Ethiopiaprosperous
Ethiopian News Ethiopian Daily news, Regarding political and social Issues.

የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀመንበር

0 278

Get real time updates directly on you device, subscribe now.

የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ሊቀመንበር

ዮናስ
የዓለም 193 አባል ሀገራት በመሪዎቻቸው ደረጃ የሚሳተፉበት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 72ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ትናንት ተጀምሯል። በየዓመቱ በሚካሄደው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ለዓለም ሰላም እና ደህንነት ስጋት የተደቀኑ ችግሮች፣ የእድገት እንቅፋቶች፣ የጤና ስጋቶች እና የርዕዮት ዓለም ልዩነቶች ቀርበው በጉባኤው ሰፊ ውይይት ይካሄድባቸዋል። ስለሆነም የሁሉም አባል ሀገራት መሪዎችም በተመደበላቸው የንግግር ጊዜ ከዓለም ወቅታዊ ሁኔታና ከሀገራቸው አቋም አንፃር የተመጠነ መልዕክት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። በጉባኤው በዋናነት ትኩረት ሊደረግባቸው የሚችሉ ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችም ከወዲሁ የመገናኛ ብዙሃኑን ቀልብ ስበዋል።የሰሜን ኮርያ የሚሳኤል ማስወንጨፍ ድርጊትና የኒዩክሌር መርሃ ግብር በጉባኤው ትኩረት ከሚስቡ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሹ እና ኢትዮጵያ ከምትመራው የጸጥታው ምክር ቤት ጋር ተያያዥ ጉዳይ ነው።
ሃገራችን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤትን በሊቀመንበርነት ማገልገል ጀምራለች። በሰኔ ወር 2016 190 አባላት ድምጽ በሰጡበት የተለዋጭ አባልነት ምርጫ 185 ድምጽ በማግኘት ያሸነፈችው ኢትዮጵያ ለሁለት አመታት በተለዋጭ አባልነት የምትቆይ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በ1967 እና 1989 ተመርጣ የነበረ መሆኑ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎ ደግሞ ለመጪው አንድ ወር ምክር ቤቱን በሊቀመንበርነት ትመራለች ።ትናንት የተጀመረውን ጉባኤ በሊቀመንበርነት የመራችው ሃገራችን የጸጥታው ምክር ቤት ሰሜን ኮርያን ወደሰላም ድርድር ለማምጣት ማንኛውንም አማራጭ እንዲጠቀም ጠይቃለች። የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይና መልእክተኛ አምባሳደር ተቀዳ አለሙ ምክር ቤቱ ሰሜን ኮርያን ለድርድር ጠረጴዛ ለማቅረብ ማንኛውንም አማራጭ ሊጠቀም እንደሚገባም ጭምር ነው ያሳሰቡት ። ጥያቄው በአለም አቀፍ መድረክ ፊት በዚህ ደረጃ ላይ ያቆመን ሚስጥር ምንድነው? የሚለው ይሆናል።

ጉዳዩ በጥቅሉ ሲታይ ኢትዮጵያ ለዓለም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ላበረከተችው አስተዋጽኦ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተሰጠ ዕውቅና መገለጫ ስለመሆኑ አያጠያይቅም።
ይህ ብቻ አይደለም በሚቀጥለው ወር ሃገራችን በሰላምና መረጋጋት ዙሪያ አንድ ዓለም አቀፍ ስብሰባ ታስተናግዳለች።ስለሆነም ይህ ሁሉ አለማቀፋዊ እውቅና ከየት የመጣ ነው ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል ማለት ነው።
የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከሁሉ በፊት የውጭ ጠላት በማፈላለግ ላይ የተመሰረተ እንዳይሆን፣ ይልቁንም ድህነትና ኋላ ቀርነታችን ዋነኞቹ ጠላቶቻችን እንደሆኑ በመቀበል፣ እነዚህን በህዝብ ጥረት ለማስወገድ በተቀረፀ ፖሊሲ የሚገዛና የሚመራ መሆኑ የመጀመሪያው ምክንያት ነው።
የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴያችን የተመሰረተው በአገር ውስጥ ድህነትና ኋላቀርነትን በማጥፋት ትግል ላይ መሆኑ እሙን ነው።ይህ በጠንካራ ህዝባዊና አገራዊ ጥቅምና ላይ የተመሰረተው የውጭ ግንኙነት አቅጣጫ ኢትዮጵያ ከመቼውም ጊዜ የላቀ ተቀባይነት እንዲኖራትና አገራዊ ጥቅሟንም እንድታሰፋ ያስቻላት ነው። ይህ ከቅርብ ጎረቤቶች ጀምሮ ከመላው አፍሪካ ጋር፣ ከዚያም አልፎ ከልዩ ልዩ የዓለም ማህበረሰቦች ጋር በተፈጠረው መልካም ግንኙነትና ለዓለም ሰላም ባበረከትነው አስተዋፅኦ እንዲሁም በገነባነው መልካም አተያይ ከላይ በተመለከተው መልኩ ተረጋግጧል።
የቅርብ ጎረቤቶቻችን ከቆየው “ጠብ ያለሽ በዳቦ” ዘመን በተለየ ሁኔታ፤ ኢትዮጵያ የሰላማቸው፣ የእድገታቸውና የተጠቃሚነታቸው ምንጭ ልትሆን እንደምትችል የተገነዘቡበት ግንኙነት ተፈጥሯል። ከኤርትራ መንግስት በስተቀር፣ ከሶማሊያ እስከ ኬንያ፣ ከሰሜን ሱዳን እስከ ደቡብ ሱዳንና ጅቡቲ ካሉ አጎራባች አገሮች ጋር የፈጠርነው መልካም ግንኙነት በአገራችን በጎ እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው።
በራሱ በኤርትራ መንግስት ተናዳፊ ባህሪ ምክንያት የተፈጠረው ምስቅልቅልም በወሳኝነት የኢትዮጵያ ነው የማይባል ድክመት የፈጠረው ነው። በመሆኑም ከኤርትራ መንግስት በስተቀር የኤርትራን ህዝብ ጨምሮ ከሁሉም አጎራባች መንግስታትና ህዝቦች ጋር ያለን ወዳጅነት ጠንካራ መሆኑም የአለምን አሰላለፍ ወደኛ መቀልበስ አስችሏል። ኢትዮጵያ ለችግራቸው የምትደርስ አገርና ፅኑ አጋር መሆኗን የሚቀበሉ አገሮችና ህዝቦች የተበራከቱትም ለዚህ ነው።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልማት፣ ሰላምና ዴሞክራሲ ይጠናከር ዘንድ የተጫወተችው ሚናም ሌላኛው ምክንያት ነው። ከምንም ነገር በፊት ኢትዮጵያ ራሷን በማንም ላይ የምትጭን ሸክም ላለመሆን ያደረገችው እንቅስቃሴ ለፈጣንና ህዝብ የሚጠቀምበት እድገት ያበቃት መሆኑ፣ በአፍሪካውያን ዘንድ በጎ ምሳሌ ሆና እንድትታይ አድርጓታል።
ከመቶ ዓመታት በፊት በቅኝ ገዥዎች ላይ በተጎናፀፈችው አንፀባራቂው የአድዋ ድል ለመላ አፍሪካውያን የኩራት ምንጭ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻና በ21ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ ደግሞ ስኬታማ የኢኮኖሚ ሞዴል ተደርጋ መታየት ጀምራለች። በዚህ ላይ አፍሪካውያን ወገኖቻችን በሚቸገሩበት ጊዜ ሁሉ ግንባር ቀደም ደራሽ ለመሆን ችላለች።
ከሩዋንዳ እስከ ቡሩንዲ፣ ከሱማሊያ እስከ ላይቤሪያ፣ ከደቡብ ሱዳን እስከ ሰሜን ሱዳን ባሉ የግጭት አጋጣሚዎች ሁሉ ከማንም በፊት ደርሳ ከባዱን ሸክም ለመሸከምና አገራቱን ከግጭት የፀዱና የተረጋጉ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ተጫውታለች።
በዚህ ላይ እንደኔፓድና የአፍሪካ ህዳሴ የመሳሰሉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ መሆኗ፣ በዓለም አደባባይ የአፍሪካውያንን መብትና ጥቅሞች ማዕከል ባደረገ ጥብቅና መሟገቷ ሁሉ ተዳምሮ አገራችን የአፍሪካውያንን ልባዊ ድጋፍና ፍቅር እንድታተርፍ ከማስቻሉም በላይ በአለም መድረክ ፊት ሞገስ እንድታገኝ አስችሏታል።
ከአፍሪካውያን ጋር በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ለመንቀሳቀስ ዝግጁ መሆኗ፣ በኢነርጂ ልማትና በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቿ አጠቃቀም ላይ በተከተለችው የአርቆ አስተዋይነት መንገድ በተለምዶ በጠላትነት ይመለከቷት ከነበሩ መንግስታት ሳይቀር የተሻለ ግንኙነት ልትፈጥር መቻሏ በእርግጥም የአለምን አሰላለፍ ወደኛ መቀልበስ ቢያስችላት ቢያንስባት እንጂ አይበዛባትም።
ከምንም ነገር በላይ የኢትዮጵያንና የአፍሪካ መብትና ጥቅሞች ማዕከል በማድረግ፣ በዚህ ረገድ የተፈፀሙ ታሪካዊ ስህተቶች እንዲታረሙና እንዳይደገሙ በመከላከል፣ በእነዚህ ምትክ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ለራሱ ሲል ከእኛ ከአፍሪካውያን ጋር በቀና መንፈስ እንዲተባበር ሃገራችን ያደረገችውም ከፍተኛ ጥረት የተሳካ ሆኗል።
ይህ ጥረት ኢትዮጵያ ከነባርም ሆነ ከአዳዲስ ጎራዎች ነፃነቷን አስጠብቃ የማንም ተላላኪ ሳትሆን በመንቀሳቀሷና በዚህም ደግሞ ለጋራ ፍትሃዊ ጥቅሞች በመሰለፍ ረገድ አስተማማኝ አጋር መሆኗን በማረጋገጧ ከሁሉም ልዕለ ሃያላን ሳይቀር በጎ ግንኙነት ለመመስረት ያስቻላት ድንቅ ስኬት ነው።
ከአውሮፓ ህብረት እስከ ተባበረው የአሜሪካ መንግስት፣ ከሩሲያ እስከ ቻይና፣ ከጃፓን እስከ ኮሪያ ድረስ ካሉ አገሮች ጋር መልካም ግንኙነት ፈጥራለች። ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ደቡብ አሜሪካና አውስትራሊያ ድረስ ካሉ አገሮች ጋር በበጎ ምልከታ ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ገንብተናል። ይህ ሁሉ ተዳምሮ በዓለም አቀፍ ግንኙነት ከሁሉም ጋር ፍቅርና ትብብርን የምታስቀድም አገር ለመገንባትና በዚያው ልክ ደግሞ ተጠቃሚነታችን እንዲሰፋ ለማድረግ አስችሎናል።

Leave A Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.

This website uses cookies to improve your experience. We'll assume you're ok with this, but you can opt-out if you wish. Accept Read More

Privacy & Cookies Policy