Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

እንግሊዝ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት አጋርነቷን እንደምታጠናክር ገለጸች

0 283

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

እንግሊዝ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት አጋርነቷን እንደምታጠናክር ገለጸች

እንግሊዝ በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ድገፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታወቀች።

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚ/ር ዴኤታ ሮሪ ስቴዋርት ጋር በኒዮርክ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የጎንዮሽ ውይይት አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በቀጠናው ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን በኢጋድ ጥላ ስር የምታደርገውን ጥረት በሙሉ አቅሟ እንደምትገፋበት ዶ/ር ወርቅነህ ገልጸዋል።

በሶማሊያ ያለው ሰላም ፈጣን መሻሻሎችን እያሳየ ነው ያሉት ዶ/ር ወርቅነህ ሆኖም ከአልሸባብ በኩል የሚሰነዘረውን ጥቃት ከስሩ ለመናድ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አጋርነት ወሳኝ ነው ብለዋል።

በተለይም የሶማሊያ ተቋማትን በመገንባትና በማጠናከር ረገድ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ አስፈላጊ እንንደሆነም ነው ዶ/ር ወርቅነህ የገለጹት።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በደቡብ ሱዳን ሰላምን ለመመለስ ኢጋድ የሚያደርገውን ጥረት እንዲደግፍም ዶ/ር ወርቅነህ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚ/ር ዴኤታ ሮሪ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላምና መረጋጋትን እንዲሰፈን የምታደርገውን ጥረት አገራቸው እንድምታደንቅ ተናግረዋል።

እንግሊዝ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ያላትን አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥልም ገልጸዋል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy