Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

በአቶ አለማየሁ ጉጆ ስም 16 ግለሰቦች የተካተቱበት የሙስና ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ሊመሰረት ነው

0 388

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

በከባድ የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር በዋሉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ኤዴታ በነበሩት አቶ አለማየሁ ጉጆ ስም 16 ግለሰቦች የተካተቱበት የምርመራ መዝገብ ተጠናቆ ክስ ሊመሰረት ነው፡፡

16 ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራው አጠናቆ ለአቃቤ ሕግ ማስረከቡን ያረጋገጠው ፖሊስ፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የነበሩት አቶ ደጉ ላቀውም በዚሁ መዝገብ እንዲካተቱ ፍርድ ቤት አዟል፡፡

ክስ እንዲመሠረት ለመስከረም 12፣2010 ቀጠሮ በተያዘለት በዚህ መዝገብ ጳጉሜ 3/2ዐዐ9 በቁጥጥር ሥር የዋሉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስትር ዴኤታ አማካሪ የነበሩት አቶ ደጉ ላቀው 17ኛ ሆነው እንዲካተቱ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት  ትላንት  ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪ ደጉ ላቀው የትራንስ ናሽናል የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ኩባንያ ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር የነበረው የፕሮጀክት ውል መጠናቀቁን እያወቁ፣ ኩባንያው ከውጭ ከቀረጥ ነፃ ስምንት ተሽከርካሪዎችን በመሥሪያ ቤቱ ስም እንዲገቡ በማድረግ መንግሥትን 1ዐ ነጥብ 5 ሚሊዬን ብር እንዲያጣ አድርገዋል በሚል የሙስና ወንጀለ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ የሆኑት አትክልት ተስፋዬ 2ዐ ሚሊዬን ብር የሚገመት ጠጠርና ብረት ለየማነ ግርማይ ጠቅላላ ተቋራጭ በማዋስና ሳይመልስ በመቅረቱ ባደረሱት ጉዳት ተጠርጥረው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡

አቶ አትክልት ተስፋዬ ጉዳያቸው ከተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በቁጥጥር ሥር ከዋሉት  ከእነ አበበ ተስፋዬ የምርመራ መዝገብ ጋር ተጣምሮ እንዲቀርብለት ፍርድ ቤት ትዕዛዙን ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ፕሮጀክት ፅሕፈት ቤት ዋና ሥራ አሰኪያጅ በነበሩት ግለሰብ ስም ሲካሄድ የነበረው ምርመራ ለመስከረም 5፣2010 ክስ እንደቀርብበት ችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል፡፡

ሪፖርተር፡‑ አባይነህ ጥላሁን

 

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy