Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ኢትዮጵያና ጣልያን የ125 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

0 364

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ኢትዮጵያና ጣልያን የ125 ሚሊዮን ዩሮ የልማት ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ አድማሱ ነበበ እና በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ሚስተር ጁሴፔ ሚስትሬታ ሁለቱን አገራት ወክለው ስምምነቱን በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል።

የትብብር ማዕቀፍ ስምምነቱ ከያዝነው ዓመት አንስቶ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በኢትዮጵያ የተቀናጀ፣ሁሉን አቀፍና ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ማገዝ ዋንኛ አላማው ነው።

ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የግብርና ልማት፣መሰረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት፣ የአስተዳደርና ስደተኞች አቅም ግንባታ የትብብር ማዕቀፉ የሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ናቸው።

በስምምነቱ አማካኝነት ለሚከናወኑት ስራዎች የጣልያን መንግስት ለኢትዮጵያ የ125 ሚሊዮን ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን 45 ሚሊዮን ዩሮ በእርዳታ መልክ ሲሆን 80 ሚሊዮን ዩሮው በረጅም ጊዜ ብድር የሚመለስ ነው።

64 ሚሊዮን ዩሮው መንግስት በግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች፣ ለእሴት ሰንሰለት ልማት፣ የስራ ፈጠራ ልማት፣ በቆዳ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሚያከናውናቸው ስራዎችና ድርቅን ለመቋቋም መንግስት ለቀረጸው ፕሮጀክት ማስፈጻሚያ ይውላል።

የተቀረው ገንዘብ ለንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ንጽሕና አጠባበቅ ላይ የሚያተኩረው ዋሽ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ፣ በአነስተኛና መካከለኛ የገጠር ቀበሌዎች ለሚከናወኑ የጤና ስራዎች እንዲሁም በአስተዳደርና ስደተኞች ጉዳይ ለሚከናወኑ ተግባራት የሚውል ነው።

የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትር ዴኤታ አቶ አድማሱ ነበበ በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት የስምምነቱ መፈረም አገራቱ ለረጅም ጊዜ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ያግዛል።

ሁለቱ አገራት በኢኮኖሚ፣ በባህልና ፓለቲካው ዘርፍ ረጅም ጊዜ የቆየ ግንኙነት እንዳላቸው አውስተው የጣልያን መንግስት ከኢትዮጵያ የልማት አጋሮች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

አገሪቷ በዋንኛነት ትኩረት በምታደርግባቸው የልማት ስራዎች በሚያደርገው ድጋፍ ተጠቃሚ እንደሆነች ገልጸው መንግስት ለስራዎቹ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ገንዘብ በአግባቡና ለታለመት አላማ በመጠቀም ውጤታማ ስራ  እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የጣልያን አምባሳደር ሚስተር ጁሴፔ ሚስትሬታ በበኩላቸው ስምምነቱ አገራቱ በልማቱ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የሚያግዝ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ስራዎች ጣልያን የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምቀጥል ነው አምባሳደሩ ያረጋገጡት።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy