Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል መካከል ሳይፈታ የቆየው የወሰን ጉዳይ በህዝብ ተሳፎ እና በስምምነት በዛሬው እለት ተፈታ 

0 663

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ሰበር ዜና

በአማራ ክልል ጠገዴ እና በትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ መካከል የነበረው ለረጅም ዓመታት ሳይፈታ የቆየ የወሰን ጉዳይ በዛሬው እለት በጠገዴ ወረዳ ቅራቅር ከተማ ላይ የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድሮች በተገኙበት በተደረሰ ስምምነት ተፈቷል ፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ዓመታት ሲያወዛግቡ የነበሩት በግጨው በረሀ የሚገኙት የማይምቧ ፣ ሰላንዴ እና የአየር ማረፊያ ሰፋፊ የእርሻና ኢንቨስትመንት ቦታዎች ወደ አማራ ክልል ጠገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡ እንዲሁም በግጨው እና በጎቤ የሚገኙ የትግሬኛ ተናጋሪዎች ያሉባቸው ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ደግሞ ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ ተከልለዋል፡፡ ወደ ትግራይ ክልል ጸገዴ ወረዳ በተካለሉት ሁለት የመኖሪያ መንደሮች ዙሪያ የሚገኙ ሳፋፊ የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች በአማራ ከልል ውስጥ እንዲካለሉ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት ለረጅም ጊዜያት ሲያወዛግቡ የነበሩት ሳፋፊ የእርሻ እና የኢንቨስትመንት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ወደ አማራ ክልል የጠገዴ ወረደ እዲካለሉ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ወደ አማራ ክልል በተከለሉ ቦታዎች ላይ የሚኖሩ የትግራይ ክልል ተወላጆች የሚያከናውኗቸው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በሙሉ በአማራ ክልል ህግ የሚተደዳዳረሩ መሆኑ በስምምነተት ላይ ተደርሷል፡፡

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy