Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ቀጣዩ ትኩረት – መልካም አስተዳደርን ማስፈን

0 257

Get real time updates directly on you device, subscribe now.


 

ቀጣዩ ትኩረት – መልካም አስተዳደርን ማስፈን

 

ወንድይራድ ተስፋዬ

 

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እየገለበተ የመጣበት ሁኔታ ቢኖርም ይህንን በተገቢው መንገድ የመገንዘብ ችግር አሁን ላይ መንፀባረቁ አልቀረም፡፡ ዴሞክራሲያዊ አሠራርን የኢ ዴሞክራሲያዊ ካባ ደርበው የሚንቀሳቀሱት ተቃዋሚዎች ይህ በህዝቡ የማይደገፍ እኩይ ሴራቸው መሆኑን መገንዘብ ይገባቸዋል። ምክንያቱም ህዝብን እንደ ህዝብ የሚንቅ ማንኛውም አካል የመጨረሻ ዕጣ ፈንታው ተተፍቶ መወርወሩ አይቀርምና ነው። እዚህ ላይ አንድ እውነታን ማንሳት ፈቀድኩ። ይኸውም መልካም አስተዳደር የህዝቡ ቀጥተኛ ተሳትፎ ካልታከለበት በመንግሥት ጥረት ብቻ ተግባራዊ ሊሆን የማይችል መሆኑ ነው። ማንኛውም ህዝብ ያልተሳተፈበት ጉዳይ ተፈፃሚ ሊሆን አይችልምና።

 

በመሆኑም በመንግሥት በኩል መልካም አስተዳደርን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉና በሂደት የሚከናወኑት ቁርጠኛ ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው መላው ህዝብም ዛሬም እንደ ትናንቱ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይኖርበታል። በተለይም ቁልፍ የዴሞክራሲ ማስፈኛ ተቋማት በሚባሉት እንደ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ዓይነቶችን በአግባቡ በመጠቀምና የሚፈጠሩ ችግሮችን ተከታትሎ በማሳወቅ ለመልካም አስተዳደር እመርታ መትጋት ከማንኛውም ዜጋ የሚጠበቅ ተግባር ነው።

 

መንግሥት ምንም እንኳን ግዴታው ቢሆንም ህገ መንግሥቱ በሚያዘው መሠረት ብሎም ራሱም ለዴሞክራሲ ሥር መስደድ ካለው ቀናዒ ፍላጎት በመነሳት፤ መልካም አስተዳደርን ለማስፈንና የዜጎች አቤቱታ የሚደመጥበት እንዲሁም ተገቢው ምላሽ የሚሰጥበት የእንባ ጠባቂ ተቋምን አቋቁሟል።

ለዴሞክራሲው ግንባታ እውን መሆንና ላሳየው የማይናወጥ ቁርጠኝነት “ጎሽ” ሊባል ይገባል እንጂ፤ ያለ አንዳች ማስረጃ በመንግሥትና በተቋሙ ላይ በደፈና ጥላቻ እየታገዙ የውርጅብኝ መዓት ማውረድ ተገቢ አይሆንም። ክንዋኔዎችን በአንክሮና በሰከነ አዕምሮ ከሚያይ ተፎካካሪ ፓርቲም የሚጠበቅ አይሆንም። ከዚህ በፊት በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ደጋግሜ አስተሳሰቤን ገልጫለሁ። ዛሬም ይኸው እደግማለሁ። የሚሞግተኝ ካለም ተቀብዬ አስተናግዳለሁ።

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የዜጎችን አስተዳደራዊ በደል ተገቢው ምላሽ እንዲያገኝ በርካታ ሥራዎችን በማከናወን ውጤት እያስመዘገበ መሆኑ ይታወቃል። በስሜት ብቻ እየተገፋፉ የተቋሙን ስም ለማጥፋት መሯሯጥ እንዲሁም መንግሥት በዘርፉ እያደረገ ያለውን ጥረት በፀረ ዴሞክራሲያዊነት ታውሮ ላለመቀበልና ለማጣጣል መሞከር “ዓይናችሁን በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የለውም። ዛሬም ይህንኑ እደግማለሁ።

 

ራሱ ተቃዋሚ ነኝ ባዩ አካልም ቢሆን አመለካከቱ ገንቢና ዴሞክራሲያዊ ባለመሆኑ በእንዲህ ዓይነቱ ጭፍን እሳቤ ጉዞው ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ሂደቱ አሜኬላ እሾህ መሆኑ አይቀርም። መልካም አስተዳደር የሚታሰበው ሥርዓቱ ተግባሩን ለማከናወን ካለው በጎ ምልከታ አኳያ መሆኑ እርግጥ ነው። ታዲያ የአገራችን ፖለቲካዊ ሥርዓትም መልካም አስተዳደርን በሂደት ለመፈፀም ቁርጠኝነት ያለው ብቻ ሳይሆን፤ መልካምና የተመቻቸ ምህዳር ጭምርም የነገሰበት ነው። ለምን ቢባል ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ ሥልጣን የህዝብና የህዝብ ብቻ መሆኑን በግልፅ በማስቀመጡ ነው። ሥልጣን የተገልጋዩ ህዝብ መሆኑ ደግሞ ለመልካም አስተዳደር እመርታ የራሱ ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚካድ አይደለም።

 

ማንኛውም የዚህ ፅሑፍ አንባቢ እንደሚገነዘበው መልካም አስተዳደር የተግባር እንጂ የንድፈ ሐሳብ ጉዳይ አይደለም። ቀደም ሲል ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ተግባሩ ከዜጎች የዕለት ተዕለት የኑሮ ሁኔታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ በመሆኑ፤ በአተገባበሩ ላይ የሥልጣኑ ባለቤት የሆነው ህዝብም ቀጥተኛ ተሳታፊ መሆን አለበት። ህዝቡ በህገ መንግሥቱ የተጎናፀፈውን ሥልጣን በአግባቡ እንዲጠቀምበት ዕድል ይፈጥራል።

 

ታዲያ የአገራችን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ይህ ሁኔታ እንዲተገበር በርካታ ተግባራትን አከናውኗል። እያከናወነም ይገኛል። ቀደም ሲል የጠቀስኩት የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ችግሮችን እየተከተታተሉ በማረም ለመልካም አስተዳደር ግንባታው የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ከተቋቋሙት ገለልተኛ አካላት ውስጥ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ህገ መንግሥታዊ ሥርዓቱ እነዚህ አካላት እንዲቋቋሙ በአዋጅ ከማፅደቅ ጀምሮ ተግባራቸውንም የመልካም አስተዳደር እመርታን በሚያረጋግጥ አኳኋን እንዲፈፅሙ እስከ ማድረግ ድረስ አመቺ የሆኑ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።

 

እነዚህ ገለልተኛ አካላት ህዝቡ በህገ መንግሥቱ ላይ የተቀመጡለት መሠረታዊ መብቶቹ ተግባራዊ መሆናቸውን ያረጋግጣሉ። እስካሁንም ድረስ በርካታ ህዝባዊ ጉዳዮችን በመመልከት የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት እየተወጡ ነው – አቅም በፈቀደ መጠን።

 

የመልካም አስተዳደር ሥራ በርካታ ዓመታትን የሚጠብቅ ከመሆኑ በላይ አገራችን ካለባት የማስፈፀም አቅም ውስንነት አኳያም ተያይዞ የሚታይ ነው። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ያለው የመልካም አስተዳደር ትግበራ አፈፃፀም የአቅም ውስንነትን ተሻግሮ መሻሻል እያሳየ ነው።

ይህ ማለት ግን ፈፅሞ የመልካም አስተዳደር ችግር በአገሪቱ ውስጥ የለም ማለት አይደለም። ሆኖም በአስቸኳይ መፈታት ያለባቸው ችግሮች በአፋጣኝ መፍትሄ እየተሰጣቸው ነው። ሌሎችም እየታዩ በሂደት ምላሽ ያገኛሉ። የጊዜ ጉዳይ እንጂ ማንኛውም የመልካም አስተዳደር ችግር በሂደት የሚስተካከል ይሆናል።  

 

ሆኖም እንደ ተቃዋሚዎቹ ሁሉንም ነገር የመደፍጠጥ አባዜ ‘ምንም አልተሰራም’ የሚል ዲስኩር ዛሬ ላይ ተቀባይነት የለውም። ምክንያቱም በተጨባጭ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ህያው አብነቶች ናቸውና። ተቃዋሚ ተብዬዎች በተለያዩ ህጋዊ አግባቦች አለመሟላት ምክንያት ምላሽ ያልተሰጠውን አንድ ነጠላ ጉዳይ በመምዘዝ እንዲሁም “የአይጥ ምስክር ድንቢጥ” እንዲሉ እነ ሂዩማን ራይትስ ዎችን የመሳሰሉ በክቡሩ የሰው ልጅ ስም የሚነግዱ አክራሪ ኒዩ ሊበራሎችን በመጥቀስ የተቋማቱን መልካም የሥራ ውጤቶች ገደል ለመክተት ይጥራሉ።

 

ይህ ደግሞ እውነታውን ለሚያውቀው ህዝብ አሁንም ቢሆን እነዚህ ወገኖች ካለፈው ድርጊታቸው አለመማራቸውን የሚያረጋግጥ እውነታ ነው። በተቃውሞው ጎራ የተሰለፉ ተቃዋሚዎች አንዳንዴም ቢሆን የተከናወኑ መልካም ተግባራትን ዓይናቸውን ገልጠው ቢመለከቱ መልካም ይመስለኛል። የተቃዋሚነት ወግና ባህል ይኸው ነውና። በመሆኑም የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚ የሆነውና የሥልጣን ባለቤትነቱን ያረጋገጠው ህዝብ፤ ሥልጣኑ በእርሱ እጅ መሆኑን ዛሬም ቢሆን ነገ አምነው መቀበል ይኖርባቸዋል።

እነዚህ ወገኖች የመልካም አስተዳደር አስፈፃሚ የሆኑትን የሲቪል ሰርቪሱን አወቃቀርና አሠራር እንዲሁም የዳኝነት ሥርዓቱን ለመኮነንም ተወዳዳሪ አልተገኘላቸውም፤ ያለ አንዳች የነጠረ ፖሊሲና ስትራቴጂ። ግና በመጀመሪያ ስለ እነዚህ ጉዳዩች በቂ ግንዛቤ መያዝ ያስፈልጋል። ‘አሁን ያሉበትስ ደረጃ ምንድው?’ ብሎ መጠየቅም የአባት ነው። በማያውቁት ጉዳይ ውስጥ ገብቶ መፈትፈት ግን ግምት ይጥላል። ትናንትም ያልኩት ይህንኑ ነው፤ ዛሬም ይኸው ደገምከ።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy