Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

ከ100 በላይ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የፋይናስ መመሪያ በመጣስ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ አድርገዋል

0 573

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

ከ100 በላይ ለፌደራል መንግስት ተጠሪ የሆኑ ተቋማት የፋይናስ መመሪያ በመጣስ ከ4 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማድረጋቸው ተገለፀ።

የተቋማቱ የውስጥ ኦዲተሮች ተጠሪነታቸው የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ከሆኑ በኋላ በ10 ወራት ውስጥ በቀረበለት የውስጥ ኦዲት ሪፖርት ነው ጥስቱ የተገኘው።

በ2009 ዓ.ም ነው ተጠሪነታቸው ለፌደራል መንግስት የሆኑ ተቋማት የውስጥ ኦዲተሮች ለተቋሙ የስራ ሃላፊ የነበራቸውን ተጠሪነት በማንሳት ለገንዝብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር እንዲሆኑ መንግስት የወሰነው።

በገንዝብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር የኢንስፔክሽን ዳሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩት፥ አሰራሩ ለውጥ አምጥቷል።

በዚህም የፋይናስ መመሪያ የጣሱ 122 ተቋማት ተገቢ እርምት እንዲያደረጉ ማስጠንቀቂያ ተጽፎባቸዋል ብለዋል።

በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጠቅላላ አስተዳደር ላይ ከሚገኙት ከእነዚህ ተቋማት የተወሰኑት ማስጠንቀቂያው ተከትለው ማስተካከያ አድረገዋል።

ቀሪዎቹ ከ100 በላይ ተቋማት ግን ማስተካከያ አላደረጉም ብለዋል።

የፋይናስና የግዥ መመሪያ በመጣስ የመንግስት ገንዘብ ከመጠቀም ጀምሮ የጥሬ ገንዘብና ሌሎች ጉድለቶች የታየባቸው መሆኑንም አቶ ፍቃዱ አንስተዋል።

በ18 ተቋማት ከ2 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ጉድለት በውስጥ ኦዲት ተረጋግጦባቸዋል።

ከዚህ ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የትምህርት ሚኒስቴር ሲሆን፥ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ 2 ሚሊየን ብር የጥሬ ገንዘብ ጉድለት ነው የተገኘበት ብለዋል።

በህግ ውሳኔ እንዲያገኙ የተደረጉና አሁን በህግ ጉዳያቸው እየታዩ ያሉ አሉም ነው ያሉት የኢንስፔክሽን ዳሬክተር አቶ ፍቃዱ አጎናፍር።

በ41 ተቋማትም በጊዜው መወራረድና መስብስብ የሚገባው ከ4 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ በውስጥ ኦዲት መገኝቱን አቶ ፍቃዱ ያነሳሉ።

ለጥቃቅን ውጪ በመስሪያ ቤቶች በካዝና 100 ሺህ ብር እንዲያዝ በፋይናንስ መመሪያ ቢቀመጥም የመንግስት ሃብት ለአደጋና ብክንት በሚያጋልጥ መልኩ መያዙም ተረጋግጧል።

በ9 ተቋማት ከ7 ሚሊየን 431 ሺህ ብር በላይ ከተፈቀደው መጠን ውጪ በካዝና በመያዝ ተገኝቷል።

አራት ተቋሞች በገቢ ግብር፣ ቀረጥ እና አዋጅ ደንብና መመሪያ መሰረት ግለሰቦችና ተቋማት ከሚያገኙት ገቢ መስብሰብ የነበረበት ከ9 ሚሊየን 875 ሺህ ብር በላይ ሳይሰበስቡ ቀርተዋል።

ማንኛውም የመንግስት ገንዘብ እና ንብረት በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር በሚያሳትመው ደረሰኝ ገቢ መስብሰብ ሲኖርበት ይህን ባለማድረግ አራት ተቋማት በሚሊየን የሚቆጠር ገንዝበ የመስብሰብና ንብረት አስገብተዋል ነው ያሉት ዳሬክተሩ።

ተቋማት ለሚያወጡት ወጪ ተገቢውን ማስረጃ ወይም የወጪ ምክንያት መዝግበው መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

በ16 ተቋማት ግን ለወጪው የተማሏ ማሰረጃ ሳይቀርብ 60 ሚሊየን ብር ወጪ መደረጉ በውስጥ ኦዲተሮች በተደረገ ማጣራት ተረጋግጧል።

መንግስት ለሀገሪቱ ከሚመድበው 69 በመቶ ለግዥ እንደሚውል የሚናገሩት አቶ ፍቃዱ፥ የውስጥ ኦዲተሮች ከፍተኛ ክትትል እንዲያድረጉ መመሪያ በሚኒስቴሩ ተሰጥቷል።

በዚህም በ14 ተቋማት በ100 ሚሊየን የሚቆጠር ገንዝብ የግዥ መመሪያ ጠብቆ መከፈል ሲገባው ይህ ሳይሆን ቆይቷል ብለዋል።

ከግዥ በተጨማሪም በ13 ተቋማት ከ8 ሚሊዮን 412 ሺህ ብር በላይ መከፈል ከሚገባው በላይ ክፍያ ተፈፅሞ ተገኝቷል።

እነዚህ ተቋማት 13 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ፥ ሐዋሳ፣ መቱ፣ ደብረ ብርሃን፣ ጎንደር፣ አዳማ እና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች መሆናቸውም ታውቋል።

የፋይናስ እና የግዥ መመሪያ በመጣስ ጉድለት የታየባቸው ተቋማት ግድፈቱን እንዲያስተካክሉ ተጠይቀዋል።

ይሁንና የተወሰኑት ብቻ ሲያስተካክሉ በርካታዎቹ የእርምት እርምጃ ባለመውሰዳቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ካቤኔ ተልኮ ውሳኔ እየተጠባበቀ ይገኛል ተብሏል።

 

 

በበላይ ተስፋዬ

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy