Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለብዙ ዘርፍ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሷን በስኬት እንዳረጋገጠች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ።

0 773

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለብዙ ዘርፍ ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሷን በስኬት እንዳረጋገጠች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አስታወቁ።

በኒው ዮርክ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 72ኛ ጠቅላላ ጉባዔም ሆነ ጎን ለጎን በተካሄዱ ባለብዙ ዘርፍና የሁለትዮሽ ውይይቶች ስኬታማ የዲፕሎማሲ ስራዎች መከናወናቸውንም ነው ሚኒስትሩ የጠቀሱት።

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመራ የልዑካን ቡድን የተባበሩት መንግስታት 72ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ተካፍሏል። የባለብዙ ዘርፍና የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን አካሂዷል።

ከአሜሪካ ፣ ከአውሮፓ ፣ ከአፍሪካና ከእስያ አገራት መሪዎች፣ ከከፍተኛ ባለስጣናት ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት፣ በአህጉራዊና ዓለማቀፋዊ ትስስሮች እንዲሁም ፈታኝ ሁኔታዎችና የመፍትሄ ሃሳቦች ላይ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

የመንግስታቱ ድርጅት 72ኛ ጉባዔና ተጓዳኝ ውይይቶች አስመልክቶ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ዶክተር ወርቅነህ እንደገለጹት ፤ አሁን በተካሄደው ጉባዔ የተገኘው ስኬት የአገራችን ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ያሳያል።

ኢትዮጵያ የጸጥታው ምክር ቤት የሰላም ማስከበር ማሻሻያ ሀሳብ አቅርባ በሙሉ ድምጽ መጽደቁ በልዩ ሁኔታ የሚታይ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር ወርቅነህ፤ የዚህ ዓይነቱን ተግባር የበለጠ አጠናክሮ መሄድ እንደሚያስፈልግም አጽንኦት ሰጥተውታል።

አሸባሪው አይ.ኤስ.አይ.ኤስ ባደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጥፋት በህግ ተጠያቂ እንዲሆን የሚያስችለው ውሳኔ በኢትዮጵያ ሊቀመንበርነት ወቅት መጽደቁን አስታውሰው፤ ኢትዮጵያዊያንን በማንነታቸው ብቻ ደማቸውን ያፈሰሰው ቡድኑ በህግ ተጠያቂ እንደሚሆን ስለተረጋገጠበት ትልቅ ጉዳይ መሆኑን አውስተዋል።

የዓለም ማህበረሰብን እያስጨነቀ ያለውን ጅምላ ጨራሽና የኒኩሌር መሳሪያዎችን በተመለከተ የተነሱት ጉዳዮችም ተጠቃሽ ናቸው።

በጸጥታው ምክር ቤት በመሪዎችና በውጭ ጉዳዮች ደረጃ የተካሄዱ ስብሰባዎችን በመምራት ጠንካራ ውሳኔዎች መተላለፋቸው የኢትዮጵያን ዲፕሎማሲ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ የሚያረጋግጡ መሆናቸውንም ነው ሚኒስትሩ ያብራሩት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy