Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአዲስ አበባ ታክሲዎች በዘመናዊ ተሽከርካሪዎች ሊተኩ ነው

0 671

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በአዲስ አበባ ከተማ ለረጅም ዓመታት እያገለገሉ ያሉት ሰማያዊ በነጭ ታክሲዎች (አነስተኛና መካከለኛ)፣ ዘመናዊ በሆኑ መካከለኛ ለብዙኃን አገልግሎት በሚሰጡ ታክሲዎች ሊተኩ መሆኑ ታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካቤኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ አቶ ፀጋዬ አርዓያ ሰሞኑን በአዲስ አበባ በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ውስጥ ላሉ 65 የታክሲ ባለንብረት ማኅበሮችና ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ እንደተገለጸው፣ በአዲስ አበባ ውስጥ በማገልገል ላይ የሚገኙት መካከለኛና አነስተኛ ታክሲዎች ያረጁና የአገልግሎት ዘመናቸው ያለፈባቸው ስለሆኑ በአዳዲስና ዘመናዊ በሆኑ መካከለኛ የብዙኃን አገልግሎት በሚሰጡ ታክሲዎች ይቀየራሉ፡፡

በትራንስፖርት ሚኒስቴር የቀረጥ ነፃ ፈቃድና የአገልግሎት አሰጣጥን ለመወሰንና ለመቆጣጠር በወጣው መመርያ ቁጥር 8/2007 መሠረት፣ በማኀበር የተደራጁና ሕጋዊ አሠራርን የተከተሉ ማኅበራት የዕድሉ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአዲስ አበባ በማገልገል ላይ ያሉ በተለምዶ 12 ተሳፋሪዎች የሚይዙ ሚኒባስ ታክሲዎችና አራት ሰዎችን የሚይዙ ላዳዎች በከተማዋ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ ማገልገላቸውን፣ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ የደረሰችበትን የዕድገት ደረጃ የማይመጥኑ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በቅርቡ ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር አድርገውት በነበረው ውይይት፣ በአዲስ አበባ ውስጥ እያገለገሉ ያሉ እነዚህ አነስተኛ ታክሲዎች ወደ ዘመናዊና ከ20 እስከ 30 ሰው በሚይዙ ታክሲዎች ለመተካት፣ ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ መንግሥት የፈቀደ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል፡፡

ባለፈው ሳምንት በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የሚሠሩ የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበራት ተወካዮች አቶ መንበሩ ሽታዬ፣ አቶ ዘሪሁን ደሳለኝ፣ አቶ ኩሩ ተሰማ፣ አቶ ይበልጣል አባተና ወ/ሮ ሰላማዊት ጌታቸው ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ የአዲስ አበባ የታክሲ ሥርዓትን ለማዘመን በመካከለኛ ታክሲዎች ወይም ከ27 እስከ 30 ሰዎች በሚይዙት ለመተካት ማቀዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህ ሊሆን የሚችለው ግን መንግሥት ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት ፈቃደኛ ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ በከተማዋ ውስጥ ያሉ ታክሲዎች በጣም ያረጁ ናቸው፡፡ በአዲስ አበባ ያለውን የታክሲ ሥርዓት ለማዘመንና የሚያገኙትን ገቢ ከቀድሞው የተሻለ ለመድረግ ከመንግሥት ጋር በወኪላቸው አማካይነት ሲነጋገሩ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የታክሲ ማኅበራት ተወካዮች ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ መካከለኛና ዘመናዊ ታክሲዎችን ከቀረጥ ነፃ ለማስገባት ለአክሎክ ጀኔራል ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ውክልና ሰጥተውታል፡፡ ድርጅቱ የቀረጥ ነፃ ዕድል የተገኘበትን ምቹ ሁኔታ በመፍጠሩ ውክልና መስጠታቸውን አክለው ገልጸዋል፡፡ ይህ ድርጅትም በአሁኑ ወቅት የታክሲ ባለንብረቶችን ውክልና ወስዶ ከመንግሥት ጋር ታክሲዎች ከቀረጥ ነፃ በሚገቡበት ሁኔታ ላይ ሲመክር መቆየቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ሥራው ወደ መጠናቀቁ ደረጃ ላይ ከመድረሱም በላይ፣ የሚመለከተው የከተማዋ መሥሪያ ቤቶች በተለይም የከተማዋ የትራንስፖርት ባለሥልጣንና የቱሪዝም ቢሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ ጉዳዮች ምክትል ኃላፊ በጻፉት ደብዳቤ ማኅበራቱ ከቀረጥ ነፃ ወደ አገር ውስጥ የማስገባት ዕድል ተጠቃሚ በመሆን፣ ደረጃቸውን የጠበቁና ለነዋሪዎችም ሆነ ለቱሪስቶች ምቾት ያለው አገልግሎት ይሰጣሉ ብለዋል፡፡

የታክሲ ባለንብረቶች ማኅበር በአሁኑ ወቅት በማኅበራቸውና በተወካዮቻቸው አማካይነት አስፈላጊውን የገንዘብ መዋጮና ሌሎች ጉዳዮችን በማሟላት፣ በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ሰማያዊና ነጭ ሚኒ ባሶችንና አሮጌ ላዳዎችን በቅርቡ ይተካሉ ተብሏል፡፡ አስተያየት ሰጨዎች እንደሚሉት ይህ ጉዳይ ከተፋጠነና በቅርቡ ዕውን የሚሆን ከሆነ፣ የታክሲ ባለንብረቶች የተሻለ ገቢ ከማግኘታቸውም በላይ፣ የከተማዋ ታክሲዎች ሙሉ በሙሉ ዘመናዊ ይሆናሉ፡፡porter.

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy