Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ጥልቅ ተሃድሶውና የኢህአዴግ መግለጫ

0 225

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ጥልቅ ተሃድሶውና የኢህአዴግ መግለጫ

                                                     ቶሎሳ ኡርጌሳ

ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በቅርቡ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በመግለጫውም ያለፈውን ዓመት የድርጅቱንና የመንግስትን የስራ አፈፃፀሞች በጥልቀት መገምገሙንና ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጡን ገልጿል። በዚህ ፅሑፍ ላይም ከመግለጫው በመነሳት በተለይ ከጥልቅ ተሃድሶው ጋር የተያያዙ ጉዳዩችን ለመመልከት እሞክራለሁ።

መግለጫው ባለፈው ዓመት የተጀመረው በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የሚገኝበት ሁኔታ በመመልከት በተሃድሶው የተገኙ ውጤቶችን ተመልክቷል። በቀጣይ የ በዝርዝር በመገምገም በሁሉም ደረጃዎች በተካሄዱ መድረኮች በተዛቡ አመለካከቶች ላይ ነጻ፣ ግልጽና መተክላዊ ትግል መደረጉን ፈትሻል፡፡ በተለይም ስልጣንን ለግል ጥቅም ከማዋል ጋር ተያይዞ የሚታይ የስልጣን አተያይ ችግር የወለዳቸው የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካ መገለጫ የሆኑት ትምክህተኝነት፣ ጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራሪነት፣ ብልሹ አሰራርና ሙስና እንዲሁም በስርዓቱ ላይ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶች ላይ ጠንካራ ትግል ተደርጓል።

ጥልቅ ተሃድሶው ፀረ ዴሞክራሲያዊነትና አድርባይነት እየቀነሰ እንዲሄድ ማድረግ መቻሉንና ተሃድሶውን ተከትሎ ጀታች እስከ ላይ የማጥራት ስራዎች መከናወኑ ተመልክቷል። በተለይም ሀዝቡን ባሳተፈ መልኩ የመንግስስትን አመራሮች በየደረጃው በመገምገም የጠራ መስመር መያዝ ተችሏል።

በተለይም በሲቪል ሰርቪስ ውስጥ በተካሄዱ የጥልቅ ተሃድሶ መድረኮች የሰቪል ሰርቫንቱ የአገልጋይነት መንፈስ ማነስና ውጤታማ አገልግሎት አለመስጠት በዚህም ተገልጋዩን ህዝብ ለምሬት የሚዳርጉ ችግሮች መኖራቸው በመለየት ችግሮቹን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥረቶችን ተደርገዋል። እነዚህ ጥረቶች ወደፊትም ተጠናክረው ይቀጥላሉ። ምክንያቱም አሁንም ድረስ ጥረቶቹ በተሟላ ሁኔታ የህዝቡን አመኔታ በሚያስገኝ መልኩ የተፈቱ ባለመሆናቸው ነው። ርግጥ ሲቪል ሰርቫንቱ ፐብሊክ ሰርቫንቱ መልካም አስተዳደርን ዕውን ማድረግ ያለበት ዋነኛው ምክንያት ልማትን ለማፋጠንና ዴሞክራሲውን ለማስፋት ነው። ይህን ሃቅ ሀገራችን እያካሄደች ካለችው ልማት አኳያ ስንቃኘው፤ የኢፌዴሪ መንግስት ባለፉት 26 ዓመታት መንግስት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በገበያ ተኮር ሥርዓት እንዲራመድ በማድረግ፣ ዕድገቱ ቀጣይና ተከታታይ እንዲሆን ብሎም የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል ችሏል። በዚህም በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሀገሪቱ እያስመዘገበችው ካለችው የምጣኔ ሃብት ዕድገት ተጠቃሚ በመሆን የነብስ ወከፍ ገቢያቸው እንዲያድግ ማድረግ ተችሏል።

ሆኖም በሲቪል ሰርቫንቱ ውስጥ በአሁኑ ወቅት መሻሻሎች ቢኖሩም ሙሉ ለሙሉ የህዝቡን አመኔታ ያተረፉ ናቸው ብሎ መናገር የሚያስችል አይደለም። እናም ኢህአዴግ በመግለጫው ላይ እንደገለፀው ይህን ሁኔታ ትኩረት ሰጥቶ መፍታት ያስፈልጋል። የህዝቡን አመኔታ የሚሸረሽሩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ላይ እንደ አምናው ከህዝቡ ጋር በመሆን ተገቢውን የእርምት ርምጃ በመውሰድ ጥልቅ ተሃድሶውን ማጠናከር ተገቢ ነው።

ርግጥ በአሁኑ ወቅት ገዥው ፓርቲና መንግስት ከመላው ህዝብ ጋር በመሆን የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና ችግሮችን ማስተካከል የሚቻልበት ቁመና እና አቅም ላይ ይገኛሉ። እናም ወደፊትም በጥልቅ ተሃድሶው እንቅስቃሴ ላይ የሚቀርቡ ችግሮችን በመፍታት በህዝቡ ዘንድ አሁን እየታየ ካለው የበለጠ አመኔታ መፍጠር ይገባል ብዬ አምናለሁ።

ህዝብን የሚያስከፉ የመልካም አስተስዳደር ችግሮች እንደ አምናው ዘንድሮም በተጠናከረ ሁኔታ በመለየት፤ በገጠርና በከተማ የስራ ዕድል ፈጠራ በሚመለከት ስራ ፈላጊዎችን በማወቅ፣ በማደራጀት፣ በማሰልጠንና መሰል ተግባራትን እውን በማድረግ ተጠቃሚነትን ማስፋት ያስፈልጋል። በተለይም የስራ ፈላጊዎችን ፍላጎት በማየት አቅም በፈቀደ መጠን አምና የተከናወኑ ስራዎችን ዘንድሮ ማስፋት ተገቢ ነው። ርብርቡም በዚህ ዘርፍ ጠንካራ መሆን ያለበት ይመስለኛል።

በተለይ ሙስናና ብልሹ አሰራርን በሚመለከት ከጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴው ጋር ተያይዞ ዋናው ስራ በአመላከት ላይ የሚደረግ ትግል መሆኑን እንደተጠበቀ ሆኖ ችግር ውስጥ የገቡ በፌዴራል፣ በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በሌሎች ታችኛው የአስተዳደር እርከኖች የሚገኙ በርካታ ቁጥር ያላቸው አመራሮች ላይ ፖለቲካዊና አስተደዳራዊ ርምጃ መወሰዱ የአምናው ጥንካሬ ነው። ይህ ጥንካሬም ዘንድሮም ሀዝቡን ባሳተፈ ሁኔታ በተጠናከረ ሁኔታ ተፈፃሚ መሆን አለበት።  

ኢህአዴግ በመግለጫው ላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወሰን ጋር ተያይዞ ይነሱ የነበሩ ችግሮች የተፈቱና መፈታት መጀመራቸውን ገልጿል። በዚህም በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ፣ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም በኦሮሚያና በቤንሻንጉል ከወሰ ጋር የተያያዙ ችግሮችን መፍታት መቻሉን ጠቅሷል። በተጨማሪም በትግራይና በአማራ ክልሎች መካከል የነበሩትን ችግሮች በመፍታት ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውንም እንዲሁ። አያይዞም በበኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል አሁንም ትኩረት የሚሹ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን ገልጿል።

ርግጥ ከድንበር ጋር ተያይዘው ይፈጠሩ የነበሩ ችግሮችን በመፍታት ረገድ ረጅም ርቀት መጓዝ ተችሏል። ሆኖም በኦሮሚያና በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች መካከል ከወሰን ባሻገር የሚታዩና ከፌዴራላዊ ስርዓታችን ጋር አብረው የማይሄዱ አንዳንድ ተግባራት ገዥው ፓርቲና መንግስት በህገ መንግስቱ አግባብ መሰረት ተገቢውን እርምት መውሰድ ይኖርባቸዋል።

ለዘመናት ተጋብተውና ተዋልደው የኖሩትን የኦሮሚያንና የኢትዮጵያ ሶማሌን ህዝቦች ለማጋጨት ላይ ታች የሚሉ አመራሮችም ሆኑ ተመሪዎች በጉዳዩ ዙሪያ ባላቸው ተሳትፎ መጠን ሊጠየቁ ይገባል። ማናቸውም አለመግባባቶች በህገ መንግስቱ መሰረት እንደሚፈቱ እየታወቀ፤ በህዝቦች ደም ተራ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሯሯጡ የህዝብ ጠላቶች ካሉም ተጣርቶ ተገቢው የማስተካከያ ርምጃ መወሰድ አለበት። ይህ ሲሆንም የህዝቦቹን ዘላቂ ሰላም ዋስትና እንዲያገኝ ማድረግ ይቻላል።

ርግጥ ማንም ሰው ቢሆን ገዥው ፓርቲና መንግስት የተካሄደው ጥልቅ ተሃድሶው ሀገሪቱን ከመስቀለኛ መንገድ የታደገ፣ በተቀመጠለት አቅጣጫ በመተግበር ላይ ያለና የህዳሴውን ጉዞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ያደረገ መሆኑን ይገነዘባል። በተለይም የስርዓቱ አደጋ የሆኑትንና ጫፍ ደርሰው የነበሩትን እንደ ትምክህትና ጠባብነት ያሉ ችግሮች ላይ በተካሄደው ጠንካራ ትግል አመለካከቶቹ እየተቀረፉ ነው—አሁንም ቀሪ ስራዎች ቢኖሩም።  

ያም ሆኖ ግን የጥልቅ ተሃድሶው ሂደት በድርጅቱ አመራርና አባላት እንዲሁም በመንግስት ስራ ላይ በተሰማሩት ሲቪል ሰርቫንቶች ዘንድ መነቃቃትን ከመፍጠር ባሻገር ለበለጠ ትግል እንዲነሳሱ አድርጓቸዋል። ህዝቡም ቢሆን ቀስ በቀስ ከማማረር ወጥቶ ችግሮች በሂደት ሊፈቱ እንደሚችሉ የተመለከተበት መድረክ ሆኗል።

ይህም ገዥው ፓርቲና መንግስት ሀገራችን ውስጥ እውን እንዲሆን ያደረጉት ፌዴራላዊ ስርዓት በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ ማናቸውንም ችግሮች የመፍታት ብቃትና አቅም ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቀው ያደረገ ይመስለኛል።

በጥቅሉ በጥልቅ ተሃድሶው የተገኙ ውጤቶች በቀጣዩ ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሶስተኛው ዓመት ላይ ህዝቡን ከጫፍ እስከ ጫፍ በማነቃነቅ ሊጠናከሩ ይገባል። ይህን ማድረግ የኢትዮጵያን ህዳሴ በቅርበት ለማየት የሚደረገውን ጥረት ማጎልበት ይሆናል ብዬ አምናለሁ።  

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy