Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

        የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋናችን

0 809

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

        የአካባቢ ጥበቃና የደን ሽፋናችን

                                  ዳዊት ምትኩ

የትግራይ ክልል በአካባቢ ጥበቃና ከሲጋራ ነፃ የሆነን አካባቢን በመፍጠር ህብረተሰቡን ከበሽታ ለመከላከል ባደረገው ጥረት ሰሞኑን ሽልማት አግኝቷል፡፡ ሽልማቱ በአገራችን የተከናወነውን የአካባቢ ጥበቃ ስራ የሚያሳይ፣ በተለይም ተመናምኖ የነበረውን የደን ሽፋናችንን ወደ 15 በመቶ ከፍ እንዲል እያደረገች ያለችውን ጥረት የሚገልፅ ነው፡፡ ይህ ለውጥ የአገራችን ከፍታ አንዱ ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል ይመስለኛል፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ የአካባቢ ጥበቃን መሰረት አድርገው እየተሰራባቸው ካሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል፤ የተጎዱ መሬቶችን ከእንስሳትና ከሰው ንክኪ ነጻ በማድረግ እንዲያገግሙ የማድረግ ቴክኖሎጂ አንዱ ነው፡፡

ቴክኖሎጂው በዕፅዋት ሽፋን መሳሳትና በአፈር ለምነት መቀነስ ሳቢያ የተጎዱና ምርታማነታቸው የተቋረጡ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ የሚያደርግ ከማድረግ አንፃር የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

ቴክኖሎጂው የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ እንዲያገግሙ ለማድረግ በየአካባቢው መልክዓ ምድር ሊተገበር የሚችል ሲሆን፤ ለአካባቢው አየር ፀባይ ተስማሚ የእፅዋት ዝርያ በመምረጥ ተስማሚ የእርከን ዓይነቶችን መለየት እና የገቢ ምንጭ ሊያስገኙ የሚችሉ ስራዎች ተቀናጅተው የሚሰሩበት ሁኔታ በማጤን ህብረተሰቡ የሚጠቀምበትን መንገድ ለማሳየት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እንዲከናወኑ አስችሏል፡፡

ማህብረሰቡም የተጎዱ ቦታዎችን መልሶ እንዲያገግሙ የማድረግና የማልማት እንዲሁም ዕውቀትና ክህሎት እንዲያዳብር ያግዛል፡፡ የመሬት ጥበቃ ችግርን በማሳበብ ህብረተሰቡ ከአካባቢው እንዳይሰደድ አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የጓሮ አትክልቶችንና ፍራፍሬዎችን አልምቶ ራስንና ቤተሰብን ለመመገብ ብሎም ጤናው እንዲሻሻል በማድረግ ረገድ መንግስት አስቀድሞ በሽታን ለመከላከል ለያዘው ዕቅድ የራሱን ድርሻ ይጫወታል፡፡

በዚህም ምክንያት በየአካባቢው ጠፍተው የነበሩ የእፅዋትና የእንስሳት ዝርያዎች በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡ ቴክኖሎጂው ለአካባቢ ጥበቃ ከሚያደርገው ጉልህ ድርሻ ባሻገር፤ ከግብዓት አቅራቢዎች ጋር የአቅርቦት ትስስር በመፍጠር በማህብረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው አድርጓል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው አስተማማኝ በመሆኑም ለቴክኖሎጂ ዘላቂነት ወሳ” ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

እንደሚታወቀው የተጎዱ መሬቶችን መልሶ እንዲያገግሙ ለማድረግ የተለያዩ ሀገር በቀል ዛፎችን መትከል ዋነኛው አማራጭ ነው፡፡ ለዚህም በርካታ የችግኝ ማፍያ ጣቢዎችን በብዛት መጠቀም ያስፈልጋል፡፡

በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሀብቶችም ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን የዛፍ፣ የፍራፍሬና የአትክልት ችግኞችን ለገበያ በማቅረብ የስራ መስክ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል፡፡ በአነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ለተደራጁ ግለሰቦች የሰብል ፍርፍሬና፣ አትክልት የዛፍ ችግኞችን አቀናጅቶ በማምረት የገቢ ምንጭን ማሳደግም ችሏል፡፡

እርግጥ ለአካባቢ ጥበቃ አጋዥ ናቸው ተብሎ እየተሰራባቸው ካሉ ቴክኖሎጂዎች መካከል የቀርከሃ ልማትና ዕደ ጥበብ ቴክኖሎጂ ተጠቃሽ ነው፡፡ የቆላም ሆነ የደጋ የቀርከሃ ምርት፤ ለማገዶ፣ ለግንባታ ስራዎች፣ ለቤት ውስጥ ቁሳቁሶች እንዲሁም ለኢንዱስትሪ ግልጋሎትነት መዋል መቻሉ የቀርከሃ ዕደ ጥበብ ውጤቶችን ከማምረትና ለገበያ ከማቅረብ በተጨማሪ ገቢ ያስገኛል፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንደሚገልፁት፤ የቀርከሃ ተክል ብዛት ያላቸው የሚጠላለፍ ረዣዥም ስሮች ያሉት በመሆኑ አፈርን አቅፎ መያዝ የሚችል ነው፡፡ በአየር ውስጥ ያለውን ሙቀት አማቂ ጋዞችን በመምጠጥ የምድርን ሙቀት በመቀነስ ረገድም አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የተጎሳቀለ መሬት መልሶ እንዲያገግም ያግዛል። በመሆኑም መንግስት ለዘርፉ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራበት ይገኛል፡፡

እዚህ ላይ የአካበቢ ጥበቃን የተሻለ ለማድረግ የተፈጥሮን ሥነ- ምህዳር ለመጠበቅ ከሚደረገው ርብርብ ባሻገር፤ የዕለት ተዕለት ኑሮአችን የምንጠቀምባቸውን መሣሪያዎች መመልከት ጠቃሚ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም አገራችን ከፍተኛ የሆነ የጋዝ ልቀትን ለመቀነስ ከፀሃይ ኃይል ኤሌክትሪክ የሚያመነጭ ቴክኖሎጂዎችን በአማራጭነት እየተጠቀመች በመሆኑ ነው፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ የፀሃይ ሃይልን በመሰብሰብ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ ቴክኖሎጂ የሚገኘው የኤሌክትሪክ ሃይል ታዳሽ በመሆኑ በዘላቂነት መጠቀም ይቻላል፡፡ በየትኛውም መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥና በቂ ፀሃይ ጨረር በሚገኝባቸው አካባቢዎች ሁሉ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል ቴክኖሎጂ ስለሆነም በሀገራችን ተመራጭ ሆኗል፡፡

በአገሪቱ የሚኖረው ሰፊው ህብረተሰብ አርሶ አደር በመሆኑ የኤሌክትሪክ መስመር ባልተዘረጋባቸው አካባቢዎች ተደራሽ በመሆን ከፍተኛ የሃይል አማራጭ ሆኖ ይገኛል፡፡ በባህላዊ የማገዶ አጠቃቀም ምክንያት ወደ አካባቢ አየር የሚለቀቁትን አማቂ ጋዞችን የሚቀንስ ስለሆነም ለአካባቢ ብክለት መቀነስ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው። የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን የሚያከናውን መስሪያ ቤትን በሚኒስቴር ደረጃ አቋቁማ እየሰራች ነው። ይህመ ከአፍሪካ ግንባር ቀደም ሀገር እንድትሆን አድርጓታል፡፡

የአካባቢ ሙቀት ሳቢ ጋዞችን ልቀት በመቀነስ አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የእንስሳትና የሰብል ምርታማትን በማሳደግ፣ የአርሶና አርብቶ አደሩን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ፣ የካርቦን ልቀትን ለመቀነስ ደንን በመጠበቅና በማልማት፣ ከታዳሽ ኃይል ምንጭ የኤሌክትሪክ ኃይል በሰፊው በማመንጨትና ዘመናዊና ኃይል ቆጣቢ ቴክኖሎጂዎችን በትራንስፖርት፣ በኢንዱስትሪና በህንፃ ኮንስትራክሽን ዘርፎች በመጠቀም ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች ነው፡፡

አገራችን በዋነኛነት የምትጠቀመው ሌላኛው አማራጭ የታዳሽ ኃይል ልማር ከፀሐይ ኃይል የሚገኘው የታዳሽ ኃይል ዘርፍ ነው፡፡ የአስራ ሦስት ወር የፀሐይ ፀጋ እንዳላት ሁሌ የሚነገርላት ኢትዮጵያ  እጅግ ሰፊ የፀሐይ ኃይልን የማመንጨት አቅም አላት፡፡ 2 ነጥብ 199 ሚሊዮን ቴራ ዋት አወር ዓመታዊ አቅም አላት፡፡ ከፀሐይ ኃይል በሁለት ዓይነት መንገዶች ማመንጨት ይቻላል፡፡

አንደኛው ፎቶቮልታይክ የሚባለው ኃይልን ወደ ኤሌክትሪክ ቀይሮ ወደ መስመር ማስገባት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ ፀሐይ ሙቀት ውኃን በማጋል ተርባይኑን በእንፋሎት ትነት የማሽከርከር መንገድን የሚከተል ነው፡፡

በዚህ ረገድ የፀሐይ ኃይልን በእጅ በቀላሉ በሚንቀሳቀሱ መብራቶች ለየቤቱ አጠቃላይ ፍጆታ ለማዋል በሚያስችል ስርዓት የተዘጋጁ አካባቢያዊ ሽፋን በሚሰጥ መልክ የተዘጋጁ እና ለማሞቅ ወይም ለማብሰል የሚያገለግሉ ሆነው የተዘጋጁ ሆነው ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረት የፀሐይ ኃይል ልማት በዋናነት በገጠሩ አካባቢ ኤሌክትሪክ ኃይልን ለማዳረስ እንዲውል ነው፡፡ ስለዚህም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሳተፉበት እያበረታታ ነው፡፡ ውጤትም አግኝቷል፡፡

በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በተለይ የተራቆቱ አካባቢዎችን በማልበስ ረገድ የተገኘው ውጤት አገራችን የምትከተለው አረንጓዴ ፖሊሲ ውጤት ነው፡፡ ከክልሉ ተጨባጭ ለውጥ ሌሎች ክልሎችም ተገቢውን ትምህርት በመውሰድ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲውን ተመርኩዘው ተሸላሚ መሆን የሚገባቸው ይመስለኛል፡፡

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy