Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የኢትዮጵያ ቀን

0 315

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የኢትዮጵያ ቀን

ዮናስ

ሃገራችን ባለፉት 10 ዓመታት በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በአገራዊ መግባባት ዙሪያ በርካታ ውጤቶችን አስመዝግባለች። ለዚህም በህዝብ የሚወከሉ ድምጾች በየደረጃው በሚገኙ ምክር ቤቶች እንዲከበሩ መደረጉ አንደኛው ማሳያ ነው። ህዝብ በመረጠው ፓርቲ መመራቱ፣ ዘላቂ ሰላም ማስፈንና ፈጣን፣ ቀጣይነት ያለውና ፍትሃዊ የኢኮኖሚ እድገት እንዲመዘገብ መደረጉ በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በአገራዊ መግባባት ለተከናወኑት ስራዎች ሁነኛ ማሳያዎች ናቸው።

በአሁኑ ሰአት በአገሪቱ የሚከሰተው ተደጋጋሚ ድርቅ ወደ ርሃብ እንዳይሸጋገር ያስቻለ አቅም ተፈጥሯል። ይህንን በኢትዮጵያ ቀን ማስቀጠል እንዲቻል በአዲሱ ዓመት በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በአገራዊ መግባባት ዙሪያ የሚከናወኑ ስራዎች የህዝብ እርካታ መፍጠር አለመፍጠራቸውን በመከታተልና ህዝብ ለሚያነሳቸው የመልካም አስተዳዳር ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ሊሆን ይገባዋል።

 ውሳኔ የተላለፈባቸው ጉዳዮች በፍጥነት እንዲፈጸሙ ማድረግ፣  የፍትህ መዘግየት እንዳይኖርና ህዝብን የማሳተፍ ሥራ ስለኢትዮጵያ ቀን (ጷጉሜ 4 ቀን) በአዲሱ አመት በትኩረት ማከናወን ተገቢ ይሆናል። ይህ ማለት ግን ስለኢትዮጵያ ቀን ባለፉት ዓመታት የጾታ እኩልነት፣ በራስ ቋንቋ የመናገርና የመተዳደር፣ ልማትና ዴሞክራሲ ተሳስረው እንዲተገበሩ የሚያስችሉ ሥራዎች በአግባቡ መከናወናቸውን መካድ አይደለም። ይህ ብቻ አይደለም፤ የህገ-መንግስት አስተምህሮን እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ማዳረስ፣ የህዝቡን ተሳትፎ የበለጠ ማጠናከር፣ ህብረተሰቡ መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ ስለመሰራቱ በጠያቂ ትውልድ መፈጠር ውጤቱ ታይቷል።  

ስለኢትዮጵያ ቀን እኛ እየተናገርን ያለው በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታና በብሔራዊ መግባባት ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ቢከናወኑም አሁንም በክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ጠንከር ያሉ ሥራዎች አልተሰሩምና ስለኢትዮጵያ ቀን በተጠናከረ መልኩ መሰራት አለበት ነው።

ይህ ሲሆን ሃገሪቷ ከድህነት ወጥታ ከበለጸጉ አገራት ተርታ ለመሰለፍና የተሻለ ውጤት እንድታመጣ ያስችላታል። የጎደለን እኮ ትንሽ ነገር ብቻ ነው። በአፈጻጸም ሂደቱ ላይ ቁርጠኛ መሆን። እንጂማ ባለፉት ዓመታት ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታና ለአገራዊ መግባባት የሚጠቅሙ ሥራዎች እና ለዚሁ የሚበጁ በርካታ መደላድሎች ተፈጥረዋል።

 የሲቪክ ማህበራት፣ መገናኛ ብዙሃን፣ የህዝብ እንባ ጠባቂ፣ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተግባራትና ህዝቡን በቀጥታና በተዘዋዋሪ የማሳተፍ ሥራዎች ተሰርተዋል። የሚቀረው ስለኢትዮጵያ ቀን እነዚህን የበለጠ እንዲጠናከሩ ማድረግ ነው። ህገ መንግስቱ ላይ መግባባት እንዲኖር፣ የተለያዩ መዋቅሮችና ሥርዓቶች እንዲፈጠሩ እና ነጻ ገበያ ሥርዓት እንዲኖር ተደንግጓል። ስለኢትዮጵያ ቀን እነዚህን ማስረጽና የበለጠ በስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ ስለምን ያቅተናል ነው? ጥያቄው። ባሳለፍናቸው 10 አመታት ካሽቆለቆልንባቸው ጉዳዮች መካከል የወጪ ንግድ ዘርፍ ዋነኛው ነው።

ስለኢትዮጵያ ቀን በአዲሱ ዓመት የወጪ ምርትን በማሳደግ የውጭ ምንዛሪ በስፋት እንዲገኝ መስራት ያስፈልጋል። በየቦታው የሚታዩ ችግሮችን በተመለከተ ህብረተሰቡ በተረጋጋና በሰከነ መንፈስ ጥያቄዎችን የሚያቀርብበትና የተሻለ ሥራ የሚሰራበት ዘመን እንዲሆን ማድረግም ስለኢትዮጵያ ቀን ይጠበቃል። ሌላው ስለኢትዮጵያ ቀን  በአዲሱ ዓመት የህግ የበላይነት እንዲከበር፣ ዴሞክራሲ እንዲጎለብት፣ በስልጣን አተያይ ላይ ያለውን የተዛባ አመለካከትን በማስተካከል የህዝብ ውግንናን ወደ ነበረበት ለመመለስ የሚያስችሉ ሥራዎችን ማከናወን ያስፈልጋል።

ባላፉት 10 ዓመታት ስለኢትዮጵያ ቀን ከተከናወኑ ስራዎች ሊደነቁ የሚገባቸውን ማድነቅና ስለኢትዮጵያችን ከፍታ ተሞክሮውንም ማስፋት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ በመሰረተ ልማት ዘርፍ የተከናወኑት ሊወሱና ሊወደሱ ግድ ነው።

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ከሚወስኑ መሰረታዊ ነገሮች አንዱ የሀይል መሰረተ ልማት እንደሆነ ሁሉም የሚስማማበት ነው። የሀይል አቅርቦት ለግብርና፣ ለኢንዱስትሪና ለአገልግሎት ዘርፎች እድገት እጅግ መሰረታዊና እንደ ደም ስር የሚታይ ነው። መንግስት ይህንን እውነታ ገና ከጅምሩ በመገንዘብ በሰጠው ልዩ ትኩረት የሀይል ምንጭ የሆኑት የውሃ፣ የነፋስና ይጂኦተርማል ሀይል አመንጪ ተቋማትን በመለየትና በመገንባት በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የነበረውን የሀገሪቱን የሀይል አቅርቦት ችግር ለመፍታት ሰፋፊ ስኬታማ የሆኑ ጥረቶችን አድርጓል። ከእነዚህ እና በአስደማሚ ሁኔታ ከተገነቡት የሀይል ተቋማት ውስጥም ዋንኛውና እንደ ምሳሌ የሚጠቀሰው በአሁኑ ሰአት በግንባታ ላይ የሚገኘው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ነው።

በሚሊኒየሙ ማግስት ወይም 2002 ላይ የመብራት አገልግሎት ከነበረው የ41 በመቶ ሽፋን በ2008 ወደ 56 በመቶ ደርሷል። በተመሳሳይ መልኩ በ2002 ዓም 2000 ሜጋ ዋት ብቻ የነበረው የማመንጨት አቅማችን በ2008 ዓም 4ሺ 269.5 ሜጋ ዋት የደረሰ ሲሆን በግንባታ ላይ ያሉ የሀይል ማመንጫ ፕሮጄክቶች ሁሉ ሲጠናቀቁ የሀገሪቱ የሀይል አቅርቦት ስለኢትዮጵያ ከፍታ ወደ 11ሺ ሜጋ ዋት ይደርሳል። እንዲሁም የማከፋፈያ መስመር ግንባታ ርዝመት በኪሎ ሜትር በ2000 ዓም ከነበረው 99ሺ 110 ኪሜ በ2008 ዓም በአማካይ 124ሺ 812.3 ኪ/ሜ ለማድረስ መቻሉም ስለኢትዮጵያ ቀን ሊወደስ ይገባዋል። በዚህ በሚፈጠረው አቅምም የሀገር ውስጥ የሀይል ፍላጎታችንን ከማሟላት አልፈን ጎረቤት ሀገራትን በመብራት ሀይል መሰረተ ልማት ማስተሳሰር እንደምንችል ጥርጥር የለውም። እየተሰራ ያለውም ከዚሁ አንፃር ነው።

የማይደረስባት ትመስል የነበረችው ግዙፍ፣ ሰፊ እና ውስብስብ አለማችን በዚህ ዘመን የአንድ መንደር ያህል በቴክኖሎጂ እገዛ ቅርብ ልትሆን ችላለች። በዚህ ዘርፍ የተፈጠረውን አለማዊ እውነታ የመጠቀም አጋጣሚ የምርጫ ሳይሆን አስገዳጅ ሆኗል፡፡ ይህን የተረዳው መንግስት የቴሌኮም አገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻል ከአናሎግ ወደ ዲጂታል ሽግግር የጀመረው ይህ ነው የሚባል የኢኮኖሚ አቅማችን ባላደገበት ወቅት የነበረ መሆኑ የመጀመሪያው ለውዳሴ የሚያበቃ ቁርጠኝነት ነው።

የውጭ ኃይሎች በዘርፍ ጫና አሳድረው ወደ ግል እንዲዛወር ያልፈነቀሉት ድንጋይ ባይኖርም መንግስት የቴሌኮም አግለግሎት ቁልፍ የኢኮኖሚ ተቋሞች ከሚባሉት ወስጥ አንዱና ዋነኛው በመሆኑ ለህዳሴ ጉዛችን ያለውን ተፅእኖ በመገንዘብ በመንግስት እጅ እንዲቆይ መደረጉ ስለሃገራችን ከፍታ ተገቢ ነው። ይህም በመሆኑ ህዝቡን በአጭር ጊዜ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ተችሏል።

መንግስት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት በ2008 ዓ.ም የተንቀሳቃሽ ስልክ ደንበኞች ቁጥር 46.0 ሚሊየን፣ የመደበኛ ስልክ ተጠቃሚዎችን 1.1 ሚሊየን እንዲሁም የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር 13.6 ሚሊየን መድረሱ ስለሃገራችን ከፍታ ሊወሳና ሊወደስ የሚገባው ነው። እንደሌሎቹ የመሰረተ ልማት አውታሮች ሁሉ የቴሌኮም ዘርፉ በእያንዳንዱ ዜጋ በራፍ ላይ ደርሷል። በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ያሉ የሁለተኛ እና የመሰናዶ ተማሪዎች ጭምር በሳተላይት ስርጭት/ፕላዝማ/ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

በተጨማሪም የፍርድ ቤት ክርክርና ውሳኔዎችን ባለጉዳዮቹ ባሉበት ሆነው በቀጥታ የቪዲዮ ኮንፍራስ እንዲከታተሉ በማድረግ አላስፈላጊ ወጪና እንግልትን በማስቀረት ለመልካም አስተዳደር መስፈን የበኩሉን አስተዋእጾ ማበርከት የቻለ አንጋፋ አውታር ነውና ለአፈጻጸሙ ውዳሴ ይገባል።

በአጠቃላይ ሀገሪቱ በመሰረተ ልማቱ ዘርፍ እያከናወነች ያለው ከፍተኛ ኢንቨስትመንት ለኢኮኖሚያዊ፣ ፓለቲካዊና ማህበራዊ እድገታችን የማይተካ ሚና የሚጫወት እና በፈጣን የእድገት ጎዳና ሮጠን ከድህነት የምናመልጥበት የሀገራችንን ከፍታ ጠቋሚ ነው፤ በመሆኑም ለዚህ ሁሉ ስኬት ውዳሴና አድናቆት መስጠት ተገቢ ነውና ስለኢትዮጵያ ቀን አድንቀናል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy