Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

አላባራ ያለው የቢንያም ከበደ (የኢትዮዽያ ፈርስቱ) ሟርት እና አዲሲቷ ኢትዮዽያን እና ስርዓቱን ምክንያት እየፈለገ የማጠልሸት ዘመቻው።

2 427

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

አላባራ ያለው የቢንያም ከበደ (የኢትዮዽያ ፈርስቱ) ሟርት እና
አዲሲቷ ኢትዮዽያን እና ስርዓቱን ምክንያት እየፈለገ የማጠልሸት ዘመቻው።
እያንዳንዱን ድንገተኛ አደጋም ሆነ የስርዓቱን እንቅስቃሴ እንዳሻው እያወላግደ እና ያለስሙ ስም እየሰጠ መዓት ማውራት የዕለት ተዕለት ሞያው አድርጎታል። በሶስት ስርዓቶች ሲከመር የኖረ እና በዚህ ስርዓት መፍትሄ እያገኘ የነበረ የቆሻሻ ክምር ፣ የመፍትሄው ስራ ከመገባደዱ ጥቂት ቀድሞ የመደርመስ ኣደጋ ቢደርስበት ፣ ተቆጥሮ የማያልቅ መልካም ስራ ለውድ ሃገራቸው ያበረከቱትን የከተማይቱ ከንቲባ ወደ ወህኒ ሊጥልለት የሚያበቃ ምክንያት አድርጎ ሊጠቀምበት ተራወጠ። ተሳቀበት እና ታለፈ። በቅርቡ የኢትዮዽያን ሚለንየም አስረኛ አመት ደመቅ ባለ ሁኔታ ለማክበር እና ፤ ይህን ታታሪ እና በድንቅ ሁኔታ ሃገሩን በፍጥነት እየለወጥ ያለ ህዝብ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፍ ለማድረግ የተደረገውንም ጥረት ፣ ዓቅሙ የፈቀደውን ያህል ሊኮንነው ጣረ። እንኳን እንደ ኢትዮዽያ ዓይነት አስገራሚ ውጤት የታየበት ስራ የሰራ ህዝብ ፣ በችግር እና ለውጥ በማይታይበት ጉዞ ላይ ያሉ ከተሞች እና ሃገራት ፣ መጪውን ዘመን ተስፋ ለማድረግ እና በደስታ ዓመቱን ለመቀበል ከፍተኛ ውጪ የሚደረግባቸው ዝግጅቶች ያካሂዳሉ። ከዜጎች ደስታም ባለፈ ፣ በጊዜያዊነትም ቢሆን በከተሞች እና በአጠቃላይ የሃገር ኢኮኖሚ ላይም የሚፈጥረውን መነቃቃት ከግምት ውስጥ በማስገባትም ነው ፣ ከተሞች እና ሃገራት እንዲህ ዓይነቱን ወጪ ለማውጣት የሚደፍሩት። በርካታ ከተሞችም በዝግጅቶቻቸው ምክንያት በተፈጠረው የኢኮኖሚ መነቃቃት የተገኘውን ጠቀሜታም በአሃዝ የሚገልጹበት ሁኔታም አለ ፤ በተለይም ባደጉት ሃገራት። ኢትዮዽያ ለተደረገው ዝግጅት ወጣ የተባለው ገንዘብ ፣ በበርካታ ሃገሮች ለfire work ብቻ ከሚወጣው ገንዘብ በጣም ያነሰ ነው። በሚለንየም አዳራሽ የተደርገው ዝግጅት እዛው ታፍኖ የሚቀር ሳይሆን ፣ በተሌቪዥን መስኮቶች ተላልፎ እጅግ ብዙ ሚልዮኖች ኢትዮዽያውያንን የሚደርስ እና በዓላቸውን በደስታ እንዲያከብሩ የሚያስችል ነው። በትናንሽም ሆነ በትላልቅ ከተሞቻችን ለዓዲስ ዓመት ዋዜማ ተብለው በየሆቴሉ እና በየመዝናኛ ስፍራዎች የሚኖሩ ዝግጅቶችን የመካፈል አቅም የሌላቸው ወይንም ገንዘባቸውን መቆጠብ የመረጡ ዜጎቻችንን ከቤታቸው ሳይወጡ ደስ እንዲሰኙ ማድረግ እንዴት ነው ሃጢያት የሚሆነው? በምንስ ሂሳብ ነው ፣ ያውም በዚህ የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ዓቅም በፈጠርንበት ዘመን ፣ ኢትዮዽያውያን ከመላው ዓለም ተለይተው የዓዲስ ዓመትን በዓል በደስታ ማክበር እንዲነፈጉ የተፈለገው? ከበዓሉ በፊት በነበሩት አስር ቀናትም ይካሄድ የነበረውን ስርዓት ፣ ማለትም ቀናቱን በተለያየ የከበረ ትርጉም ያላቸው ሁነቶች ታስበው እንዲውሉ መደረጉም ለቢንያም ፈጽሞ አልተመቸውም ነበር። ዘንድሮ ለሱ የሚመች ነገር ከየት ይመጣል? የቀናቱን አከባበር በሚያጣጥልበት እና እራሱ እያዋረደ በነበረበት ወቅት ከተናገራቸው እራሱን ያስገመቱ ሁኔታዎች አንድ ልጥቀስ። ባልሳሳት ፣ የሰላም ቀን በሚከበርበት ቀን ይመስለኛል ፣ የተመረጠው ቀለም ነጭ ነበር። ነጭ ቀለም እጅግ በርካታ የሆኑ የመልካም ምሳለኔት ያለው የከበረ ቀለም ሆኖ ሳለ ፤ ቢንያም ከበደ “የመሸነፍ ምልክት ነው” ማለትን መረጠ። ከበርካታ የነጭ ቀለም መልካም ትርጉሞች በጥቂቱ ፤ የብርሃን ፣ የተስፋ ፣ የንጽህና ፣ የሰላም እና የመሳሰሉት። የመዳን ተስፋን በሚሹ ህሙማን ፊት የሚቀርቡ የህክምና ዶክተሮች የሚለብሱት እና ፣ በበርካታ ሃገራት የሰው ልጆች ትልቅ የደስታ ቀን በሆነው በሰርግ ዕለት ለሙሽራይቱ የተመረጠውን ቀለም ፣ ክፉ ትርጉም አለው አለን። ጃፓን እና የተባበረው አሜሪካን ጨምሮ ብዙ ሃገራትም በሰንደቅ ዓላማቸው ቀለማት ውስጥ ያካተቱት ትልቅ ምሳሌነት እና ትርጉምን የያዘ የቀለም ዓይነት ነው ፤ ነጭ። ይባስ ብሎ በዛ ቀን እሱ ጥቁር ለብሶ በመዋል ለመለየት ማሰቡንም ገለጸልን። የጥቁር ቀለም ትርጉም ደግሞ የነጭ ተቃራኒ እና በዘመናችን አስጨናቂ ወገኖች በአሸባሪዎች የተመረጠ ቀለም ነው። ከጨለማ ፣ ከሽብር እና ከመሳሰሉት ጋር የሚዛመደዉን ቀለም ለመልበስም መረጠ – ‘ቀለምን መልአክ ይመርጠዋል’ ልበል ።
አንድነትን ለማሳየት እና በፍጹም ፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ መልኩ ለአንድ ቀን ተመሳሳይ ቀለም እንልበስ የተባለበትን አጋጣሚም ፣ ምርጫ በሌለው ሁኔታ እና በትእዛዝ ዕድሜ ልክ አንድ ዓይነት ልበሱ ተብሎ ከታዘዘበት ከአስከፊው የደርግ ስርዓት ጋር ሊያመሳስለውም ፈለገ።
ሰሞኑንም ሌላ አሳዛኝ ክስተት ተፈጥሯል ፣ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎቻችን የተወሰነ ድንበር አካባቢ። እያንዳንዱ መልካም ያልሆነ ዜና የሰውዬውን ቀልብ መሳቡም አይቀሬ ነው – እነ ኢሳትን በሚያስንቅ ሁኔታ። የእንድ ጠንካራ እና የተረጋጋ ስርዓት መመዘኛው ፣ እኔ እንደምረዳው ፣ ምንም ዓይነት ችግር ወይም አደጋ የማያጋጥመው መሆን አይደለም። እንደዛ ከሆነ ፣ በዓለም ላይ አንድም የተረጋጋ ሃገር ወይም ስርዓት የለም ማለት ነው። መለኪያው ፣ የሚያጋጥመውን ሰው-ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ አደጋ ተቛቁሞ ማለፍ የሚችል እና እንደ ሰርዓት ወይም እንደ ሃገር መቀጠል የሚችል መሆን አለመሆኑ ነው። ያልተረጋጉ እና የብዛኛውን ህዝብ ይሁንታ ወይም ድጋፍ ያላገኙ ስርዓቶች አንድ ቀን የተለኮሰ እሳት ወይም የተነሳ ወጀብ ይዟቸው ይጠፋል። የተረጋጉት ግን ፣ የመጣውን ችግርም ሆነ አደጋ በህዝብ እና በጠንካራው መንግስት የተባበረ ስራ ይወጡታል። የተለኮሰ እሳት ወዲያው ቦግ ብሎ እንዲጠፋ ወይንም ሰደድ ሆኖ ሃገሩን የመብላት አቅም እንዲያጣ ለማድረግ የሚቻለው በስራ እንጂ በአጋጣሚ አይደለም። ቱኒዚያ ላይ አንድ ግለሰብ እራሱን በማቃጠሉ እሳቱ በቀላሉ ሰደድ ሆኖ ስንቱን እንደበላ ብዙዎቻችን እናስታውሳለን። ኢትዮዽያ ውስጥ ያው ድርጊት (እራስን ማቃጠል) በቀጥታ ተከስቶ እና ሌሎችም በርካታ እሳቶች ተለኩሰው የታለመላቸውን ግብ መምታት ያቃታቸው እና ወደ ሰደድነት ያልተቀየሩት ለምን ይሆን እንደው ባጋጣሚ አይመስለኝም። ባለፉት ሩብ ምዕተ ዓመታት የተሰሩ በርካታ ስራዎች ውጤት ነው። የብዙ ሚልዮኖች ህይወት ፣ በገጠርም ሆነ በከተማ ፣ ለማመን በሚችግር መልክ ተቀይሯል ፣ በመቀየርም ላይ ነው። በእስካሁኑ የለውጥ እና የእድገት ጉዘ ተጠቃሚ ያልሆኑትን ጨምሮ ፣ የበለጠ ለማደግ እና ለመለወጥ የሚፈልጉ እጅግ ብዙዎችም ተስፋ ጨብጠዋል። ስለዚህ ፣ ይህን ተስፋ የሚያጨልምም ሆነ ወደ ቀደመው ህይወት የሚመልስን ማንኛውንም አካሄድ ለመቀበል ፈቃደኛ የሆነ የህብረተሰብ ክፍል ፣ በብዙ ቁጥር ፣ ማግኘት የማይቻልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል እላለሁ። የኢትዮዽያን ጥፋት እና ውድመት አጥብቀው የሚሹ የውጭ እና በተወሰነ ደረጃ የውስጥ ጠላቶችም (እነ ኦነግ እና ግምቦት 7) ባሉበት እና ዛሬም ገና ሙሉ ለሙሉ ከድህነት ባልወጣንበት ሁኔታ ፣ ኢትዮዽያ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚለኮስ እና ቦግ ብሎ የሚጥፋ እሳት ለምን ኖረ ማለት ተጨባጭ ሁኔታዎችን ፍጹም ያላገናዘበ እና ሊተገበር የማይችል አመለካከት ነው ብዬ አምናለሁ።
ባለፈው በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎች “ጀነራል እና ሌላም የማዕረግ ስማቸው እየተገፈፈ ይጠሩ” በማለት እና ጥፋታቸው በህግ ፊት ያልተረጋገጠ ሰዎችን በራሱ ፍርድ ወንጀለኛ አድርጎ እንዳቀረባቸው ፤ ዛሬም በሁለቱ ችግር ባጋጠማቸው ክልሎቻችን አመራሮች ላይ እና አልፎም በፌደራሉ ስርዓት እና መሪዎች ላይ ተመሳሳይ ውርጂብኝ እያወረደባቸው ይገኛል። እራሱ ከሳሽ እና እራሱ ዳኛ በመሆን ፤ የሃገር ከፍተኛ ባለውለታዎችን ስም ማጥፋቱን ተያይዞታል። ደጋግሜ እንደምለው ፣ ይህ ስርዓትም ሆነ በውስጡ ያሉት መሪዎች በአብዛኛው ለፈተና እና ለውጣ ውረድ አዲስ ያልሆኑ እና ሰፊ ልምድ ያካበቱ በመሆናቸው ፣ እያንዳንዱን የሚመጣ ችግር አብዛኛውን የህብረተሰቡን ክፍል ከጎናቸው በማሰለፍ ይወጡታል። መወጣት ብቻ አይደለም ፣ ከችግሩ ተምረውም ጠንክረው የመውጣት ልዩ ችሎታ ያላቸው መሆኑን ባለፉት 26 ዓመታት ኖረን ያየንው እውነት ነው። እንኳን በዚህ ተራ የልምድ ጋዜጠኛ ተብዬ ፣ በሌሎች ከፍተኛ ግምት የሚሰጣቸው ግለሰቦች ፣ የመገናኛ ብዙሃን ተቛማት እና ሃገራት ትችትም የሚሸማቀቁ አለመሆናቸውም በጣም ደስ ያሰኘኛል።
ውሾቹም ይጮሃሉ ፣ ግመሎቹም ይጓዛሉ። ከአምላክ ጋራ ፣ የኢትዮዽያን የህዳሴ ጉዞ ማስቆም ወይም ወደኋላ መመለስ የሚችል ምንም ዓይነት ምድራዊ ሃይል የለም። ጠላቶቿም ፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ፣ ይሰነካከላሉ ፤ ህልማቸውም ሆነ ሟርታቸው በምድሪቱ ላይ አይሰራም።
  1. David Begna says

    Thank you so much. I totally agree on this aritcle. Ben’s peessimism became too much. In a way I respect him and couldn’t find a way to tell what is doing is totally anti EPRDF propaganda. For now he said that our government is the same as ‘derg’ and we will see what will come next.

  2. Daniel Thomas says

    Ben is a mercenary,he doesn’t have his own stance.He is an opportunist.He only looks for his advantage only.He is not allowed to kid on my country.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy