Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የአዲስ አበባ ውኃ ታሪፍ ጭማሪ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ታገደ

0 591

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የውኃ ታሪፍ ጭማሪ እንዲደረግ ውሳኔ ቢያሳልፍም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ውሳኔው ተግባራዊ እንዳይደረግ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰማ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ሥራ አመራር ቦርድ ለከተማው ነዋሪዎች በሚቀርበው ውኃ ታሪፍ ላይ ማሻሻያ (ጭማሪ) እንዲደረግ በበጀት ዓመቱ መጀመርያ ውሳኔ አሳልፈው ነበር፡፡

የታሪፍ ጭማሪው መነሻ የአዲስ አበባ ከተማ የውኃ ታሪፍ ከሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችና ከሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ በመሆኑ፣ ይህ የታሪፍ ምጣኔ ዝቅተኛ መሆኑ ደግሞ ባለሥልጣኑ ለሚያከናውናቸው ግዙፍ ፕሮጀክቶች ሁነኛ የፋይናንስ ምንጭ መሆን ባለመቻሉ ነው ተብሏል፡፡

የባለሥልጣኑ ባለሙያዎች በተለያዩ አማራጮች የታሪፍ ጭማሪ ጥናት ካካሄዱ በኋላ ማሻሻያው በሥራ አመራር ቦርዱና በካቢኔው ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በመጨረሻ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ትዕዛዝ ተግባራዊ እንዳይደረግ መታገዱ ተረጋግጧል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ አወቀ ኃይለ ማርያም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ የታሪፍ ጭማሪው ተግባራዊ ከመደረጉ በፊት አገልግሎት አሰጣጡን የተሻለ ደረጃ ማድረስ ያስፈልጋል በሚል ምክንያት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭማሪው እንዲዘገይ አድርገዋል፡፡

አቶ አወቀ ጨምረው እንደገለጹት፣ የንፁህ ውኃ የማምረቻ ዋጋ በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል፡፡ አንድ ሜትር ኪዩብ ንፁህ ውኃ የማምረቻ ዋጋ ከስድስት ብር በላይ መሆኑን፣ ነገር ግን ለኅብረተሰቡ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ላለው የማኅበረሰብ ክፍል ከሁለት ብር ባነሰ ዋጋ ይቀርባል ብለዋል፡፡

ይህንን በተመለከተ በተደረገው ጥናት የኅብረተሰቡን አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ጭማሪ ተደርጎ እንደነበር፣ ከባለሥልጣኑ የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከራሱ ግምጃ ቤትና በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ዋስትና ከውጭ በሚያገኘው ብድር በአሥር ቢሊዮን ብር ወጪ፣ በርካታ የውኃና የፍሳሽ ፕሮጀክቶችን በማካሄድ ላይ ነው፡፡

በሁለቱም አገልግሎቶች የሚያስከፍለውና ለሚሰጠው አገልግሎት የሚያወጣው ወጪ የተመጣጠነ ባለመሆኑ፣ የከተማ አስተዳደሩ የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣንን እንደሚደረጉም ተገልጿል፡፡

ባለሥልጣኑ ከዚህ ችግር ለመውጣትና በራሱ ገቢ ራሱን ለመቻል የውኃ ታሪፍ ጭማሪ ማድረግ የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ የታሪፍ ለውጥ ሳያደርግ ከአሥር ዓመት በላይ እንደሆነው ተገልጿል ethiopianreporter

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy