Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በውጭ መገናኛ ብዙሃን እይታ

0 457

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች እያከናወነች ያለውን ስኬታማ ተግባራት የተለያዩ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃን በድረገጾቻቸው ለንባብ አብቅተዋል። በተለይም በኢኮኖሚው መስክ እየታየ ያለው ለውጥ፣ የውጪም ሆነ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በማከናወን ላይ ያሉት ተግባራት በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ ሆነው ለመውጣት የሚያስችላቸውን አቅጣጫ እንደያዙ ዘገባዎቹ የዳሰሱዋቸው እውነታዎች ናቸው። ባለፈው ሳምንት መልካም ገጽታዎችን አጉልተው ካስነበቡት መካከል ኢትዮጵያና ኬኒያ ይበልጥ ኢንቨስትመንት እያሰቡ ስለመሆኑ፤ አገራዊ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሃዝ ማሻቀብ ጤናማ ያልሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት መሆኑ፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያውን አሪክ አየር መንገድ የማስተዳደር ስራ ሊረከብ ነው የሚሉትና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ኢትዮጵያና ኬንያ ይበልጥ ኢንቨ ስትመንትን እየሳቡ ነው

ኢትዮጵያና ኬንያ የሌሎች የአፍሪካ ሀገራት በተለየ ሁኔታ ኢንቨስትመንትን እየሳቡ መሆኑ የአፍሪካን የኢኮኖሚ የበላይነትን ከናይጄሪያና ደቡብ አፍሪካ ሊረከቡ እንደሚችሉ ኮንትሮል ሪስክ የተባለ አጥኚ ተቋም ገለጸ፡፡

ተቋሙ በድረገፁ ባሰፈረው ዘገባ በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ባወጣው ጥናት መሰረት ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2016 3 ነጥብ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከሌሎቹ የአህጉሪቱ ሀገራት በሰፊ ልዩነት ቀዳሚ መሆን ችላለች ብሏል።

ኢትዮጵያ ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2015 .ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ውስጥ በአማካይ የ10 ከመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ የቻለች ሲሆን ባለፈው አመት ደግሞ የነጥብ የምጣኔ ሀብታዊ እድገት ማስመዝገቧን ኮንትሮል ሪስክ የተባለው አጥኝ ተቋም በድረገፁ አስፍሯል።

አገራዊ የዋጋ ግሽበቱ ወደ ሁለት አሃዝ ማሻቀብ ጤናማ ያልሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት መሆኑ ተጠቆመ

የኦል አፍሪካ የወሬ ምንጭ በድረ ገጹ ባስነበበው ዘገባ የነሃሴ ወር አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት 10 ነጥብ በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።ምንጩ ኤጀንሲው አወጣሁ ባለው መግለጫ ወርሃዊ የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ወር ከተመዘገበው የነጥብበመቶ የዋጋ ግሽበት በአንድ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ።

በወሩ ምግብ ነክ በሆኑ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ለግሽበቱ መጨመር ምክንያት መሆኑን ምንጩ ዘግቧል። በወሩ የምግብ ነክ ሸቀጦች ግሽበት 13 ነጥብ በመቶ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን፥ ይህም ባለፈው ወር ከተመዘገበው የ12 ነጥብ በመቶ አንጻር የነጥብ በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

ምግብ ነክ ባልሆኑ ሸቀጦች ላይ የተመዘገበው የነጥብ በመቶ ግሽበት፤ ባለፈው ወር ከተመዘገበው ነጥብ በመቶ ግሽበት አንጻር የነጥብ በመቶ ጭማሪ ታይቶበታል ነው ያለው ኤጀንሲው። ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበትም ከአንድ አመት በኋላ ተመዝግቧል፤ ለመጨረሻ ጊዜ ባለሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት የተዘመገበው በጥር ወር 2008 .ም ነበር። በወቅቱ ሃገራዊ የዋጋ ግሽበቱ 10 ነጥብ በመቶ ሆኖ ነበር የተመዘገበው።

(All Africa & FBC 9 September 2017- All the Time)

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያውን አሪክ አየር መንገድ የማስተዳደር ስራ ሊረከብ ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የናይጀሪያውን አሪክ አየር መንገድ የማስተዳደር ስራ ለመረከብ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ድርድር እያደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አሪክ አየር መንገድን ለማስተዳደር እየተደረገ ባለው ድርድር በቴክኒክ ጉዳዮች ላይ መግባባት መደረሱን ተናግረዋል፡፡

የናይጀሪያ አየር መንገድ በ2012 በደረሰበት ኪሳራ ከተዘጋ ወዲህ ሀገሪቱ ብሔራዊ አየር መንገድ የላትም፡፡ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ የናይጀሪያ መንግስት ከሌሎች ጋር በሽርክና የመሰረተው ቨርጂን ናይጀሪያ እና የናይጀሪያ አየር መንገዶች በደረሰባቸው ኪሳራ ምክንያት መዘጋታቸው ይታወሳል፡፡የናይጀሪያ መንግስት በአሁኑ ወቅት በግል ሲተዳደር የነበረውን አሪክ አየር መንገድ ካለፈው የካቲት ወር ጀምሮ ወደ መንግስት ይዞታ በማዞር እያስተዳደረው ይገኛል፡፡

ይህን ተከትሎም አየር መንገዱን ትርፋማ ለማድረግ የናይጀሪያ መንግስት የማስተዳደር ስራውን ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የናይጀሪያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ጎድፍሬይ ኦዱዲግቦ፤ አየር መንገዱን በውል ለማስተዳደር እየተካሄደ የሚገኘው የሁለቱ ወገኖች ድርድር በመልካም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቴክኒክ ድጋፎችን የሚሰጥበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ኦዱዲግቦ ተናግረዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የናይጀሪያና የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ የሁለትዮሽ ግንኙነት ለመመስረት የጋራ ኮሚሽን መመስረታቸውን አምባሳደሩ ጠቅሰዋል፡፡ በጋራ ኮሚሽኑ በሚደረጉ ስብሰባዎችም የተለያዩ የሁለትዮሽ ስምምነቶች የሚካሄዱ ሲሆን፤ የአሪክ አየር መንገድን የማስተዳደር ስምምነትም ይፈረማል ተብሎ እንደሚጠበቅ ነው የጠቆሙት፡፡

እንደ አምባሳደሩ አገላለፅ የጋራ ኮሚሽኑ ስብሰባ በመጪው ህዳር ወር በአቡጃ ሲካሄድ አየር መንገዱን የማስተዳደር ስምምነት ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በበረራው ኢንዱስትሪ ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደር ኦዱዲግቦ፤ የአሪክ አየር መንገድን ማስተዳደሩ የሀገሪቱ የአየር መንገዶች ህልውና እንዲረጋገጥና የአገልግሎት አድማሳቸው እንዲሰፋ ያስችላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

(Guardian Newspapers 10 September 2017)

ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ አለም አቀፍ ስምምነት ያስፈልጋል ተባለ

በዓለማችን ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ኢኮኖሚ ለመገንባት አዲስ ዓለም አቀፍ ስምምነት እንደሚያስፈልግ የተመድ የ2017 የንግድና ልማት ሪፖርት አመለከተ። በተባበሩት መንግስታት የንግድና የልማት ጉባዔ የ2017 ሪፖርት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ይፋ ተደርጓል። በሪፖርቱ የዓለማችን ኢኮኖሚ እያደገ መሆኑም ተወስቷል። እድገቱ ፍትሃዊና የሁሉንም ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ያልቻለ መሆኑንም ነው ያመለከተው።

የዓለም አቀፍ ፋይናንስ ስርዓት ያለመረጋጋቱን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ በአሁኑ ወቅት ያለው ሉላዊነት ፍትሃዊ ካልሆነና ካልተረጋጋ ኢኮኖሚ ጋር የተያያዘ መሆኑን ጠቁሟል። ዓለም አቀፍ ገበያ በኪራይ ሰብሳቢዎች እጅ መውደቁን ያወሳው ሪፖርቱ፤ ገበያው እነርሱን ብቻ እንጂ ብዙሃኑን ተጠቃሚ እንደማያደርግ አመልክቷል።

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሩዋንዳና ታንዛኒያ ጥሩ ዕድገት ማስመዝገባቸውን ጠቅሶ፤«አፍሪካ በዓለም አቀፉ ተጽዕኖ እጅጉን ተጎድታለች» በሚል አትቷል።«ሁሉንም ተጠቃሚ ያደረገና ዘላቂ ኢኮኖሚ ለማረጋገጥ አዲስ አለም አቀፍ ስምምነት ያስፈልጋል» በማለትም ለችግሮቹ መፍትሄ አመላክቷል።

በኢኮኖሚው «የማገገም፣ ማሻሻያ እና መልሶ ማከፋፈል” እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል የ21ኛው ክፍለ ዘመን አጀንዳ እንደሚያስፈልግ ሪፖርቱ በተጨማሪ መፍትሄ ጠቁሟል። ለዚህም እአአ 1930ዎቹ የነበሩት «አለም አቀፍ የማገገም፣ ማሻሻያ እና መልሶ ማከፋፈል ስምምነት ፖሊሲዎች አሁንም ጠቃሚ ናቸው» በማለት ገልጿል።

በአፍሪካ የተባበሩት መንግስታት የንግድና የልማት ኮንፈረንስ ክፍል ዳይሬክተር አቶ ታፈረ ተስፋቸው በበኩላቸው፤ ሁሉም የዓለማችን መንግስታት ዘላቂና ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን እንዲሰሩ ሪፖርቱ ማሳየቱን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነድፋ በመተግበር ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሰራች መሆኑን ጠቅሰው፤«ይሄን ዓይነት መንገድ መከተል ችግሮቹን ለመፍታት ይረዳል» ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ከሁለት ነጥብ አምስት በመቶ በታች እያደገ ያለው የዓለማችን ኢኮኖሚ ደካማ ሆኖ መቀጠሉን ሪፖርቱ ጠቁሟል። የዓለም አቀፍ ንግድ እኤአ በ2015 እና 2016 ወደ አንድ ነጥብ አምስት በመቶ መውረዱን በሪፖርት የተጠቆመ ሲሆን የኢዜአን ዘገባ የተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተቀባብለውታል ።

በሞኒተሪንግ ክፍል

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy