመንከባከብ መብት አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም እያንዳንድ ማንነት ራሱን የማስተዳደር ሙሉ መብት የተረጋገጠለት መሆኑ በሕገ መንግሥቱ ተደንግጓል፡፡ ከዚህም ጋር ሴቶች በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ መስኮች ከወንዶች ጋር እኩል መሆናቸውንና ከዚህ በፊት በነበረው ልዩነት ምክንያት የተፈጠረባቸውን ጫና ለመቅረፍ ልዩ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ተደንግጓል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት መሬት የብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የጋራ ሀብት መሆኑን ደንግጓል፡፡

እነዚህ ማንነቶች ራሳቸውን የማልማትና በማያቋርጥ ሁኔታ ኑሯቸውን የማሻሻል መብት እንዳላቸው እንዲሁም አባል የሆኑበትን ማኅበረሰብ በሚመለከቱ የመንግሥት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ላይ ሀሳብ የመስጠት መብት እንዳላቸው በሕገ መንግሥቱ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ እንዲሁም አናሣ ብሔረሰቦች ያለምርጫ በልዩ ሁኔታ የሚወከሉበት ከሃያ የማያንስ መቀመጫዎች በተወካዮች ምክር ቤት እንዲኖራቸው መደንገጉ ድምፃቸው ከፍ ብሎ እንዲሰማ ያስችላል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት ከኃይማኖትና እምነት ጋር በተያያዘ የሕዝብን ደህንነት፣ ሰላም፣ ጤና፣ ትምህርት፣ የሞራል ሁኔታ የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች እና የመንግሥትና ኃይማኖት መለያየት ለማስጠበቅ በሚወጡ ሕጎች ኃይማኖትና እምነትን የመግለፅ መብት እንደሚገደብ ነው፡፡ እንዲሁም ትምህርት ከኃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከትና ከባህላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ምንም እንኳ ኃይማኖቶች ለሠላም፣ ለጤና፣ ለትምህርትና ለሌሎች ደሞክራሲያዊ መብቶች አደጋ እንደማይሆኑ ይታወቃል።

እነዚህ ድንጋጌዎች ተፈላጊ የሆኑበት ምክንያት ኃይማኖትን ሽፋን በማድረግ የእምነት ነፃነትና እኩልነት የሚፃረሩ እንቅስቃሴዎች ስለሚታዩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የእምነት ነፃነትና የኃይማኖት እኩልነት የሚፃረር እንቅስቃሴ በቀጥታ ሌሎች ዴሞክራሲያዊ መብቶችን ስለሚፃረር ነው፡፡ ይህ ፀረ ዴሞክራሲ እንቅስቃሴ ለሕዝብ የሚገደብ መብት አይኖርም የሚለውን የሕዝብ ልዕልና መሠረታዊ አስተሳሰብ ስለሚፃረር ጭምር ነው፡፡ ከእነዚህ ድንጋጌዎች የምንገነዘባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች አሉ፡፡

አንደኛው የሥርዓተ መንግሥት አወቃቀር ማንነቶችን መሠረት ያደረገ መሆኑን ነው፡፡ እያንዳንዱ ማንነት የራስ አስተዳደርን የመመሥረት መብት ተጎናፅፏል፡፡ የማንነት መገለጫ የሆኑት ሁሉም ቋንቋዎች እኩል እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራል ሥርዓት ከሌሎች በርካታ ፌዴሬሽኖች የሚለየው ጉዳይ አወቃቀሩ በማንነቶች ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ማንነቶችን የሚመለከቱ መብቶች ከጅምሩ ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና እንዲያገኙ ማስቻሉ ነው፡፡ ማስቻል ብቻ ሳይሆን በሁሉም አካባቢዎች ዕውን እየሆነ ነው።

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአገራዊ አጀንዳዎች ላይ የመወሰን ሥልጣንና ኃላፊነት እንዲኖራቸው በማድረግ በኢትዮጵያ እድገትና ሥልጣኔ ላይ እንዲረባረቡ የሚያስችላቸው ምህዳር መፍጠርም ያስፈልጋል፡፡ ይህ ዓይነቱ አዲስ ግንኙነት ኢትዮጵያን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል ሰፊ አቅምና ጠንካራ ጉልበት እንዲኖር ያስችላል፡፡ የጋራ አስተዳደር የተፈጠረበት አንዱ መነሻ እምነትም ሁሉም ማንነቶች የኢትዮጵያ ባለቤቶች ለማድረግ ነው፡፡

እንዲሁም ማንነቶች በአካባቢ ጉዳዮችና እነሱን በሚመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ወሳኞቹ እንዲሆኑ ማድረግ አንዱ መሠረታዊ እምነት ነው፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእለት ተእለት አኗኗራቸውንና የወደፊት ሕይወታቸውን በሚወስኑ አጀንዳዎች ላይ የሚወስንላቸው ከላይ የሚጫን ኃይል እንዳይኖር ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

አገሪቱ የምትመራባቸው መሠረታዊ መርሆዎች፣ ፖሊሲዎችና ሕጎች የሚመነጩት የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፍላጎቶችን ለማሟላት በመሆኑ እያንዳንዱ የመንግሥት እንቅስቃሴ ከዚህ አንፃር ይቃኛል፡፡ የመንግሥት ሥልጣን፣ መንግሥት የሚያራምዳቸው እምነቶች፣ የሚከተላቸው መርሆዎችና ፓሊሲዎች ምንጭ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ናቸው፡፡

ህገ መንግሥቱ አገሪቱ ፍትሃዊ የምጣኔ ሀብት ዓላማዎችን ማራመድ እንዳለባት በግልጽ ደንግጓል። ይህንን ዓላማ ለማረጋገጥ መንግሥት ዜጎች በአገሪቱ የሚገኘውን ሀብት በፍትሃዊነት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አሰራር የመቀየስ ኃላፊነት ወድቆበታል።

በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ክልሎች በመንግሥት ልዩ እገዛ ተደርጐላቸው ጭምር የልማቱ ተጠቃሚነታቸው መረጋገጥ እንዳለበትም ህገ መንግሥቱ በማያሻማ መልኩ ደንግጓል። መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብቶችን በሕዝብ ስም በይዞታው ስር በማድረግ ለዜጎች የጋራ ጥቅምና እድገት የማዋል ኃላፊነት እንዳለበትም እንዲሁ።

ከዚህ በተጨማሪ ዜጐች ለልማት መሠረት የሆኑ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶች፣ የምግብ ዋስትና፣ የንፁህ መጠጥ ውኃ፣ የመኖሪያና የማህበራዊ ዋስትና የማግኘት መብት እንዲኖራቸው ደንግጓል። በደርግ ሥርዓት ወቅት ማንኛውም ዜጋ ተገፍፎ የነበረውን የግል ሃብት ባለቤት የመሆን መብት በመሠረቱ ተንዷል። ዛሬ ሁሉም ዜጋ የግል ንብረት ባለቤትነት መብቱ በህገ መንግሥቱ ተረጋግጦለታል።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት ባለፉት ሥርዓቶች ምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ፍትህ ሳያገኙ የቆዩና በዚህም ምክንያት በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝ}ቦች በመንግሥት ልዩ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ዋስትና ሰጥቷል። በዚህ መሠረትም የፌዴራል መንግሥት ፍትሃዊ የልማት እንቅስቃሴ ከማረጋገጥ በተጨማሪ፤ በልማት ወደ ኋላ የቀሩ ሕዝቦች መላ አቅማቸውን አሟጠው እንዲጠቀሙ ለማስቻል ልዩ ድጋፍ እየሰጣቸው ይገኛል። ይህ እንዲሆንም የፈቀዱት ክልሎች ናቸው። ክልሎች ራሳቸውን በራሳቸው ከማስተዳደር ባለፈ፤ ለፌዴራል መንግስቱ ከራሳቸው ስልጣን ቆርሰው በሰጡት ስልጣን ተጠቃሚ መሂናቸውን የሚያረጋግጥ ነው።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy